ከ10 ሺ የሚበልጡ ተገን ጠያቂዎች ኤርትራውያን ድንበሮች ዳግም በመከፈታቸው ወደ ኢትዮጵያ መጓዛቸው ታወቀ
ከመስከረም መባቻ 2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ ጀምሮ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ተዘባተው የነበሩ ድንበሮች በመከፈታቸው ከ10 ሺ የሚበልጡ ተገን (ጥገኝነት) ጠያቂ ኤርትራውያን መግባታቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኤጀንሲ አስታወቀ በተጨማሪም ጥገኝነት ከመጠየቅ አልፈው ወደ ከቤተሰቦቻቸውና የስጋ ዘመደቻቸው ለሃያ ዓመት ተራርቀውና ተለያይተው የነበሩትም እየተቀላቀሉ መሆናቸውም ታወቋል፡፡
የሁለቱም ድንበሮች የተዘጋው እ.ኤ.አ በ1998 ዓ/ም በሁለቱም ሃሮግ በተፈጠረው አለመግባባትና ጦርነት ነው ፡፡በዛን ጊዜ ኤርትራውያን ተገን ጠያቂዎች ራሳቸው ወገኖችና ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችን ድንበር እንድያሻግራቸው ገንዘብ ይከፍሉ ነበር፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን የነፃ እንቅስቃሴውን በመጠቀም ከአገራቸው ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡና ጥገኝነት እየጠቁ ናቸው፡፡
ሃረጉ የተባለች ሴት እንደተገለፀችው “እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ወዳጆቼን ፣ ቤተሰቦቼንና ሌሎችን አቅፌ ሳምኳቸው ከደስታዬ ብዛት የተነሳ አለቀስኩኝ ደስታዬን በቃላት እጥረት ለመግለፅ አልችልም ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ፤ ከቤተሰቦቼም ጋር ጥሩ ጊዜ እያሳልፍኩ ነኝ ስትልም ከቤተሰቦችዋ ጋር ከተቀላቀለች በኋላ ትገልፃለች“፡፡
በስደተኞች መመዝገቢያ ማእከላት ሁሉም ስደተኞች እየተመዘገቡ አይደሉም ምክንያቱም ስማቸውን ካስመዘገቡ ወደ ሃገራቸው ሊመልስዋቸው እንደሚችሉ ሃሜት ስለሰሙ ነው ይህም ለዘጋርድያን ጋዜጣ ገልፀዋል በሁለቱም ሃገሮች የተደረጉት ስምምነቶች በግልፅ ለህዝብ ስላልተገለፁ ፍርሃትና ጥርጣሬ አላቸው፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገቡም አንድ ኤርትራዊ ዜጋ አስተማሪ እንደገለፀው “የኛ የስደተኝነት ሁኔታ ሊቀለበስ (ሊመክን) ስለሚችል ትልቅ ፍርሃት አለን (እንሰጋለን)“ ሲል ለዘጋርድያን ገልፀዋል፡፡ እነዚህ ሁለር ሃገራት ስለኛ ምን እንደተስማሙ የምናውቀው ነገር የለም ሲልም ይገልፃል፡፡
ድንበሩ ከመከፈቱ በፊት ወደ ኢትዮጵያ የገቡም በጣም ተጨንቀዋል ለአፍርቃ ሞኒተርስ ሲገልፁም ቀደም ሲል ወደ ኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የገቡትም የሁለቱም አገሮች ዝምድና ለነሱም ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ይሰጋሉ ፡፡ ይህንን በመፍራትም ወደ ኪንያ ወይም ኡጋንዳ በህገ–ወጥ መንገድ ለመጓዝም ያስባሉ ፤ ይህም ለህገ–ወጥ ደላሎችና አዘዋዋሪዎች ከ2000 (ሁለት ሺ ዶላር) በላይ ሊያስከፍላቸው ይችላል፡፡
እንደተባበሩት መንግሰታት የስደተኞች ከፍተኛ ከሚሽን ከሆነ ኢትዮጵያ ለስደተኞቹ ደህንነትና ጥበቃ አጥብቃ እንደምትሰራ ገልፀዋል፡፡ ጥገኝነት ጠያቂዎች በሚገቡበት ጊዜ በመመዝገቢያ ማእከልነት መመዝገብ አለባቸው ፤ ይህም ከመንግስት ከለለና ድጋፍ ከእርዳታ ድርጅቶች ኤንጅኦዎች ድጋፍና እርዳታ ለማግኘትና ያስችላቸዋል ሃገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስደተኞችን በመቀበልና በማስጠለል በአፍርቂ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፤ ይህም ወደ 932000 (ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሁለት ሺ) ስደተኞችን በማስጠለልና በመንከባከብ ማለት ነው ይህም 175 ሺ ከኤርትራ የመጡ ናቸው፡፡
TMP – 23/10/2018
ፎቶ፥ የኔርወይ እርዳታ ምክር ቤት። በእንዳባጉና የመቀበያና መመዝገቢያ ማእከል አዲስ ገቢዎች ለምዝገባ ሲጠባበቁ የሚያሳይ
ፅሑፉን ያካፍሉ