የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህፃናት መብት በካሌ በየቀኑ እየተሰጠ መሆኑ እየተጣሰ መሆኑ የእርዳታ ድርጅት ቡዱን ገለፀ

ፎቶ ዶች ቬለ 250 ህፃናት በአስቸጋሪና ብርዳም ወቅት በፈረንሳይ ሰሜናዊው ዳርጃ

ሲዲኬ (ትክክለኛ ስሙ አይደለም) የ14 ዓመት አፍጋኒስታዊ ስደተኛ ሲሆን በሰሜናዊ ፈረንሳይ የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ የሚኖር ነው። ከሌሎች 250 የሚጠጉ ወላጅ (አሳዳጊ) የሌላቸው ህፃናት ጋር በጎደና ላይ ያለ ምንም ምግብ፣ ውሃና መጠለያ ይኖራል።

ከዶችቬለ ( የጀርመን ድምፅ ሬድዮ) የዜና ወኪል ባደረገው ቃለ ምልልስ ሲዲኬ ከሁለት ዓመት በፊት በታሊባን ታጣቂዎች አባቱና ወንድሙ ከተገደሉበት በኃላ ከምስራቃዊ አፍጋኒስታን ናንጋርሃር ከተባለው ክፍለ ሃገር እንደወጣ ይገልፃል። አስቸጋሪውን ጉዞና መከራ በኢራን ፣ ቱርክ ፣ የባልካን አገሮችና ጀርመንን ተሻግሮ ነው ፈረንሳይ ሃገር የደረሰው።

አሁን እሱና ሌሎች አራት አፍጋኒስታናውያን ስደተኛ ህፃናት ጋር አንድ ቡዱን መስርተው እሱ ባምቢኖስ ብሎ የሚጠራቸው ምንም ዓይነት ገንዘብ ሳይኖራቸው እነዚህ ህፃናት በእርዳታ ድርጅቶች እገዛ የምግብ ፣ ብርድ ልብስ ፣ ልብስ ፣ ድንኳንና የምግብ ማብስያ እንጨት እየተረዱ እሱን ተማምነው ይኖራሉ።

የፈረንሳይ መንግስት በካሌ መጠለያ አባወራ የሌላቸው ህፃናት የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያ የመስጠት ግዴታ አለበት። ይሁን እንጂ እንደ የወጣት ተገን ጠያቂዎች አገልግሎት (አር.ዋይ.ኤስ) ተጨማሪ አልጋዎች ለመስጠት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው የሌለው ይላል።

“የወጣት ተገን ጠያቂዎች አገልግሎት እንደሚለው ከሆነ 580 አባወራ የሌላቸው ህፃናት በ2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ በካሌ መሰረታዊ ነገሮች እንዲቀርብላቸው ጥያቄ አቅርበዋል። ነገር ግን የአከባቢው ባለስልጣናት 270 የሚሆኑት አንድ የአካል ጉዳተኛ ጨምሮ ማመልከቻዎች ውድቅ አድርገዋቻዋል። “

ህፃናት ካሌ ሲደርሱ አያሌ ችግሮችን አልፈው ነው። ሲል ጀረሚ ሮቻስ የቀድሞ የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኛ የነበረ ለዶች ቬለ ተናግራል። አብዛኛዎቹ ስደተኞ ህፃናት የተለያዩ ስቃይና እንግልት እንዲሁም ሰቆቃ ቀምሰው ነው እዛ የደረሱት። በተለይም በሊቢያ በኩል አድርገው ከመጡ ፤ እዚህ ካሌ ከደረሱ በሃላም አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ያጋጥማቸዋል ፣ የወደፊት ተስፋቸውም ይጨልማል። ይህም ለተስፋ መቁረጥ ይደርጋቸዋል።

“ተገን ጠያቂዎች እርዱ የተባለ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን የሚመዘገብ እንደገለፀው ከሆነ መዝገቦች እንደሚያመለክቱት ፖሊሶች ስደተኞችን አከላውና ስነ-አእምሮዊ ጉዳት ያደርሱባቸዋል። 244 የሚሆኑ ጉዳዮችን ሲታዩ መጠሊያዎችን (ድንኳኖችን) ማፈራረስ ፣ ንብረቶችን መውረስ (መዝረፍ) ፣ ድብደባና በፖሊሶች ውሾች እንደሚነከሱ ነው የሚገልፁት። ዩቶፕያ 56 የተባሉት የእርዳታ ቡዱኖቹ እንደሚሉት ከሆነ 10 ህፃናት የህክምና እርዳታ እንደጠየቁና ይህም ከሰኔ እስከ ታህሳስ 2018 ዓ/ም ባለው ጊዜ በፖሊስ ድብደባ በደረሰባቸው ጉዳት መሆኑ ገልፀዋል። “

TMP – 01/03/2019