ጀርመን ስደተኞችን መመለስ ልታፋጥን ነው፡፡
በጀርመን ውስጥ ያሉ የፖሊስ መኮንኖች የ23 አመቱን ቶጎዋዊ ስደተኛ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ለማድረግ ከስደተኛ ቡድኖች ጋር ለ3 ቀን ከተደረገ ግጭት በኃላ በደብቡ ፣ ኢልዋንገን ከተማ ውስጥ ያለን የስደተኞች መጠለያ በግንቦት 3 ከበዋል፡፡
ይህ አዲሱ ኦፕሬሽን በቅርቡ በጀርመን የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆረስት ሲ. ሆፈር ‹‹የስደተኝነት ማስተር ፕላን›› በሚል ቀርቧል፡፡
ሲ ሆፈር ህገ ወጥ ስደተኝነትን ለመግታት ከፍተኛ እርምጃ እንደሚወስዱ፣ የጥገኝነትን ሂደት እንደሚያፋጥኑ እና ውድቅ የተደረጉ ስደተኝነት ጠያቂዎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማፋጠን ቃል ገብተዋል፡፡
አሾሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ሲሆፈር ኢልዋንገን በርሊን ለሚገኙ ሪፖርተሮች እንደገለጹት ‹‹በኢልዋንገን የተፈጠረው ህግን የሚያከብሩ ሰዎችን በጥፊ መምታት ነው፡፡››
‹‹የእንግዳ ተቀባይነት መብት በዚህ መልኩ መረገጥ የለበትም›› ሲሉ ሲሆፈር አክለው ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ሲገልጹ ‹‹የደህንነት ባለሥልጣናት ያላቸውን ሁሉ ሀይል እና ቁርጠኝነት በመጠቀም›› ወደ ሀገር መመለስ ስራዎች የሚያከናውኑ ፖሊሶችን የሚቃወሙ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞችን መመለስ አለባቸው፡፡
እንደ ጀርመን ፖሊስ ከሆነ ውድቅ የተደረጉ ጥገኝነት ጠያቂዎች ለመውሰድ ሲመጡ ከሚያጋጥማቸው ሁኔታ አንጻር ትልቅ ደረጃ ያለው ኦፕሬሽን አስፈላጊ ነው፡፡
ኢንዋንጌን አቅርቢያ ያለ አሌን ከተማ ምክትል የፖሊስ ኃላፊ የሆኑት በርናንድ ዌበር ለሪፖርተር እንደገለጹት ‹‹ከ150-200 የሚደርሱ አፍሪካውያን ስደተኞች በከፍተኛ ብጥብጥ ይህን ከመፈጸም ሲከላከሉ ነበር፡፡››
እንደ ዌበር ገለጻ ግለሰቡን ወደ ጀርመን ለመምጣት ወደላፈባት ሀገር ጣሊያን እንዲሄድ ለማድረግ ውሳኔ ተላልፎዋል፡፡
እንደ አውሮፖ ህብረት ‹‹የደብሊን ህግጋት›› ስደተኞች መጀመሪያ በገቡበት አባል አገር ጥገኝነት ማመልከት አለባቸው፡፡
እንደ አዲስ የስደተኝነት እቅድ አካል፣ ጀርመን ጥገኝነት ጠያቂዎችን በማዕከላዊ የጥገኞች ማዕከላት ማቆየት ትፈልጋለች፤ እዛ ከሌሎች 1,500 ስደተኞች ጋር ለ2 አመት ያህል የሚቆዩ ይሆናል፡፡
ስደተኞቹ የጥገኝነት ማመልካቸው እስኪጸድቅ በመላ ሀገሪቱ አይበተኑም፡፡
ዳኛዎች በጥገኞች ማዕከላት የሚሰሩ ሲሆን፤ ማመልከቻቸው ያልጸደቀላቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች በቀጥታ ከማዕከሉ ወደ ሀገራቸው ወይም ወደ ገቡበት ሀገር እንዲመለሱ ይደረጋሉ፡፡
ሲሆፈር ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ስደተኞች እንደይሸሱ ማቆያ ቦታዎችን መጨመር ይሻሉ፡፡
TMP – 29/05/2018
ፅሑፉን ያካፍሉ