በሱዳን ሰማንያ አራት ኤርትራውያን ሰደተኞች ከህገ-ወጥ ደላሎችና አጋቾች (አፋኞች) እንደዳኑ ታወቀ

መስከረም 18/2018 / የሱዳን መንግስት ሃይሎች 84 ኤርትራውያን ስደተኞች ከሰላ አስተዳደር ውስጥ በህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ታፍነው የነበሩ ማስለቀቃቸው ሱና የተባለ የዜና ምንጭ ገልፀዋል::

የነፍስ ማዳኑ ስራ (ኦፕሬሽኑ) የተካሄደው በአከባቢ  ማህበረሰብ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰደተኞች በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ታፍነውና ታግተው መወሰዳቸው መረጃ ካገኙ በኋላና ቦታውም ከራይድሬር በተባለው ጫካ ውስጥና ሪፊ አረብ አከባቢ መሆኑን ከታወቀ በኋላ ነው፡፡

በከሰላ አስተዳደር የብሄራዊ ደህነትና የመረጃ አገልግሎት ሃላፊ አለም አልዲንሃሺም ተጎጂዎቹ (ታጋቾቹ) በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ላይ መገኘታቸው 51 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውና በአጋቾቻቸውም ብዙ ስቃይና እንግልት እንዳይደርስባቸው ገልፀዋል፡፡ ሃላፊው ጨምረው እንደገለፁት ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ታጋቾቹን ይዘውና አስረው 10 ቀናት እስከ ሁለት ወራት በእስረኛነት እንደቆዩ ይገልፃሉ፡፡

የነፍስ ማዳን ስራ ቡዱኑ 10 ህገወጥ  አዘዋዋሪዎችን እንዳሰረና በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ወደ አከባቢው ያለው የመንግስት የደህንነት ፍርድ ቤት ክስ እንደሚመሰረትባቸውም ገልፀዋል፡፡

ባለፈው መስከረም ወር 2011 / በኢትዮጵያና በኤርትራ የነበረው  የድንበር መከፈትና ነፃ መሆን ለኤርትራውያን ሃገራቸውን ጥለው  ወደ ኢትዮጵያ ሱዳንና ሊቢያ እንዲሁም ወደ ግብፅ በመሄድ አውሮጳ ለመድረስ ያላቸውን ተስፋ በመሰነቅ መሆኑ ታውቋል፡፡ የህገወጥ አዘዋዋሪዎች ትስስር በሰሜን ምስራቅ ሱዳን ይህንን የስደተኞች ፍልሰት እድል እንደሚጠቀሙበት ታውቋል፡፡

ሱዳን ለህገወጥ ሰደተኞች መነሻና መድረሻ እንዲሁም መተላለፍያ በመሆንዋ ይህንን ሁኔታ ለማሻሻል እርምጃዎችን በመወሰድ ላይ ትገኛለች። 2014 / .. ሃገሪቱ የፀረ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ህግ በማፅደቅና ሊያዘዋውሩ ለተገኙትም ጠበቅ ያለ ቅጣት እንደሚሰጠውና እንዲሁም ከሞት ቅጣት ጀምሮ 5 ዓመት ፅኑ እስራት እስከ 20 (ሃያ) ፃመት ፅኑ እሰራት እንደሚቀጡም ታውቋል፡፡  ካርቱም የድንበር ደህንነትን በሟቋቋም ከገረቤት ሃገሮች እንደነ ኢትዮጵያ ሊቢያ ቻድ ኒጀር  የመሳሰሉትም አብራ እንደምትሰራ ታውቋል፡፡

TMP – 2/12/2018

ፎቶ:- ስትሪት ፎር/ ሻተርስቶክ።  በከሰላ የአውቶቢስ ማረፍያ  ሱዳን።