የሞሮኮ ባህር ሃይል የስደተኞች ጀልባ ተኩሶ አንድ ልጅ አቆሰለ

ኦክተበር 10/2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ  የሞሮኮ የባህር ሃይል ስደተኞችን ጭና ከሰሜን አፍሪቃ ሃገር ወደ ስፔን ስተጓዝ ወደ ነበረች አንድ ጀልባ ተኩሶ አንድ የ16 ዓመት ልጅ ማቁሰሉ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስን በመጥቀስ ኤ.ኤፍ.ፒ የወታደራዊ ምንጭ አስታወቀ።

በደረቱ ላይ በጥይት የተመታው ልጅ ታንጀርስ ወደ ተባለው ሆስፒታል መወሰዱና ጉዳቱም መጠነኛ መሆኑ ታውቋል። የወታደራዊ ምንም እንደገለፀው ከሆነ የማስጠንቀቅያ ተኩስ ቢያሰሙም ተጠርጣሪው የሞተር ጀልባ 58 ስደተኞችን አሳፍሮ ሲሄድ የባህር ሃይል ቡዱኖች ድህንነት ላይ አደጋ በመደቀኑ የባህር ሃይል አባላት እንዲተኩሱ እንዳስገደዳቸውና ጀልባዋም እንዳትንቀሳቀስ ለማድረግ መሆኑ ታውቃል።

በሁለት ሳምንታት ውስጥ ይህ ተኩስ ለሁለተኛ ጊዜ እንዳጋጠመ ታውቃል። መስከረም 25 የባህር ሃይል ኣባሎች በተኮሱት ጥይት የ22 ዓመት ሴት ልጅ እንደተገደለችና ሌሎች ሶስት ሰዎችም እንደቆሰሉ ፣ ይህም ከጀልባው ለተደቀነባቸው አደጋ ግብረ መልስ ለመስጠት ሲሉ እንዳደረጉት ታውቃል። የሃገሪቱ የባህር ሃይል ኣባላት ጀልባዋ ላይ የተሳፈሩት ስደተኞች በሙሉ ወደ ሞሮኮ እንደመለሱዋቸው ገልፀዋል ።

በ2017 ዓ/ም እ.ኤ.አ ከሞሮኮ ወደ ስፐይን ለሚደረገው የስደት ጉዞ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱና ወደ አውሮፓ ለመጓዝም ተመራጭ እየሆነ መሆኑ ታውቃል። ይህም የሆነበት ምክንያት በሊቢያ ያለው የታጣቂዎች ቡዱኖች ዋና ከተማዋ የትሪፖሊን ለመቆጣጠር የሚያደርጉት የርስ በርስ ጦርነት መሆኑ ይገለፃል በጣም ብዙ ህገ-ወጥ ስደተኞች በህጋዊ መንገድ ሞሮኮን ለመጎብኘት ያለቪዛ ወደ ሃገሪቱ እንደሚገቡና በቀን ሰራተኝነትና በግብርና ስራ ላይ ተሰማርተው ወደ ሜዲተራንያን ባህር ለመሻገር መክፈያ ገንዘብ ለመጠቀም መሆኑም ጨምረው ገልፀዋል።

ነገር ግን የሞሮኮ ወደታደራዊ ሃይል በሜዲተራንያን ባህር ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ታውቃል። በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር በ10 ቀናት ውስጥ ብቻ 32 ጀምልባዎችን 675 ህገ-ወጥ ስደተኞችን እንደጫኑ እንደተያዙና  ታውቋል። በጥር ወር እና ነሓሴ መካከል ባሉት ጊዚያት ሞሮኮ 54000 (አምስ አራት ሺ) ህገ-ወጥ ስደተኞች ወደ አውሮፓ መዳረሻ ባህር ወደብ እንዲያዙና ይህም የ15% በመቶ ካለፈው ዓመት 2017 ዓ/ም ሲነፃፀር ጭማሪ ማሳየቱ ታውቋል።

በየብስ ላይም በሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር የሞሮኮ ፖሊስ ወደ አውሮጳ ለመሻገር ስደተኞች ያዘወትሩበታል በተባሉ ቦታዎች መደበኛ አሰሳና ቁጥጥር (ፍተሻ) እንደሚያደርጉ ታውቋል። በዚሁ ቁጥጥር የሚያዙት ህገ-ወጥ ስደተኞች ወደ ሃገሪቱ ደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል እንደሚላኩና ወደ ሰሜን ኣቅጣጫ እንደሚጓዙ ታውቋል።  

የሞሮኮ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጥር ወር 2018 ዓ/ም ጀምሮ  የህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች መረብ (ኔትወርክ) እንደተበጣጠሰ ለሮይተርስ ገልጸዋል። ሃገሪቱ በየዓመቱ ወደ 200 ሚልዮን ገደማ እንደምታጣና ድንበሯን እንደምትጠብቅ ታውቋል።

ወደ ስፔይን የሚያደርሱ ስደተኞች ብዙ መሰናክሎች (ችግሮች) እንደሚያጋጥማቸው ሲታወቅ በስደተኞች ማቆያ ማእከላትም መጥፎ ሁኔታ ላይ እንደሚቆዩና የጥገኝነት ጥያቄአቸውንም ኣቅርበው መልስ እስከ ሚያገኙ ለብዙ ጊዜ እንደሚጠባበቁ ታውቋል።

TMP – 17/10/2018

ፎቶ:ሞሮኮ ዎርልድ ነውስ። የሞሮኮ ባህር ሃይል በጀልባ ላይ ሆነው ሲቆጣጠሩ።