በሜዲትራንያን ባህር የስደተኞች መሞት እየጨመረ ነው

TMP – 24/02/2017

በሜዲትራንያን ባህር የሚሞቱ ስደተኞች ቁጥር በአሁኑ ሰዓት እየጨመረ መምጣቱ እየተገለጸ ነው፡፡ አምና በዚህ ወቅት ከነበረዉ የሟቾች ቁጥር ሲነፃፀር መጨመሩን የተገለፀ ሲሆን በአካባቢዉ የነብስ አድን ሰራተኞችና መርከቦች ቢጨምሩም የሟቾች ቁጥር ግን እየበዛ ነዉ ተብሏል፡፡

ፍሮንቴክስ የተባለ የአዉሮፓ ህብረት የባህር ጥበቃ ኤጀንሲ ባወጣው መረጃ 2017 የነብስ አድን ስራው የሚያበረታታ ቢሆንም ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ስደተኞችን ለሞት የሚዳርጉበት ተግባርም በዚያዉ ልክ ጨምሯል፡፡

ሪፖርቱ በዚህ ዓመት መጀመሪያበዚህ ዓመት, ለባሕር ጉዞ የማይበቁ እና ከአቅም በላይ ሰዎች በበዙባቸው መርከቦች ላይ ታጭቀው የነብስ ኣድን መርከቦች እንደሚገኙ በማመን አደገኛ የባህር ክልል መጓዝ፡”  እና ስደተኞች በእንደዚህ ዓይነት አደገኛ ጉዞ የሚጓዙትአውሮፓ ለመድረስ ሰብዓዊ እርዳታ የንብስ ኣድን እርዳታ መኖሩ ኣአውቀውና እሱ ላይ በመታመን ነው፡ብለዋል፡፡

የአዉሮፓ መሪዎችአሳዛኝ እንቆቅልሽተጋርጦባቸዋል ያሉት የተቋሙ ዳይሬክተር ፋብሪስ ሌገሪ፡ የህገወጥ ስደተኞችን ህይወት ከአደጋ ለመታደግ ከአምናዉ በተሻለ መርከቦች ቢሰማሩም፡ ህገወጥ አዛዋዋሪዎችዎ በዚያው ልክ ከእንጨትና ፕላስቲክ በተሰሩ ጀልባዎች ብዛት ያላቸዉ ስደተኞችን በመጫን ለሞት አደጋ የመጋለጥ እድሉ እንዳባባሱት ገልጸዋል፡፡

በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው በፍለጋ እና ነፍስ አድን ስራ በሚድትራንያን ባህር የተሰማሩ ወገኖች ባለማወቅም ቢሆን የህገወጥ አዘዋዋሪችና የሰዉ ነገዴዎችን ስራ እንዲሳካ በማድረግ ዓላማቸውን ለመተግበር በአነስተኛ ወጪ የተሳካ ውጤት ለማግኘት እና ያላቸውን የንግድ ሞዴል ለማጠናከር አስችሏቸዋል፡ብሏል፡፡ ሌገሪ አምና 2016 4500 ስደተኞች መሞታቸው፡አሳዛኝና ምክንያቱ የታወቀ ነው፦ በጣም አነስተኛ ጀልባዎች ላይ ብዛት ያላቸዉ ስደተኞች ታጭቀዉ እየመጡ ነው፡ብለዋል፡፡

ምንም እንኳን የነፍስ አድን ጀልባዎች በትክክለኛዉ የሊቢያ የባህር ክልል ቢኖሩም ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ግን በዚያዉ ልክ ግድ የማይሰጡትና ጉልበታም ሆነዋል ብሏል የፎሮንቴክስ ሪፖርት።

ከአንድና ሁለት ዓመት በፊት በሊቢያና በኢጣልያ የባህር ክልል ግማሽ መንገድ ላይ የጀልባዎች መስመጥ ይታይ ነበር  አሁን ግን በሊቢያ የባህር ክልል ዉስጥ ናቸው ሲጠፉ የሚታዩት፡ሲልም ሪፖርቱ ገልጿል።

በጥር 2017 ከሊቢያ ወደ ጣልያን በሜዲትራንያን ባህር በመጓዝ ላይ የነበሩ 228 ስደተኞች መሞታቸዉ፡ በቅርብ ዓመታት ውስጥ የወሩ ከፍተኛ ጠቅላላ ቁጥር እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የአዉሮፓ ህብረት 70% ከአፍሪካ ወደ አዉሮፓ በሚድትራንያን ባህር የሚጓዙት ህገወጥ ስደተኞች የእርስ በርስ ግጭትን ወይም ሰብአዊ መብትን ረገጣ ሽሽተዉ እንዳልሆነ ገልጾ እነዚህ የጥገኝነት ጥያቄአቸዉ ተቀባይነት እንደሌለዉም ያስታውቃል፡፡