71 ስድተኞች ከ 4 ቀናት የባህር ላይ ቆይታ በኋላ ወደ ሊብያ ተመልሰዋል

በሕገ ወጥ ወደ ኤውሮጳ ለመጓዝ አስበው ለአራት ቀናት ያህል በባህር ላይ በመቆየት ህይወታቸውን አደጋ ላይ የነበሩ 71 ስደተኞች፤ በሊብያ የባህር ወሰን ጠባቂዎች ድነው መስከረም 29/2019 ወደ ሊብያ ተመልሷል።

የሊብያ ባለስልጣናት እንደገለፁት፤ እነኝህ ወደ ባህር የገቡት ስደተኞች ለአራት ቀናት ካለ ምግብና ውሃ በመቆየታቸው በተለይ ሁለቱ በጣም የተዳከሙ ቢሆንም ህይወታቸው ግን እስከ አሁን አለ።

አላርም ፎን የተባለ በሜዲትራንያን ባህር ስድተኞችን በመደገፍ የሚንቀሳቀስ ግበረ ሰናይ ድርጅት ስለ ሁኔታው ሲገልፅ፤ ባህር ውስጥ ችግር ላይ የነበሩ እነዚህ ስደተኞች የአስቸኳይ ድርሱልን ጥሪ ብያደርጉም፤ የጣልያንና የሊብያ ባለስልጣናት መልስ ሊሰጥዋቸው አልቻሉም ብለዋል። እንደ ግባረ ሰናይ ድርጅቱ ከሆነ፤ “ ስደተኞቹ ለ80 ሰአታት ባህር ላይ ቆይተው ህይወታቸው ሊያልፍ ቀቢፀ ተስፋ ላይ ከደረሱ በኋላ የሊብያ ወሰን ጠባቂዎች እንደገኝዋቸው ገልፆል ።”  የጣልያንና የሊብያ ባለስልጣናት ግድየለሽነት ግን በጣም አሳፋሪ እንደሆነ አመልክተዋል።

 “ ድርጅቱ መስከረም 29 በቲዊተር ገፅ እንደፃፈው ይህ ግድየለሽነት ራሱ ቅሌት ነው። ሁለቱም በጣም የተዳከሙ ስደተኞች ህይወታቸው ይተርፋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ይህ የሊብያና የኤውሮጳ አገራት ጣምራ ያለ መተግበር ፖሊሲ ግን ቅሌት ነው ”ብለዋል።

በርካታ ስደተኞች ሊብያ ላይ ከደረሱ በኋላ፤ የሊብያ ባለስልጣናት ችግር ፈቺዎች አይደሉም ብለው ስለሚያምኑ፤ ከሊብያ ቶሎ ለማምለጥ ይሞክራሉ።

አንድ አል ካሁማስ የተባለ የባህር ሃይል አባል እንደሚናገረው “ በመሰረቱ ስደተኞችን በሃል ወደ ማጎርያ ካምፕ አስገቡ የሚል ትእዛዝ የለም። ባለስልጣናትም ወደ ማጎርያ ካምፑ እንድንወስዳቸው አያዙንም “  ይላል።

ትሪፖሊ ላይ ያለው የሊብያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ቃል አቀባይ ኢዮብ ቃሲም እንደሚለው ግን፤ ስደተኞች የተለቀቁት ወደ ተጨናነቀው ማጎርያ ካምፕ ሊወሰዱ ሙከራ በተደረገ ጊዜ ነው ካለ በኋላ፤ በዚሁ ማጎርያ ካምፕ ውስጥ የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደሚፈፀሙ ብዙ ጊዜ ሪፖርት ይደረጋል ብሏል ።

ሊብያ፤ ወደ ኤውሮጳ ( ጣልያን) የሚፈልሰው አፍሪካዊ ስደተኛ በጀልባ የሚተላለፍባት አደገኛ መስመር ናት። ይሁንና በዚህ መስመር ሲጓዙ አደጋ ከገጠማቸው በርካታ ስደተኞች፤ የሊብያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ሲያግዝዋቸውና ወደ ሊብያ ሲመልስዋቸው ተስተውሏል።

ይህ የሜዲትራንያን መስመር በአለም ለስደተኞች በጣም አደገኛ ከሆኑ መስመሮች አንዱ ነው። በዚህ አመት ብቻ ከ1000 በላይ ስደተኞች በዚህ መስመር ስደት ሲሞክሩ ህይወታቸው አልፏል ወይ ጠፍቷል።

TMP 17/10/2019

በዴቪድ ቦናልዶ / ስቶኮለም

የሊብያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች፤ ከሊብያ የባህር ዳርቻዎች የሚመለሱበት ህገ ወጥ ስደተኞች ለመከታተል በትጋት ይሰራሉ።