ጀርመን ሕገ ወጥ ስደትን ለመቆጣጠር ለግብፅና ለቱኒዝያ አገዘች

TMP – 07/04/2017

የጀርመን ጠቅላይ ሚኒስተር አንገላ መርከል በሰሜን ኣፍሪካ ጉብኝት ኣደረጉ፡፡ በዚህ ወር መጀመርያ በስደተኞችና በልማት ዙርያ ከቱኒዝያና ከግብፅ መሪዎች ተነጋገሩ፡፡

የጀርመን ኣላማ ከሁለቱም አገራት ኣብሮ በመስራት ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ ያለ የስደተኞች ፍሰት ለመቀነስ ነው፡፡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች ከአፍሪካ አገሮች እና ከሶርያ ወደ አውሮፓ ለመሻገር አሁን በግብፅ ይገኛሉ፡፡

ጀርመን፡ ግብፅ ጠንካራ እንድትሆን ለማገዝ የምትፈልገው በሜድቴራንያን ባህር ዳርቻ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ሕገ ወጥ ዝውውርን ለመግታት ነው፡፡

መርክል  ለግብፅ ቴክኒካዊ እገዛ በማድረግ ለአገሪቱ ድንበር ቁጥጥርና የባህር ዳርቻ ጥበቃ በመከናወን ሕገ-ወጥ ስደተኞች እና አሸባሪዎች በብዛት እንዳይገቡ የመቆጣጠርና የመንከባከብ ትግል ለማድረግ ፍቃደኝነታቸው ገለፁ፡፡

“ግብፅ ተጨማሪ ውይ’ይት የሚያስፈልጋቸው የቴክኒካዊ እገዛ ዕቅድ ሐሳቦች ቀርፃለች። ነገር ግን የድንበሩ ድህነትን የተመለከተ መቼ መሰራት እንዳለበት ኣስባለሁ። ጀርመን እገዛ ለማድረግ እጅግ በጣም ዝግጅ ናት፡” ሲሉ መርከል ተናግረዋል፡፡

“በግብፅ ተጠግተው የሚገኙ ስደተኞች የተለያዩ ናቸው፡፡ ለነዚህ ስደተኞች የተሻለ ኣማራጭ መፍጠር እንፈልጋለን፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪ 1000 የሚያህሉ በጀርመን የጥገኝነት ጥያቄ ጠይቀው ውድቅ የተደረጉ ግብፃውያን ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ፡፡

መርከል 528 ሚልዮን ዶላር አከባቢ ለኢኮኖሚያዊ ልማት ለግብፅ ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡ መርከል በተጨማሪ በቱኒዝያ 264 ሚልዮን ዶላር በልማት ፕሮጀክቶች ለማፍሰስ እንደተሰማሙ በቱኒዝ በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪ 1500 የቱኒዘያ ስደተኞች በጀርሞን የጥገኝነት ጥያቄ ኣቅርበው ውድቅ የሆነባቸው ወደ አገራቸው ለመመለስ እቅድ ተይዘዋል፡፡

ወደ ጀርመን መግብያ ክፍት በር ፖሊሲ ከወጣበት በኋላ ወደ 900,000 የሚደርሱ ስደተኞች ወደ አገሪቱ በምጕረፋቸው ከተለያዩ ወገኖች ነቀፌታ ስቧል፡፡ በባለፈው ታህሳስ ወር በቱኒዝያዊ ስደተኛ በኣኣሸባሪነት በኣንድ የጭነት መኪና በደረሰው ጥቃት ያከተለው ኣደጋ በርሊን ከተማ ውስጥ በልደት ገበያ 12 ሰዎች ሲሞቱ 56 ተጎድተዋል፡፡