ኤርትራውያን ስደተኞች በሊብያ እስር ቤቶች በአስከፊ ሁኔታ ተይዘው ይገኛሉ

650 በላይ ጥገኘነት ጠያቂዎችና ስደተኞች 430 በላይ የሚሆኑ ኤርትራውያን ጨምሮ ያለ በቂ ምግብና ውሃ በአስከፊ ሁኔታ በሊብያ ዚንታን እስር ቤት እንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ /ቤት አሰታውቀዋል፡፡

በዚንታን እስር ቤት ያለው ሁኔታ ኢሰብአዊና ክብርን የሚነካ አያያዝ ወይም ቅጣት እንዲሁም ስቃይ ያለበት ነው፡፡ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ /ቤት ቃል አቀባይ ሩፖርት ኮልቪል በሰኔ 7 ቀን በጄነቫ ባደረጉት አጭር ቃለ ምልልስ አስገንዝበዋል፡፡

አብዛኞቹ እስረኞች በከፍተኛ ደረጃ በምግብ እጥረት ህመም የሚሰቃዩ፤ በጠባብ ክፍል የታሰሩና ንፅህና በሌለው ሁኔታ የሚገኙ ናቸው፡፡ በቂ የጤና እንክብካቤ ወይም በቂ ሕክምና ባለመኖሩ ከባለፈው መስከረም ጀምሮ 22 ስደተኞች ብዙ ቁጥር ያላቸው ኤርትራውያንም ጨምሮ በሳምባ ነቀርሳና ሌሎች በቀላሉ ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች ሳብያ መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ /ቤት ገልፀዋል፡፡

አንዳንድ በእስር ቤቱ ውስጥ ታስረው የሚገኙ ኤርትራውያን በሊብያ እስር ቤት ውስጥ ስላለው አስከፊ ሁኔታ ለመገናኛ ብዙሃንና ለእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡

በአጭር ግዜ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሞተዋል እኛም ለሞመት እተቃረብን ነው፡፡ እኛ ተጠቂዎች ነን፡፡ አዲስ ህይወት እንፈልጋለን፡፡ መብቶቻችን እንሻለን፡፡ ለኛ ጥቁር ታሪክ ነው፡፡ ፈርተናል፡፡ የስሜትና የስነ ልቦና ስቃይ እየደረስብን ነው፡፡ሲሉ በእስር ቤቱ ከሚገኙ ኤርትራውያን መካከል አንዱ ለአልጀዚራ ተናግረዋል፡፡

ለመንቀሳቀስ የሚያስችል ክፍል የለንም፡፡  ሙሉ ቀን ምንም ነገር አናደርግም፡፡ እንዲሁም ብዙ አንናገርም፡፡  ሰዎች ይፀልያሉ፡  ይተኛሉ ፈዘው ይመለከታሉ፡ ይህ ብቻ ነው ያለው፡፡  አንዳንድ ሰዎች ምንም ባለማድረጋቸው ምክንያት ሃንክ ሆነዋል፡፡  ለመተኛት አይችሉም፡፡ ብቻቸውን መናገር ይጀምራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት አብደዋል፡፡ እጆቻቸውን  እግሮቻቸው ማሰር አለብን፡፡በማለት ሌላው ኤርትራዊ ሀሬፅ ለተባለ እስራኤል ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ /ቤት ቃል አቀባይ የሆኑት ሩፖርት ኮልቨል በሕገወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ወደ አውሮጳ እናሻግራቹሃለን፤ በሚል ምክንያት የጠፉት ወይም የተሸጡት ስደተኞች ጉዳይ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል፡፡ በሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ተይዘው የሚመለሱና ከዚያም ወደ እሱር ቤት የሚመለሱ ሰዎች ቁጥር ሰፊ ልዩነት አለው፡፡ በማለት ኮልቨል ተናግረዋል፡፡

የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በሕገወጥ ስደት መከላከያ ማእከል ክትትል ስር ውስጥ የሚገኘው የአልሐምስ አገልግሎት ሰጪ ማእከል በመቶ የሚገመቱ ሰዎች ማስረከቡን ዘግበዋል፡፡ ከነዚህም  200  በላይ ሰዎች በግንቦት 23 የተረከበ ቢሆንም በአሁኑ ግዜ 30 ስደተኞች ብቻ እንዳሉ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት 203 ሰዎች ወደ ማእከሉ ተወስደው እንደነበሩ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ   /ቤት ቃል አቀባይ ሩፖርት ኮልቪል ተናግረዋል፡፡

ሊብያ ባሉት ግጭቶች ምክንያት እርዳታ ተቋርጠዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ /ቤት 96 ስደተኞች ብቻ ከዚንታን እስር ቤት ለማስለቀቅ ችለዋል፡፡ ይሁን እንጂ እስከ አሁን ድረስ 3400 የሚሆኑ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች በትሪፖሊ ታስረው ይገኛሉ፤፤

TMP – 24/06/2019

ፎቶ: ቶምዌስትኮት/ ኢሪን

ኤርትራውያን ስደተኞች በሊብያ እስር ቤቶች ተይዘው ይገኛሉ