የፀረ ስደተኛ ጥቃት በጀርሞን እየተነሳሳ ነው

TMP – 07/03/2017

የጀርሞን ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት እንደሚያስታውቀው ባለፈው ዓመት ከ 3500 በላይ በስደተኞችና በመጠለያ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂዎች ጥቃቶች እንደተፈፀሙ ያሳያል፡፡

በየካቲት 26 በወጣው የመጀመርያ ደረጃ አሃዝ እንደሚያሳየው ከሆነ 560 ሰዎች ከነዚህም 43 ህፃናትን ጨምሮ ጉዳት እንደደረሰባቸው ያትታል፡፡ ሪፖርቱ ጨምሮ እንደሚያሳየው ከ 3,533 ጥቃቶች ውስጥ 2,545 የሚሆኑ በግለሰቦች ስደተኞች እና በስደት የሚኖሩ፤ 988 ጥቃቶች በጥገኝነት ጠያቂዎች መኖርያ ሆስቴሎች ላይ ሲሆኑ 217 ጥቃቶች ደግሞ በስደተኞች እርዳታ ድርጅቶችና የነፃ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ነው፡፡

የጀርመን መንግስት በቅርቡ የስደተኞች ፖሊሲው በጣም እንዳከረረውና በስደተኞች ጥቅማ ጥቅሞች ጠንከር ያሉ ህጎች፤ የጥገኝነት ጠያቂዎች ተቀባይነት ያላገኙ በቶሎ  እንዲወጡ በማድረግና በራስ ተነሳሽነት ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ስደተኞች የገንዘብ ክፍያ በማድረግ ወደ ትውልድ ሃገራቸው እንዲመለሱ ማፋጠን ይገኙበታል፡፡

የወንጀል ድርጊቶች ቁጥር በእንግሊዝና በስዊድን እየጨመረ ነው፡፡ ሁለቱም ሃገሮች በስደተኞች ጎርፍ ተጥለቅልቀዋል፡፡ ከሓምሌ 2015 እስከ ሓምሌ 2016 በጥላቻ ላይ የተመሰረቱ ወንጀሎች በ50 በመቶ በአንዳንድ የእንሊዝና ዌልስ አከባቢዎች እንደጨመረና በስደተኞች ላይ ያነጣጠ ጥቃት እንደተሰነዘረ የኣሶቼትድ ፕረስ ትንተና ያሳያል፡፡ በየካቲት 26 በስዊድን የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች ነቦሪያ ሰፈር ቫነርስቦ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ 20 ተገን ጠያቂዎች ጉዳት ደርሰባቸዋል፡፡

ብዙ የአውሮፓ አገሮች የእስላም ጦስና የስደተኞች ጥላቻ በማየት ላይ ናቸው፡፡ በቅርቡ በተደረገው  የጥናት ስብስብ እንደሚያመለክተው ከሆነ ግማሽ የሚሆኑ ሃገሮች ለስደተኞች ወደ አውሮፓ መምጣት መግባት የሚከለክል ሕግ በተለይም ከሙስለም አገሮች የሚመጡ ስተኞች ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ የሚከለክል ሕግ እንዲወጣ ይፈልጋሉ።