የ150 ህገ-ወጥ ስድተኞች አሳዛኝ ህልፈት

በዚህ አመት “ በከፋው የሜዲትራንያን ባህር እልቂት” እስከ 150 ህገ-ወጥ  ስደተኞች እንደሞቱ ( ህይወታቸው እንዳጡ) ይገመታል።

አንድ ስሙን መጥቀስ ያልፈለገው ከአስቃቂ አደጋው የተረፈ ኤርትራዊ ህገ-ወጥ ስደተኛ ለአሶሼትድ ፕረስ እንደገለፀው “ አንድ ቀን ከሰአት በኋላ በጀልባ ተጭነን ከሊብያ ጉዛችንን ወደ ጣልያን ጀመርን። ልክ ከተነሳን ከአንድ ሰዓት በኋላ ጀልባዋ መስመጥ ጀመረች። አብዛኛው ተሳፋሪዎችም ባህር ውስጥ መጥለቅ ጀመሩ” ብለዋል ።

ህገ-ወጥ ስድተኞች አደጋው የገጠማቸው ከሊብያ ወደ ጣልያን ለመግባት የሜዲትራንያንን ባህር እያቋረጡ በነበሩበት ወቅት ነው። በሊብያ  ድንበር ጠባቂዎች ቃል አቀባይ ኣዮብ ቃሲም  ለአሶሼትድ ፕረስ  እንደገለፀው በድምር 300 ስድተኞች የጫኑ ሁለት ጀልባዎች 120 ኪሎ ሜትር ከዋና ከተማ ትሪፖሊ ወደ ባህር ከተጓዙ በኋላ ሰምጠዋል። ብለዋል

የአደጋ ሰራተኞች   የ145 ሰዎች ህይወት ታድገን ወደ ሊብያ መልስናቸዋል ብለዋል። ከአደጋው የተረፉት ሰዎች መጀመርያ በአካባቢው የሚገኙ አሳ አጥማጆች እርዳታ የተደረገላቸው ሲሆን፤ በኋላ የደረሰው  የድንበር ጠባቂ ደግሞ ወደ ባህሩ ጥግ እንዳጓጓዛቸው ታውቋል።

“ ይህ በአመቱ ሜዲትራንያን ባህር ከገጠሙ እልቂቶች እጅግ የከፋው ነው ”  ያሉት ደግሞ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮምሽነር ፍሊፓ ግራንዴ ናቸው

አብዛኛዎቹ ከአደጋ የተረፉ ሰዎች ከኢትዮጵያ ቀሪዎቹ ደግሞ በወረራ ከተያዙት የፍልስጤም ግዛቶችና ከሱዳን  የመጡ ናቸው። ከአደጋው የተረፈች ሱዳናዊ ሳባ ዮሱፍ ለሮይተርስ ስትናገር “ ከአሁን በኋላ ወደ አገሬ ሱዳን በሰላም ከመመለስ በቀር የምፈልገው ነገር የለም። አገሬ ሄጄ ብሞት ይመረጣል” ብላለች። ሱዳናዊትዋ  ሳባ ዮሱፍ በአደጋው አብሯት የነበረ የሰባት አመት ልጅዋን አጥታለች።

ሊብያ ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ ህገ-ወጥ ስድተኞች በጀልባ የሚጓጓዙባት ዋነኛዋ መስመር ናት። እንደ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ዘገባ ከሆነ፤ በዚህ መስመር እስከ አሁን ወደ 700 የሚጠጋ የሞት አደጋ ተከስቷል። ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ፤ በሚቀጥለው ስድስት አመት በሜዲትራንያን ባህር ብቻ 1,000 የሰው ህይወት ይጠፋል። ያሉት ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮምሽን (UNHCR. )  ቃል አቀባይ ቻርሊ ያክሲሊ ናቸው።

የስደተኞች ከፍትኛ ኮምሽን (UNHCR.) ሪፖርት መሰረት በአሁኑ ጊዜ 6000 ህገ-ወጥ ስድተኞች በማእከላዊ ሊብያ በእስር ( ማጎርያ ካምፖች) ይገኛሉ። በዚችው አገር ውስጥ 50,000 ተጨማሪ ጥግተኝነት የጠየቁ ህገ-ወጥ ስደተኞችም እንደሚገኙ አክለው ገልፀዋል።

TMP – 02/08/2019

ፎቶ ክረዲት አልጃንድሮ ካርኒሲሮ

ፎቶ ካፕሽን የፕላስቲክ ስሪት የሆነች ትንሽ ጀልባ በህገ-ወጥ ስድተኞች ታጭቃ በሜዲትራንያን ባህር ላይ መጋቢት 3 2019  እ.ኤ.አ