ከ 25 ሰዎች በላይ በሊብያ ባህረ ጠረፍ ደብዛቸው ጠፍቷል

TMP – 11/03/2017

ከሊብያ ወደ ኣውሮፓ ለመሻገር የሜዲተራንያንን ባህር ለማቋረጥ ሲሞክሩ ቢያንስ 25 ስዎእ/ስድተኞች/ ደብዛቸው መጥፋቱ በሊብያ ባህር ጠረፍ የነፍስ አድን ኦፕሬሽን ሰራተኞች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው አርብ መጋቢት 3 እንደተጠቀሰው፡፡

ከሊብያ ባህር ሃይል የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ስደተኞችን ነአንድ የፕላስቲክ ጃልባ ከመጠን በላይ ስደተኞችን አሳፍራ የነበረው ጀልባ ውሃ በማስገባቷና መስመጥ በመጀመርዋ ከናህር ጠረፍ ዋና ከተማዋ ከትሪፖሊ በስተምስራቅ 5 ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምትገኘው የታጁራ ወደብ ገና በጥዋቱ መጋቢት 3 ነበር፡፡

የባህር ሃይል ኣባላት 115 ስደተኞች ማዳናቸው ታውቋል፡፡ በህይወት የተረፉት ሰዎች ከተለያዩ ከሰሃራ በታች ካሉት ሃገሮች ሲሆኑ አንድ ከባንግላዲሽና 6 ሴቶች እንደሚገኙበት የጠረፍ ጠባቂዎች ቃል አቃባይ ጀነራል ኣዮብ ቃሲም ተናግሯል፡፡ የኛ የጠረፍ ጠባቂዎች በታጅራ አከባቢ ፍለጋ በማድረግ የጠፉትን ሰዎች ለማግኘት ቢሞክሩም የተገኘ አንድም ሰው አለመግኘቱ ጨምሮ ገልፀል፡፡

ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ከ 2017 ጀምሮ ቢያንስ 444 ሰዎች እንደሞቱ ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የተገኘው ወቅታዊ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በየካቲት ወር የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ስደተኞችን ከያሉበትና ከሊብያ ለማስለቀም የሚያስችል እቅድ ላይ መስማማታቸው ይታወቃል፡፡የኣውሮፓ ህብረት ከሊብያ መንግስት የገንዘብ የሚያደርገው የሊብያ ባህር ዳርቻዎች ከመለቀቃቸው በፊት ስድተኞችን የጫኑ ጀልባዎችን እንዲያቆሙና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት እንዲቻል ነው፡፡

ከሊብያ ወደ ጣልያን ቸገር በሚደረገው ጉዞ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እያሸቀበ በመሆኑ ሕገ-ወጥ የሰው ኣዛዛሪዎች እረፍት የለሽ እንቅስቃሴም እየጨመረ ነው፡፡ ሕገ-ወጥ ኣዛዛሪዎች ስደተኞችን አንድ ላይ በማጎርና ለባህር ጉዞ አመቺ ባልሆኑ የፕላስቲክ ጀልባዎችና ለአሳ ማጥመጃ የሚያገለግሉ የእንጨት ጀልባዎች መጠቀም  ሰዎእ አንድ ላይ ማጨቅ የተለመደ ተግባር ከሆነ ውሎ ኣድረዋል፡፡ ባለፈው ወር መጨረሻ የ 74 ሰዎችን አስከሬኖች በምዕራብ ሊብያ ዛውያ በተባለችው የጠረፍ ከተማ ኣቅራብያ መገኘታቸው ና የጀልባ ሞተርም እንደተሰረቀ ይታወቃል፡፡

በየካቲት 22 የአለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት በሊብያ የ 105 ስደተኞች መጥፋት/መሰወር/ ዘግቦ በተጠቀሰው ቀን ደግሞ 13 የሰዎች ኣስከሬኖች በውሃ ተጠርገው አልኮምስ በተባለው ቦታ ከተመሳሳይ ጃልባ የሞቱ መሆናቸው ሪፖርት ያመለክታል።