የስደተኞች ፍልሰት መደበኛ ዋስትና ያለው እንደሚያደርግ የታመነበት ስምምነት በ164 ሃገሮች ድጋፍ አገኘ

የደተኞችን ደህንነትና መብት የሚያስጠብቅና ህገወጥ ስደትን የሚያስቀር 193 አባል ሃገራት 164 ሃገራት የደገፉት ዓለም አቀፍ ስምምት በኖሮኮ ማራካሻ ታሕሳስ 10/2018 / .. ተፈርሟል።

ስምምነቱ አለም አቀፍ ሲሆን የሰደትን አመራር የሚያሳይና 23 ዋና ዋና አላማዎችን  ያካተተና ለህጋዊ ሰደት አዲስ እድል የሚከፍትና ህገወጥ ስደትን የሚያስቀር ሲሆን የራስ ስነምግባርና መመዘኛ ነጥቦችን ያካተተ መሆኑም ታውቋል።

የተባበሩት  መንግስታት ዋና ፀሃፊ ኣንቶንዮ ጉተሬዝ እንደገለፁት የስምምነቱ ዋና ዓላማ የስደተኞችን ስቃይና እንግልት እንዲሁም ስርዓተ አልበኛነት የሚከላከል ፍኖተካርታ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣን ስዊስ አርበር የስምምነቱ የወደፊቱ ጠቀሜታ ሲገልፁ ስምምነቱ በሚልዮኖች ለሚቆጠሩ ህዝቦች ማለትም ስደተኞች ከኋላቸው ትተዋቸው የመጡት ቤተሰቦችና በሚገቡበት ያሉትና የሚያስተናግዷቸው /ሰብ አባላት ህይወት ላይ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ሁሉም ሃገራት ስምምነቱን አልተቀበሉትም። ብዙ ሃገሮች ከስምምነቱ ወጥተዋል እነዚህም ሃገራት አሜሪካ ኣውስትራልያ፡ ቺለ፡ ቸክ ሪፓብሊክ፡ ጥልያን ፡ ሃንጋሪ፡ ፖላንድ ላቲብያ ሰሎባክያና ዶሞኒካ ሪፐብሊክ ናቸው። ሌሎች መንግስታት እንደ እስራኤልና ቡልጋርያም ስምምነቱን እንደማይፈርሙ ገልፀዋል።

አንተንዮ ጉተሬዝ በማራካሻ ተገኝተው ስምምነቱን አስመልክተው የአንዳንድ መንግስታት ስጋቶች ሲገልፁ ስምምነቱ አስገዳጅ አለመሆኑና የአገርን ሉኣላዊነት እንደማያሰጋም ገልፀዋል። በሃገሪቱ የስደተኞችን ፖሊሲ ጫና እንደማይፈጥርና እንደመሳርያም እንደማያገለግል በአፅንኦት ገልፀዋል። በተጨማሪም ሲገልፁ ስምምነቱ ለአለም አቀፍ ትብብር መነሻ እንደሚሆንና በመንግስታት መካከል ትብብርና በመልካም ጎንና እምነት በመተባበርን የሚጋብዝ ነው ብለዋል።

የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌናሜርክል ሲገልፁ ስምምነቱ ህገወጥ ሰደት ከማበረታታት ይልቅ እንደሚከላከል ይህም ደህንነታቸው የተጠበቀ በህጋዊና መደበኛ በሆኑ ሁኔታ የሚካሄድ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ይህንን ጉዳይ የስራ ጉዳይ ተሎ የሚተው ጉዳይ አለመሆኑና ችግሩንም አይፈታውም ብለዋል።

ብዙ የአህጉርና ዓለም አቀፋዊ የአብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ስምምነቱ በጣም ጠቃሚ ችግር ፈቺ እና የስደተኞችን መብት የሚያስከብር ነው ብለውታል። የህፃናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) ትምህርትና የጤና አገልግሎት እንዲያገኙና ከጉልበት ብዝበዛና ስቃይ እንደሚከልላቸው ገልፀዋል።

ይሁን  እንጂ በሶስተኛው ወገን ህጉ አስገዳጅ አለመሆኑ ስጋት እንዳለ ገልፀዋል። የአለም አቀፍ መስቀል ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ሲገልፁ ይህንን ችግር ለማስቀረት ቆርጠን ከተነሳን ስምምነቱ በስነምግባር ደረጃ አስገዳጅ መሆን አለበት ብለዋል።

የተ.. ጠቅላላ ጉባኤ በሚቀጥለው ታህሳስ 19/2018 / (..) ስምምነቱን ያፀድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል።

TMP – 18/12/2018

ፎቶ: UNDESA/twitter. ማራኮሽ, ሞሮኮታህሳስ 10, 2018-ስብሰባው የተካሄደበት ቦታ

ስለ ስደት ማወቅ የምትፈልጉት ማነኛውም አይነት ጥያቄ በኢመይል አድራሻችን ልታገኙን ትችላላችሁ።

ጥያቄዎቻችሁ በኢመይል አድራሻችን ላኩልን። ባልደረቦቻችን በፍጥነት ይመልሱላቹኋል። ሁሉም የኢመይል መልእክት
ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው።

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ