በሞሮኮ-ስፔን መስመር የስደተኞችን ሞት መጨመሩ ተነገረ

የደቡባዊ አውሮፓ ሃገራት ስደተኞች የሚያልፉባቸው የጠረፍ መንገዶች በአግባቡ ማስተዳደር ባለመቻላቸው ምክንያት ብዙ ስደተኞች አደገኛው የመንገድ ምርጫ ተከትለው መሄድ ቀጥለዋል።  

የአውሮፓ ህብረት እና አባል ሃገራቱ ባህር ተሻግረው የአውሮፓ ምድር የሚረግጡ ስደተኞች ለመቀነስ ባደረጉት ርብርብ አጠቃላይ የቁጥር ቅነሳ ታይተዋል። ይሄውም በዚህ አመት ብቻ  108,000 የተመለሱ ሲሆን ይህ ቁጥር ባለፈው አመት ከነበረ   159,996 እንዲሁም በ2016 ከነበረው  348,591 የስደተኞች ብዛት በታች ሆነዋል።  ይህ ከ2016 ጀምሮ እየታየ ያለ የስደተኞች ቅነሳ የምያስደስት ቢሆንም  አሁንም አደገኛው የባህር ላይ ጉዞ ለማድረግ በ2018 ብቻ ቢያንስ 2,133 የምያህሉ ስደተኞች ህይወታቸው አጥተዋል

ከሞሮኮ ወደ  ስፔን , ባለ አደገኛ መስመር ላይ አሁን አሁን ዋናው የስደተኞች መስመር ሆነዋል። ይህ የሆነው በተለይ ጣልያን በማእከላዊ የሜዲትራንያን ባህር ላይ የነበረ መስመር በመዝጋትዋ ምክንያት ነው። በዚሁ ምክንያት በ2018 ብቻ  ከ680 በላይ ሰዎች ሞተዋል አልያም የገቡበት አይታወቅም። ይህ ቁጥር በ2017 ከነበረው ተመሳሳይ አደጋ ሶስት ዕጥፍ ነው።   

ይህ ጊዜ በቁጠር ቅነሳ የሚታይበት ነው። ይሁንና ስፔን ላይ ግን አይሰራም” ብለዋል የአይኦኤም ቃል አቀባዩ ጆል ሚልማን ኖቨምበር 23 ላይ  በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ።  

ሚልማን ጨምረው እንደገለፁት ስደተኞች በአሁን ሰዓት ከማነኛውም ጊዜ በበለጠ አደገኛው የባህር ጉዞ የሚመርጡበት ሁኔታ ነው ያለው። እንደ ቃል አቀባዩ አባባል ባለፈው ወር ብቻ 24 የምያክሉ ስደተኞች በስፔኑ ካዲዝ ፖርት አከባቢ ውሃ በልተዋቸው ቀርተዋል።   

የቅርቡ ዜና የምያመለክተው ደግሞ ከአፍሪካ ቅናት የመጡ ስደተኞችን ጭና በመጓዝ ላይ የነበረች አንድ ጀልባ ከሞሮኮ ተነስታ ወደ ስፔን እየተጓዘች በነበረችበት ወቅት እንጅንዋ ቆሞ በባህሩ ላይ አራት ቀናት ቆይታለች።  

የሞሮኮ የባህር ሃይል ኖቨምበር 24 ላይ 15 የሰው አስከሬን አግኝቻለሁ ብለዋል፤ እንደ ኤኤፍፒ ገለፃ። በዚሁ ኦፕሬሽን ሌሎች 53 በህይወት ተገኝተው በባህር ጠረፉ ወደምትገኝ ናዶር የምትባል የሞሮኮ ከተማ ተወስደዋል።   

ስደተኞች የአውሮፓን ምድር ለመድረስ  በጣም ፈታኝ እየሆነ ባለበት በዚህ ወቅት  እንዲሁም የስደተኞች ቁጥር በአማካይ እየቀነሰ ባለበት ሰዓት ጣልያን የመሳሰሉ ሃገራት  ግን በህገ ወጥ ስደት ያላቸው ጠንካራ አቋም ቀጥለውበታል።   

በቅርቡ የሲስልያን ተሟጓች በመዲሰንሳን ፍሮንቲዪር እና ኤስኦኤስ ሚዲትራኒ የተባሉ የባህር ጥበቃ ተቋሟት የሚደርሱ ጥቃቶችን እንዲቆም መጠየቁ ተገልፀዋል።  እነዚህ ተቋማት የተከሰሱት  በግማሽ አመት ውስጥ ብቻ 24 ቶን የሚመዝን አደገኛ ቆሻሻ በ11 የጣልያን ወደቦች በመድፋታቸው ነው።   

የኤምኤስኤፍ መሪ የሆነው ካርሊን ከሌጂር ለሁለት አመታት ያክል ከህገ ወጥ የሰው ንግድ አከላት ግኑኝነት አላችሁ ከሚል  የሀሰት ክስ ጀምሮ ከምርመራ አካላት ግኑኝነት አላችሁ የሚል የተዛባ ገምጋም   በኋላ አሁንም ጥላሸት መቀባቱ ቀጥለዋል። የሰብአዊ ስራዎቻችን እንዳንሰራ ዕንቅፋት እየሆንብን ናቸው። በተደራጀ የወንጀል ስራ እየተከሰስን ነው ያለነው።” ብለዋል።  

ቢቢሲ እንደዘገበው የደህንነት ጀልባዋ በማርሲ-ፈረንሳይ ለወራት ያህል ጊዜ እንድትቆይ ከተደረገ በኋላ ከጣልያን በተደረገባት ጫና ምክንያት ፓናማ ባለቤትነቱ ወስዳለች።   

በቅርቡ የጣልያን ፓርላማ ህገ ወጥ ስደትን  በተመለከተ አዲስ ህግ እንደምያፀድቅ እየተነገረ ነው። ህጉ በሂማኒተርያን ስራ ላይ የሚንቀሳቀሱ ተቋማትን የሚፈትሽ እና ህገ ወጥ ስደተኞችን የሚከለክል ይሆናል። ይሁንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለሙያዎች እየረቀቀ ያለው ህግ ተቋውሞውታል።  

ፎቶ: ግብላተር ስትራይት /ስደተኞች በሞተር ጀልባ ላይ ሆነው ይታያሉ

TMP – 19/11/2018