ፈረንሳይ ተጨማሪ ጀልባዎች ወደ ሊብያ የጠረፍ ጥበቃ አካላት ልትልክ ነው

የፈረንሳይ የመከላከያ ሚኒስትር ፌቡራሪ 21 ላይ ያወጣው መግለጫ እንደምያሳየው ሀገሪቱ ሊብያ እያደረገችው ላለች ህገ ወጥ ስደትን የመግታት ጥረት ለመደገፍ ስድስት ጀልባዎች ልትሰጥ ነው።

ሚኒስትር መስርያቤቱ አውስት ፍራንስ ለተባለ የሚድያ አውታር በሰጠው መግለጫ እንዳወሳው ይህ ድጋፍ ፈረንሳይ ለሊብያ እያደረገችው የነበረች ድጋፍ ተጨማሪ ነው ብለዋል። ልክ እንደሌላ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት በዚህ ሁለት አመት ውስጥ  ፈረንሳይ ህገ ወጥ ስደትን በጥብቅ መከታተል  ጀምራለች።

የፈረንሳይ የመከላከያ ሀይል ሚኒስትር ፍሎሮንስ ፓርሊ ይሄንን ቃል የገቡት  ፌቡራሪ 21 ላይ በሊብያ ሚኒክ ከተማ ከሊብያው ጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሰራጅ ጋር ተገናኝተው ባካሄዱት የፀጥታና ድህንነት ኮንፈረንስ  ነው። የፈረንሳዩ የመከላከያ ሚኒስትር የሊብያ የባህር ጠረፍ አካላት ለማሰልጠን የምያስችል ፕሮግራም ለማዘጋጀት ፈቃደኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

12 ሜትር እርዝማኔ ያላቸው መለጠጥ የሚችሉ በፈረንሳዩ ሲሊንገር ቡድን የተሰሩ ጀልባዎች በፈረንሳይ መንግስት ተገዝተው ወደ ሊብያ እንደሚተላለፉ ተነግረዋል።  ይህ ድጋፍ በያዝነው የፈረንጆ አመት በሶስት ምዕራፎች ተከፋፍለው የሚሰጡ ይሆናሉ።

ጣልያንም ከሊብያ ጋር በወደብ አስተዳደር ዙርያ አብረው ለመስራት ያላት ዝግጁነት ገልፃለች። በመሆኑም የሮማው መንግስት አራት ፓትሮል ጀልባዎች ለመላክና የህይወት አድን ማእከል ለማቋቋም የምያስችላት ስራ ጀምራለች።

ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት LCG ን በማጠናክር ህገ ወጥ ስደተኞች አደገኛውን ሜዲትራንያን ባህር አቋርጠው እንዳይሄዱ ሲሰሩ ቆይተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊብያ ባለ ተልእኮ እንደገለፀው በመጀመርያዎቹ የ2018 ዘጠኝ ወራት ውስጥ  29,000 ስደተኞች እንዲመለሱ አድርጓል።

እንደ   UNHCR ገለፃ ደግሞ በ2019 የፈረንጆ አመት ውስጥ እስከ ፌቡራሪ 22 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ   LCG   779 ሰዎችን ከሊብያ ወደ ጣልያን ለመሄድ ሲሉ በቁጥጥር ስር አውለዋል።   ወደ አውሮፓ የሚሄዱ የጀልባዎች ቁጥጥር  2,640 ስደተኞችን ከተሰደዱበት ከባለፈው የፈረንጆች አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር መቀነሱን ታውቀዋል።

በቴሌቭዥን በተላለፈ የሊብያ የጠረፍ ጥበቃ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀነራል አዩብ ቃሲም የሊብያ መንግስት አቋም በገለፁበት ቃለመጠይቃቸው እንደገለፁት “በሊብያ በኩል በህገ ወጥ መንገድ በባህር ወደ አውሮፓ ለመሄድ የሚንቀሳቀሱ አካላት በወንጀል ይጠየቃሉ። ምክንያቱም ይህ ውሳኔ ለራሳቸው ህይወትም አስጊ ነው’። ይህ እንቅስቃሴ የሚመሩትም በህግ ፊት ቀርበው ይዳኛሉ።”  ብለዋል።

TMP – 9/3/2019

ፎቶ: ናቱርስፖርትስ/ሻተርስቶክ. በጣልያን የላምፑስዳ ወደብ አከባቢ የወዳደቀች ጀልባ ትታያለች።

ስለ ስደት ማወቅ የምትፈልጉት ማነኛውም አይነት ጥያቄ በኢመይል አድራሻችን ልታገኙን ትችላላችሁ።

ጥያቄዎቻችሁ በኢመይል አድራሻችን ላኩልን። ባልደረቦቻችን በፍጥነት ይመልሱላቹኋል። ሁሉም የኢመይል መልእክት
ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው።

ስደት አስበዋል? ለምክር አገልግሎት ይደውሉልን


ፈረንሳይ ውስጥ ከሆኑ

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ