ጣልያን: ሊብያ በሚ ገኘው የስደተኞች ማጎርያ ጣብያ ውስጥ ስደተኞችን ደብድበዋል የተባሉት ሶስት ሰዎች ታሰራል
በሊበያ የስደተኞች ማጎርያ ጣብያ ውስጥ ስደተኖችን አስገድደው ደፍረዋል፣ ኢ–ሰብአዊ ድብደባ (ቶርች) ፈፅመዋል የተባሉ ሰስት ሰዎች፤ በጣልያን ፖሊስ ስር መዋላቸው ታውቀዋል፡፡ እነዚሁ አንድ ጊኒያዊና ሁለት ግብፃውያን በጣልያን ፖሊሶች ሲሲሌ ውስጥ ሊታሰሩ የቻሉት፤ወንጀሉን በፈፀሙት ወቅት የተመለከቱ ሌሎች ስደተኞች በሚሲና (ጣልያን) የስደተኞች መመዝገብያ ማእከል አግኝተዋቸው ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ ነው፡፡
ጥግተኛ ጠያቂ ስደተኞች፤ በአደገኛው የሊብያ ዛዊያ ማጎርያ ካምፕ ውስጥ ኢሰብአዊ ጥቃት ያደረሱባቸውን ሰዎች በቀጥታ መለየት ችለዋል፡፡የአይን እማኝነት የሰጡት ስደተኞቹ እንደተናገሩት፤ዛጉያ ማጎርያ ካምፕ ውስጥ፤ ገራፊዎቹ ከስደተኛ ቤተሰቦች ያስለቅቅያ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ፤ ኮንቴኖች እንደ ቤት ይጠቀሙ ነበር ብለዋል፡፡ እኒዚህ የታሰሩ ሶስት ሰዎች፤ ጥፋተኝነታቸው ከተረጋገጠ፤የ 6500 ዩሮ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ታውቀዋል፡፡
“ ገራፊዎቹ ወደ ቤተሰቦቻችን እንድነደውል ስልክ ይሰጡናል፡፡ ከዚያ እንዴት የተጠየቅነው ገንዘብ ከፍለው ማስለቀቅ እንደሚችሉ እናግዛቸዋለን” ብለዋል፡፡ አንድ ጥግተኛ ጠያቂ ስደተኛ ምስክርነቱ ለመንግስት ባለስልጣናት ሲሰጥ “ እኔ ታሰሬ እያለሁ፤ ሁለት ስደተኞች ለማምለጥ ሲሞኩሩ በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ አይቻለሁ” ብለዋል፡፡
ስደተኞቹ በዛዊያ ማጎርያ ካምፕ በነበሩበት ወቅት፤ ደረቅ ኮሮሾና የባህር ጨው ውሀ ብቻ ይቀርብላቸው ነበር፡፡ ከነሱ ጋር ማጎርያ ካምፕ ውስጥ የነበሩ ሁሉም ሴቶች ደግሞ፤“ በተለያየ ዘዴና በተደጋጋሚ ወሲባዊ ጥቃት ተፈፅምባቸዋል፡፡“
ከ2018 እ ኤ አ ጀምሮ አብዛኛዎቹ በሊብያ ማጎርያ ካምፕ ለቶርችና ስቃይ የተደረጉት ስደተኞች፤ በቅርብ ግዜ ወደ ጣልያን ሲሲሊ ገብተዋል፡፡
በወንጀለኝነት የታሰሩት ሶስቱ ሰዎች ደግሞ፤ ስደተኞች በመምሰል ሜዲተራንያንን አቃርጠው ሲሲሊ ገብተው የጥግተኝነት ጥያቄ ሲያቀርቡ ነው የተያዙት፡፡
የጣልያን ፖሊስ የጠየቃቸው ተጠቂ ስደተኞች እንደገለፁት ” በማጎርያ ካምፕ ውስጥ በብትር፣በሰድፍ፣ በፕላስቲክ ቆመጥና በኤሌክትሪክ ሾክ ተገርፈዋል” ያሉ ሲሆን፤ ግርፋቱ መቛቛም ያልቻሉ ሰዎቹም ሲሞቱ ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡ በግርፋት ብዛት ሰውነታቸው የቆሰሉና የታመሙ ሰዎችም ህክምና ተነፍጋቸው ለከባድ ስቃይ ተዳርገዋል፡፡
በዛውያ ማጎርያ ካምፕ የገራፊዎቹ አለቃ የሆነው ሊብያዊ ኦሳማ፤ ስደተኞቹ ለይተው አግኝተውታል፡፡ አንድ የአይን ምስክር እንደገለፀው “ ኦሳማ ሁሉ ግዜ ሁለት ጠመንጃ ይዞ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ እሱና አሽከሮቹ በጋራ ደግሞ፤ በርካታ ሴቶችን አስገድደው ይደፍሩ ነበር፡፡ “ ካሉ በሃላ “ በተለይም በኤሌክትሪክ ሾክ የሚያስገባቸው ሰዎች ህልናቸውን ስተው መሬት ላይ ይዘረገፉ ነበር “ ብለዋል፡፡ ሌላ የአይን እማኝ ደግሞ “ እኔ ራሴ በኤሌክትሪክ ሾክ አማካኝነት በርካቶች ሲገደሉ አይቻለሁ“ ብለዋል፡፡
ጉደዩን የያዘው ዋና አቃ ህግ ለሚድያ እንደገለፀው፤ “ በሊብያ ማጎርያ ካምፕ ተፈፅመዋል የተባሉት ኢሰብአዊ ግፎች ባደረግነው ምርመራ እውነትነታቸው ተረጋግጠዋል፡፡ ስለዚህ ለሰብአዊ መብት ጥበቃና ለወንጀለኞች ቅጣት፤ አለም አቀፍ ተግባራዊ ንቅናቄ ሊጀመር ይገባል “ ብለዋል፡፡ በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ሪፖርት መሰረት በአሁኑ ወቅት ከ 5000 በላይ ስደተኞች በሊብያ ማጎርያ ካምፖች በከፍተኛ ሰቆቃ ስር ይገኛሉ፡፡
TMP 02/10/2019
ፎቶ ከሬዲት፤– ሮበርት ፔልቶን / MOAS.eu
በአቡ ሳሊም ማጎርያ ካምፕ ውስጥ ሊብያ በእስር ላይ የምትገኝ ሴት
ፅሑፉን ያካፍሉ