በሞሮኮ ወደብ አከባቢ በደረሰው የጀልባ መገልበጥ አደጋ የብዙዎች ህይወት አለፈ
የሞሮኮ የባህር ሀይል እንደገለፀው ቢያንስ 45 ስደተኞች በሞሮኮ በኩል ወደ ስፔን ለማለፍ ፈልገው እየተንቀሳቀሱ በነበሩበት ወቅት በአጋጠመ አደጋ ህይወታቸው አልፈዋል። እነዚህ ህፃናት እና እርጉዝ እናቶች እንደሚገኙባቸው የነተገረላቸው የአደጋው ሰለባዎች፡ ሁሉም ከአፍሪካ ሀገራት የመጡ መሆናቸው ተገልፀዋል።
የ የሞሮኮ የባህር ሀይል ማርች 14 ቀን 2019 እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር 13 ሴቶች የሚገኙባቸው 21 ስደተኞች በከፍተኛ የህይወት ሽረት ውስጥ ያገኘ ሲሆን የአንድ ሰው አስከሬንም አግኘተዋል። ይህ 67 ሰዎች ጭኖ ሲሄድ የነበረ ጀልባ በባህር ጠባቂዎች ከባህሩ ለመውጣት ችለዋል።
የባህሩ ጠባቂዎች ጀልባው ከመገልበጡ ሁለት ሰዓት ቀድመው ከተጓዦቹ ጋር ኮሙኒኬሽን እንደነበራቸው ገልፀዋል። ለትርፍ ያልተቋቋመ በስደትና ስደተኞች ዙርያ የሚሰራ ተቋም እንደገለፀው አደጋው የተከሰተው በሞሮኮ እና ስፔን መካከል ባለው የባህር አካል ነው።
ይህ ሞሮኮ ላይ ማእከሉ ያደረገ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም የሚመሩ ሄለና ማሊኖ ማርች 13 ቀን 2019 ላይ ወደ ስደት እየሄዱ ከነበሩ ቤተሰብ ከሆኑ አካላት ዘንድ ኮሙኒኬሽን እንደነበራቸው ገልፀዋል። ይሁንና እሳቸው ያገኙት ሰው ከትንሽዋ ጀልባ ጋር የነበረ እና ከቀኑ 9፡45 አከባቢ ላይ እንደነበር ተናግረዋል።
ስደተኞቹ ለማሊኖ እንደገለፁላቸው ከሆነ ጀልባአቸው ሚዛኑ ጠብቆ አልሄድ ብለዋቸው ነበር። ከሁለት ሰዓታት በኋላም ደውሎ ስያናግራቸው የነበረ ስደተኛ “በቃ እየሰመጥን ነው። ጀልባው ውሃ ገብቶበታል።” እንዳላቸው ገልፀዋል።
“ሌላ በግምት ከ12 እስከ 14 ዕድሜ የሚሆናት ልጅም እዛ ነበረች፤ ሳትድን ቀረች።” ብለዋል ማሊኖ።
ሞሮኮ በርከት ያሉ ስደተኞች የሚተላለፉባት በር ሆና የምታገለግል ሀገር ነች። ይህ የሆነበት ምክንያትም ሊብያ ስደተኞች ወደ አውሮፓ እንዳይሄዱ ስለምትከለክል እና ጣልያን ደግሞ ስደተኞች ጭነው በባህር ለሚያቋርጡ ጀልባዎችና መርከቦች በሮችዋ ስለዘጋች ነው ተብለዋል።
በ 2018 ሞሮኮ 89 ሺ ሰዎች እንዳስቆመች መዘገብዋ የሚታወስ ሲሆን ይህ ቁጥር በባህር ላይ አደጋ ከሚደርስባቸው ሰዎች አንድ ሶስተኛ ድርሻ ብቻ እንደሆነ ተገልፀዋል። ወደ 80% የሚጠጉ በሞሮኮ የታገቱ ስደተኞች የውጭ ሀገር ዜጎች መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል። የሀገሪቱ መንግስት 229 የህገ ወጥ የሰው ልጅ ንግድ ኔትወርኮች እና መረቦች መበጣጠስ እንደቻለ ገልፀዋል።
በ2018 የአውሮፓ ምድር ከረገጡ 112,000 ስደተኞች ግማሽ የምያክሉ ከሰሜናዊ አፍሪካ ክፍል ሜዲትራንያን ባህር በማቋረጥ አውሮፓ የደረሱ ናቸው።
TMP – 25/03/2019
ፎቶ: ሶንያ ቦኔት/ሻተርስቶክ. አደጋ የደረሰበትን ጀልባ በሳንታ ፖላ፣ አሊቻነቴ ስፔን ወድቆ ይታያል።
ፅሑፉን ያካፍሉ