ሌሎች 170 ስድተኞች በሜዲትራንያን ባህር ላይ መቅረታቸው ድጋፍ ሰጪ ኤጀንሲዎች ገለጹ

170 የሚገምቱ ስደተኞች ከሊብያና ሞሮኮ በመነሳት ሜዲትራንያን ባህር ለማቋረጥ በመኮሩበት ሰዓት የገብቡበት ሳይታወቅ መቅረታቸው ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ጃንዋሪ  19/2019 ላይባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።  

በመጀመርያው ሙከራ ሶስት ህገወጥ ስደተኞች በሞተር ጀልባ ለመሄድ ሲሞክሩ የተያዙ ሲሆን ሌሎች ሁለት ህጻናት የሚገኙባቸው የገቡበት ሳይታወቅ ቀርተዋል። 120 ስደተኞችም ለመሄድ በመዘጋጀት እንደነበሩ ተገልጸዋል።  ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደገለጸው እነዚህ ስደተኞች  አብዛኞቹ ከምዕራብ አፍሪካ የሄዱ ሲሆን ወደ 40 የሚተጉ ደግሞ ከሱዳን የተነሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።  

የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የሊብያ ቃል አቀባይ ፍላቭዮ ዲ ጊኮሞ እንደገለጹት ስደተኞቹ ወደ ሜዲተራንያን የተነሱት በምስራቅ የትሪፖሊ ክፍል ከምትገኘው ጋራቡሊ ተብላ ከምትጠራ ቦታ ነው።  ቃል አቀባዩ እንዳሉት  ከ10 እስከ 11 ሰዓት ለምያህል ጊዜ በባህር ላይ ከቆዩ በኋላ ጀልባዋ መስመጥ ጀመረች። ስደተኞቹም እየዘለሉ ወደ ባህሩ መግባት ጀመሩ።” ብለዋል ለሮይተርስ በሰጡት ቃል።  ከሞት የዳኑ ስደተኞች በአሁኑ ሰዓት በጣልያን ላምፑድያ ህክምናዊ ድጋፍ እየተሰጣቸው ነው።  

ሁለተኛው አደጋ ያጋጠመው አልቦራን ባህር ላይ ያጋጠመ ሲሆን 53 ስደተኞችን የገቡበት ሳይታወቅ የቀረበት ገጠመኝ ነው፡ እንደ ዩኤንኤችሲአር ገለጻ።  በአሁኑ ሰዓት በሞሮኮ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኝ  አንድ በህይወት የቀረ ስደተኛ  እንደገለጸው ለ24 ሰዓታት በባህሩ ቆይተዋል።

እንደ ዩኤንኤችሲአር ገለጻ ከሆነ ለበርከት ያሉ ቀናት በፍለጋ ላይ እንደነብሩና በመጨረሻም በህይወት የተገኘ ስደተኛ እንደሌለ ገልጸዋል።  ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ  በዘግናኙ የ170 ስደተኞች ሞት የተሰማው ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ይሁንና የጥፋቱ መነሻና ምክንያት ብቻውን ማጣራት እንደማይችል አብራርተዋል።   

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነር የሆኑት ፍሊፖ ግራንዲ የሚዲትራንያን ትራጀዲ በዚህ መልኩ መቀጠል የለበትም” ብለዋል። አክለውም “በአውሮፓ በሮች ላይ እየጠፋ ላለው የሰው ህይወት ባላዩ ማለፍ አይገባንም። ሁሉም ዓይነት መንገድ ተጠቅመን ህይወት ማዳን ይገባናል” ብለዋል።  

ከአይኦኤም የተገኘ ዳታ እንደምያሳየው በጀመርያዎቹ 16 የ2019 ቀናት ብቻ  4,449 ስደተኞች እና አሳይለም ጠያቂዎች አውሮፓ ገብተዋል።  80% በባህር በኩል ወደ አውሮፓ የሚሄዱ ስደተኞች በራቸው ስፔን አድርገዋል።  

TMP – 05/02/2019

ፎቶ ክሬዲት: ገነ ኢሰንኮ/ ሻተርስቶክ. ስደተኞች በስፔን ወደቦች ላይ