ሱዳን፡ ከሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ነፃ የወጡት ሕፃናት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገናኙ

ሕፃናት በምሥራቅ ሱዳን ከሚገኘው ካምፕ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ፡፡ ፎቶው፡ ሳሊ ሃይደን/ ዘ ኣይሪሽ ታይምስ

የሰዎች አዘዋዋሪዎችን የሚዋጋ (NCCHT) የሱዳን ብሔራዊ ኮሚቴ በ27 ሓምሌ እንደ አ.አቆ እንዳለው  ከሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ነፃ የወጡት 80 ሕፃናት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ማገናኘቱን ገልፆአል፡፡ በኮሚቴው ሊቀ መንበር በኢስማኢል ቲራብ የወጣው መግለጫ፣ በሰዎች አዘዋዋሪዎች የተጠቁ ሰዎች በስደተኞች ካምፕና በሌሎች የመኖርያ ቦታዎች ላይ ለቤተሰቦቻቸው ማስረከባቸው ያሳያል፡፡ ቲራፕ ንግግሩን በመቀጠል የእነዚህ የተጠቂዎች ጠላፊዎች በፍርድ ላይ መሆናቸው በማመልከት፣ በእርሱ የሚመራው ኮሚቴ ከብሔራዊው የሕፃናት ደኅንነት ምክር ቤት በመተባበር የተቀሩት ተጠቂዎች ቤተሰብ በማፈላለግ ላይ ያለ መሆኑን ገልፆአል፡፡

ዕድሜያቸው በ13 እና 17 መካከል የሆኑት ተጠቂዎች በ24 ሓምሌ እ.ኣ.ኣቆ በካርቱም በሻርጀል ናይል አካባቢ በተደረገው የፖሊስ እንቅስቃሴ ከብረት በተሠራው የዕቃ ማስቀመጫ ታጭቀው ነበር የተገኙት፡፡ ወጣት ተጠቂዎቹ ወደ ሌሎች አዘዋዋሪዎች ለመተላለፍ የተዘጋጁ ነበሩ፡፡

የአገሩ ከፍተኛ የዓቃቤ ሕግ የደኅንነት ፅ/ቤት ምክትል ፀሓፊ፣ ሙታዚም ዓብደላሕ ተጠቂዎቹ ከብረት በተሠራው የዕቃ ማስቀመጫ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ክፉኛ መደብደባቸውና በዚሁ ምክንያትም የአካልና የአእምሮ መዛባት እንደደረሰባቸው ለሬድዮ ዳባንጋ ተናግሮአል፡፡

ሕጋዊ አሀዝ እንደሚያሳየው፣ በታሕሣሥ 2017 እና በመጀመርያው ሓምሌ 2018 መካከል የሱዳን ባለሥልጣናት በምሥራቃዊ ካርቱም፣ ከሰላና ገዳርፍ አስተዳደር በጠቅላላ 642 የሰው ሕገወጥ ዝውውር ተጠቂዎችን ነፃ አውጥተዋል፡፡

ለሕገ – ወጥ ስደትና ሰዎችን የማስተላለፍ ሥራ ጀማሪ የሆነው የሱዳን መንግሥት፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ይህንኑ ያልተለመደ የሰዎችን ዝውውር ድርጊት ለመዋጋት ችግሩን ለመፍታትና እርምጃን ለመውሰድ ኃይለኛና ጥብቅ የሆነ ሕግ በማውጣት ላይ ትገኛለች፡፡ ከሚወሰዱት አዳዲስ እርምጃዎች ጥቂቶቹ በአዘዋዋሪዎች ላይ ጥብቅ የሆነ ቅጣት፣ ማለት በሞት እስከ 5 እስከ 20 ዓመት እስራት መቅጣትን ያጠቃልላል፡፡

በሌላ በኩልም ከብዙ የአውሮፓ አገሮችና የአውሮፓ ሕብረት ጋር አብረው የሚሠሩ ድርጅቶችን በማቋቋም ረገድ ሙከራዎች ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም መንግሥት ሰዎች አዘዋዋሪዎች የሚጠቀሙባቸው የመሸጋገርያ ኬላዎችና የማስተላለፊያ እምብርቶች ላይ በጣም የጠበቀ የደህንነት ጥበቃ አድርጓል፡፡ እነዚህ ሰዎችን በማስተላፍ ረገድ የፖለቲካ ትኩሳት ያለባቸው ቦታዎች ከኤርትራ ጋር የሚያዋስነው የሱዳን ምሥራቃዊ ጠረፍ፣ ከኢትዮጵያና ከሊቢያ የሚያዋስኑት ጠረፎች ናቸው፡፡      

ሱዳን፣ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ድጋፍ በ2018 እና በ2019 የሰዎች ሕገ-ወጥ ዝውውርን ለመዋጋት ብሔራዊ ፕላን አውጥታለች፡፡

በቅርቡ የወጣው በሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR ሪፖርት፣ አገሪቷ ከዓለም እጅግ ከፍተኛ ስደተኞችን በማስተናገድ ስምንተኛ አገር መሆኗን ያሳያል፡፡ በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ 906,000 ስደተኞች መኖራቸው ሪፖርቱ ይገልፃል፡፡  

TMP – 13/08/2018