አውሮፓ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የኢንዳስትሪ ልማት ድርጅት የስራ አማራጮችና የሱዳን ኢኮኖሚ ከፍ እንዲል ተስማሙ

በሱዳን አዲስ ፕሮጀክትና ዘላቂነት ያለው የስራ ዕድል እንዲያድግ የአውሮፓ ሕብረትና የተባበሩት መንግስታት የኢንዳስቱሪ ልማት ድርጅት 3 ሚልዮን ዶላር ለማቅረብ ተስማሙ፡፡

የአውሮፓ ህብረት ሓላፊ ተወካይ  በሱዳን አምባሳደር ጆን ማይክል ዱሞንድ እና የተባበሩት መንግስታት  የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ተጠሪ ካልድ ኢል መከወድ በመጋቢት 14 ስምምነቱ ተፈራረሙ፡፡ የአውሮፓ ህብረት እምነት  እገዛው ለአፍሪካ  ልምታዊ ክልሎችና ለስደተኞች የመጠልያ ከለላ ፕሮግራም በምብራቅ ኣፍሪቃ ለ3 ዓመታት የሚቆይ ፕሮጀክት ነው፡፡

የዚህ ፕሮጀክት አላማ የስራ አማራጪዎች ከፍ ማድረግ፣ የንግድ ስራ ማነቃቃትና ማነሳሳት፣ በወጣት ስደተኞች ፣በጥገኝነት አዳኞች  እና የስደተኞች ተቀባይ አባሎች ለካርቱም መንግስት ይውላል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ለሞያዊ ትምህርት፣ ለስልጠና፣ ለጥቃቅን የንግድ ስራዎች እድገትና ለጋዊ ከለላ፤ የውስጥ ተፋናቃዮችና ከኤርትራ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ስዳንና ከሌሎች አገሮች ለተፈናቀሉ የሚውል ነው ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ተወካይ ተናግረዋል፡፡

አባሳደር ጆን ማይክል ዱሞንድ ፕሮጀክቱ እንዴት ስራ ላይ እንደሚውል ሲያብራሩ፤ “ይህ ፕሮጀክት ለወጣቶች ስልጠና  ለጎልማሶች ስደተኞችና  ለጥገኛ ስደተኞች ለቀጣይ ስራቸው መወዳደርያ  የሚሆን ለሞያዊ ቀላል አቅም ግንባታ ይውላል፡፡ አሰልጣኞች ከአዲስ የስራ አመራጮች በቂ ጥቅም እንደሚገኙ ቃል ገብተዋል፡፡ የንግድ አገናኞችና የረጅም ግዜ ተማሪዎች  የድህነት ደረጃ ቅነሳና ስራ አጥነትን ለማስወገድ አዲስ በር ከፋች ነው፡” ይላሉ።

የአውሮፓ ህብረት እንደገና በመጋቢት መጀመርያ ሳምንት ሌሎች የፕሮጀክቶች ቁጥር በምግብ ዋስትና ዙርያ፣ ለድህነት ቅነሳ፣ ለውሃ ስራዎች፣ ሞያዊ ስልጠና፣ ጤናና ትምህርት በአንድ በከፍተኛ የሕገ ወጥ ስድተኞች የተጠቃች የምስራቅ ሱዳን ከተማ ገዳሪፍ  ተጀምረዋል፡፡

ስዳን ከአውሮፓ አገራትና ከአውሮፓ ህብረት በመተባበር በሕገ ወጥ ስደተኞችና ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ጠንካራ ስትራቴጂ በመቅረፅ ከባድ ትግል እያካሄደች ነው፡፡

አውሮፓ ህብረት ባለፈው አመት ለሱዳን 100 ሚልዮን ዶላር መድበዋል፡፡ ይህ በአገሪቱ የሚኖሩ ስደተኞች የተሻሻለ የአኗኗር ሁኔታና ለጠንካራ የድንበር ጥበቃ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 40  ሚልዮን ዶላር ከአስቸኳይ የእርዳታ ገንዘብ  ለተሻለ የስደተኞች አስተዳደር ለአፍሪካ ክልል ተሰጥተዋል፡፡