ኢትዮጵያና ሱዳን በሁለቱም የጋራ ድንበሮች ላይ ሕገ-ወጥ ስደትንና ሽብርተኝነትን የሚዋጋ ኃይል ሊያሰማሩ ነው፡፡
ኢትዮጵያና ሱዳን በሁለቱም የጋራ ድንበሮች ላይ የሰዎች ዝውውርና ሽብርተኝነትን የሚዋጋ የጋራ ወታደራዊ ኃይል ለማሰማራት ተስማሙ፡፡ በተጨማሪ ሁለቱም ወገኖች ሽብርተኝነትን፣ ሕገ- ወጥ ስደትንና የሰዎች ዝውውርን ለመዋጋት ትብብራቸውን በማጠናከር የማስተባበሩ ሥራ coordination ከፍ እንደሚያደርጉ ተስማምተዋል፡፡
ይህንኑ በክልሉ ከታዩት የተደባለቀ ስደት፣ የስደተኞች ፍልሰትና ጠረፍ በማቋረጥ የሚከሰቱ ወንጀሎችን መፍትሔ በመስጠት ረገድ ከተሠሩት በርካታ የማደራጀት ተግባር አንዱ ነው፡፡
በሁለቱም የሱዳንና ኢትዮጵያ የጋራ ወታደራዊ ኮሚሽን በካርቱም ባደረጉት ስብሰባ በወጣው መግለጫ መሰረት፣ ሁለቱም አገሮች ወታደሮቻቸውን ከጠረፉ በማስወጣት ከሚቀጥለው ታሕሣሥ ወር በፊት ከሁለቱም በተውጣጡ ኃይሎች ተክተው እንደሚወጡ አስታወቀዋል፡፡
የሱዳኑ የጦር ኃይሎች ቺፍ ኦፍ ስታፍ ጄነራል ካማል ዓብደል ማዕሩፍ “በሁለቱም አገሮች ያለው ዝምድና ዘልዓለማዊ ነው፣ በጦሩ መካከል ያለው ዝምድናም ታሪካዊ ነው” ካሉ በኋላ በተጨማሪም በሁለቱም የጋራ ጠረፎች ያለው ውጥረት ለማርገብ ሁለቱም ወገኖች በከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
በመቀጠልም የጋራ ኃይሉ ሽበርተኝነትን በመዋጋት፣ ተቃዋሚ ቡድኖች ጠረፍ ከመሻገር በመከላከልና ሕገ-ወጥ ስደትንና ሰዎችን ዝውውር በማክሸፍ ተግባር ላይ ይሠማራሉ ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኃይሎች ቺፍ ኦፍ ስታፍ፣ ጀነራል ሰዓረ መኮነንም የተደረገው ስምምነት፣ ሁለቱ አገሮች የፀጥታ ስጋትንና በጠረፍ አካባቢ የሚደረጉ ወንጀሎችን በአንድነት ለመዋጋት ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡
“በተጨማሪም እነዚህ ወታደሮች የጠረፍ ፀጥታን በመደገፍና ጠቅላላው ክልሉን ለማረጋጋት ይረዳሉ” ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ሱዳንም ከሌሎች ጎረቤት አገሮች ፀጥታን የማደራጀት ሥራ ትሠራለች፡፡ ባለፈው ሕዳር ወር የሱዳን መንግሥት የጋራ ጠረፎችን እየተዘዋወሩ በሚጠብቁ የጋራ ጠባቂዎች አሠማርቶ ለመጠበቅና ለመቆጣጠር፣ እንደዚሁም መረጃ ለመለዋወጥ፣ ለተልእኮው የሚያስፈልግ ማእከል ለማቋቋምና በጋራ ጠረፎቹ የልማት ፕሮጄክቶችን ለማካሄድ የስምምነት ውል ከሊቢያ፣ ከቻድና ከኒጀር ጋር በኤንጃሚና የስምምነት ውል framework agreement ተፈራርመዋል፡፡
TMP – 09/09/2018
መግለጫ፡ የኢትዮጵያና ሱዳን የተጣመረ ሰንደቅ ዓላማ ስፒሎች፡፡ ፎቶ፡ www.crossed-flag-pins.com
ፅሑፉን ያካፍሉ