ቬና ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ስምምነት ለትወጣ ነው
አውስትሪያ የተባበሩት መንግስታት ከሚፈራረሙት የስደተኞች ውል እንደማትፈርም አስታውቃለች:: የማትፈርምበትም ምክንያት የአለም አቀፍ የስደተኞች አቀባበል ዝግጅት በቂ አለመሆኑን ተከትሎ ነው በማለት ነው:: ቬና እንደምትፈራው ከሆነ ህገ–ወጥና ሕጋዊ ስደትን ስለማይለይና የአውስትሪያን ሉአላዊነት ስለማያከብር ነው:: ስምምነቱ ማራካሻ ሞሮኮ ውስጥ በሚቀጥለው በዚህ ዓመት ታሕሳስ ወር በሚካየድ የመንግስታቱ ጉባኤ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል::
ቻንስለር ሰባስትያን ኩርዝ ለብሄራዊ ሬድዮ ስርጭት አገልግሎት እንደገለፁት “መንግስታቸው በሚያደርገው ስብሰባ አውስትሪያ የስምምነቱ አካል እንደማትሆን ተናግረዋል:: በንግግራቸውም አጋራቸው የስደተኞች ስምምነት ውስጥ ያሉት ነጥቦች እንደገና እንደሚያጤኗቸውና … የሚሰደዱና ጥገኝነት (ከለላ) ፈላጊዎችን ስለማይለይ መሆኑ አስታውቋል:”:
“በሚቀጥለው 2019 ዓ/ም እ.ኤ.አ በሚካሄደው የተ.መ.ድ ጠቅላላ ጉባኤ ድምፅ ተአቅቦ እንደሚያደርጉም ጨምረው ገልፀዋል:: አውስትሪያ ከአሜሪካና ሃንጋሪ ቀጥላ ከስምምነቱ ከወጡት አገሮች ሶስተኛዋ ሃገር መሆኑዋ ነው :: “
የሚስተር ኩርዝ ወግ አጥባቂ የአውስትሪያ ህዝቦች ፓርቲ ከተጓዳኛቸው የአውስትሪያ ነፃነት ፓርቲ በ2017 ዓ/ም እ.ኤ.አ ስልጣን መያዙ ይታወቃል:: የጥምረት መንግስቱ የፀረ ስደተኞችን አቋም በማራመድ በምርጫ በማሸነፍ የአውሮጵያ የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በ2015 ዓ/ም በማሻቀቡ ወደ ስለልጣን የመጣ ነው::
“ስደት የሰብአዊ መብት ጉዳይ አለመሆኑና መሆንም እንደሌለበት” ምክትል ቻንስለሩ ሄንዝ ክርስቲያን ስትራሽ ገልፀዋል:: “ወደ አውስተሪያ ማን መግባት እንዳለበት የምን ወስነው እኛ ነን” ሲሉም ተናግረዋል::
የተ.መ.ድ የስደተኞች ስምምነት ሰነድ በ2018 ዓ/ም (እ.ኤ.አ) በ72ኛው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የተዘጋጀው ይኸው ሰነድ በሃምሌ 13/2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ መሆኑ ፕሬዝዳንት ሚሮስላቭ ለጅክካ ሲገልፁ የስደተኞች ሰነዱ ስደትን ኣይይደግፉም ስደትንም አያቅምም ብለዋል::
የአውሮጳ ኮሚሽን ቃል አቀባይ እንደገለፀው “የአውስትሪያ መንግስት የወሰደውን አቋም አሳዝኖናል ብለዋል:: ስደት የአለም አቀፍ ችግር መሆኑና አለም አቀፋዊ መፍትሄም እንደሚያስፈልገው ሃላፊነት መስወድም እንዳለባቸውና ውጤትም የሚገኘው የጋራ ጥረት ሲኖር መሆኑና ለዚህም አውስትሪያ በድርድሩ ላይ ወሳኝና ቁልፍ ሚና እንደተጫወተች ገልፀዋል:: ፖላንድ ቅሬታዎንና ቀጥላ ከስምምነቱ ለመውጣት እንደምትችል ገልፃለች:: “
TMP – 5/11/2018
ፎቶ፥ አሌክሳንደሮስ/ ሸተርሎክ/። የአውስተሪያው ቻንስለር ሰባስተያን ኩርዝ ከአውሮጳ ህብረት መሪዎች ጋር ጥቅምት 17 2018 ስብሰባ ሲገቡ ብራስለስ ቤልጅየም።
ፅሑፉን ያካፍሉ