አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ሕብረት መንግስታት ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ስምምነት ለመውጣት ፍላጎታቸውን እያሳዩ ነው

አስገዳጅነት የሌለው የተ.. የስደተኞች ውል (ስምምነት) እክል እየገጠመው መሆኑ ተገለፀ:: የዚህ ምክንያት ደግሞ አባል አገራት እንደነ ፖላንድ ቼክ ሪፐብሊክ ቡልጋርያና ክሮሽያ የመሳሳሉት በታህሳስ ወር 2018 / .. ሞሮኮ ውስጥ የተፈረመውን ውል ላለመፈረም እያቅማሙ ስለሆኑ መሆኑን ታውቋል:: እነዚህ አራቱ መንግስታት የአሜሪካ የሃንጋሪና አውስትራልያ ፈለግ በመከተል መሆኑ ነው:: እነዚህ አገሮች ምክንያታቸው ሲገልፁ ስምምነቱ ህጋዊና ህገወጥ ስደትን ስለሚያደባልቅና የማይለይ መሆኑና አገሮችን ሉአላዊነትም በጥያቄ ውስጥ ስለሚያስገባ ነው ይላሉ:: የስምምነቱ ደጋፊዎች ግን ስምምነቱ አስገዳጅነት የሌለውና ሰደትን የማያበረታታና ስደትንም የማያቆም ነው ይላሉ:: የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሚሮስላቭ ላጂካክ ስምምነቱ አያስገድድም ሙሉ በሙሉም የአገሮችን ሉአላዊነትን ያከብራል ብለዋል::

ህዳር 12/2018 / .. የቡልጋርያ ጥምር መንግስት ስምምነቱን እንደማይፈርም አስታውቆ ምክንያቱ ሲገልፅም የሃገሪቱን ፍላጎት አደጋ ውስጥ ይከታል ሲል ይገምታል:: የቡልጋርያ መንግስት አቋምም ወደ ስምምነቱ እንደማትገባ ነው ሲሉ የማእከላዊው የቀኝ አክራሪ ፓርቲ  ምክትል ሊቀመንበር ሴቭታን ሴቭታኖቭ ከአመራሮች ስብሰባ በኋላ ገልፀዋል::

ቼክ ሪፐብሊክም የአለም አቀፉን ስምምነት እንደማትፈርም የመንግስት የመረጃ ምንጭ ለሮይተርስ ገልፀዋል:: የቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ምክትል ጠቅላላ ሚኒስቴር ሪቻርድ ባርቤክ ለጋዜጤኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫየቼክ ሪፐብሊክ መንግስት የህገወጥና ህጋዊ የስደት መመሪያዎችን ስትደግፍ መቆየቷና ይህም የቼክ ሪፐብሊክና ሌሎች የአውሮፓ ሃገሮች ሲያሳስቡ መቆየታቸው እና የመጨረሻው ረቂቅ እነዚህን ሃሳቦች እንደማያንፀባርቅ ይገልፃሉ::

የፖላንድ ጠቅላይ መኒስተርም ማቴውዝ ሞራዊክ ደግሞ አገራቸው ከዚህ የአለም አቀፍ ስምምነት እንደምትወጣ  ገልፀው የኛ የቅድሚያ መመሪያችንና ስራችን የአጋራችንና የድንበራችን ደህንነትን ከስደተቶች ፍሰት መቆጣጠር ነው ሲሉ  ገልፀዋል::

የክሮሽያ ፕሬዝዳንት ከሊንዳ ግራባር ኪታሮቪች ደግሞ ስምምነቱን ላለመፈረም መፈለጋቸውን ገልፀዋል:: ይህንን የገለፁት ከዩሮ አክቲቭ ጌታዎርክ ጋር ሲናጋሩ አጋራቸው ስምምነቱን እንደማትፈርም ገልፀዋል መንግስታቸው ፍላጎቱ ቢያሳኝም ቅሉ

ኦስትሪያና ሃንጋሪ ከአውሮፓ ሃገራት ስምምነቱን እንደማይፈርሙ የወሰኑት ከአሜሪካ መንግስት ቀጥለው የገለፁት ሃገራት መሆናቸው ባለፈው ሓምሌ መሆኑን ታውቋል::  

የአውሮፓ ህብረት የስድስቱ አባል ሃገራት ውሳኔ ይቃወማል:: የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ስደትንና ሌሎችም ጉዳዮች በሚመለከት በአንድነት ግንባር እንዲቆሙ የአውሮፓ ኮሚሽን ሃላፊ ጂን ክላውድ ጀንከር ሲገልፁ አንድ ወይም ሁለት ወይም ሶስት ሃገራት የተባበሩ መንግስታቱ ስምምነት ከለቀቁ እኛ እንደ አውሮፓ ህብረት ለራሳችን ፍላጎትም መቆም እንደማንችል ነው ብለዋል::

ሊዊስ አርበር የተ.. ለአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ልዩ ተወካይ የአውሮፓ ህብረትን በስጭት በማስተጋባት የስምምነቱ ዓለማ የድንበር ዘለል የሰዎችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እንደሆነ ገልፀዋል::

የተባበሩት መንግስታት የስደተቶች ስምምነት ሰነድ የተጠነሰሰው 72 ኛው የተ.. ጠቅላላ ጉባኤ በሓምሌ 13/2018 / .. ሲሆን በሞሮኮ ዋና ከተማ ማራካሻ በዚህ ዓመት ታህሳስ ወር ሁለተኛው ሳምንት በሚካሄደው የተ.. ስብሰባ እንደሚፀድቅ  የጊዜ ሰሌዳ ተይዞለታል::

TMP – 21/11/2018

ፎቶ:- ፕሮሺክ ራደኽ/ ሻተርስቶክ። የስደተ ቡዱን ሃንጋሪን ለቀው አውስትሪያ ሲገባ ጀርመን ለመድረስ ጥቅምት 6 2015