በጣልያን የባህር ዳርቻ ስደተኞች የጫነች ጀልባ በመስመጥዋ 13 ሴቶች ሞተዋል 8 ህፃናት ደግሞ የደረሱበት ጠፍቷል

የጣልያን የላምፖዶሳ ደሴት  ጠረፍ ጠባቂዎች፤ በጥቅምት 6/2019 ከሰጠመችው ጀልባ ላይ፤ 13 ሴት ስደተኞች አስከሬን አግኝተው ለማውጣት ችሏል። 8 ህፃናት የሚገኙባቸው ቀሪዎቹ በጀልባዋ የነበሩ ስደተኞች ደግሞ እስከአሁን  ጠፍቷል። እንደ ጣልያን ባለስልጣናት እምነት፤ የሰጠመችው ጀልባ መጀመርያ ከሊብያ ስትነሳ 50 ሰዎች ጭና የነበረች ሲሆን፤ቱኒዝያ ላይ ስትደርስ የተሳፋሪ ቁጥር ጨምራለች።

በጀልባው ላይ የነበሩት ስደተኞች፤ ሃላፊዎች ሲመጥዋቸው ወደ አንዱ የጀልባው ጥግ  በመሽሻቸው ለጀልባው መስመጥ ምክንያት እንደሆነ ሲገለፅ፤ ከተሳፋሪዎች መካካል 22 ብቻ ህይወታቸው ሲተርፍ የተቀሩት ሞቷል። ከሟቾች መካከል አንድ የ12 አመት ህፃንን ጨምሮ የ13ቱ አስከሬን በቤተሰቦቻቸው ድጋፍ  ለመለየት ተችሏል።

አንድ ሳልቫቶረ ቪላ የጣልያን የሕግ ጠበቃ  እንደተናገረው ” ጀልባዋ የምትተርፍበት ምንም አማራጭ አልነበራትም። ከመካከላቸው አንድም ተሳፋሪ ደግሞ የህይወት አድን ጃኬት አልነበረውም።’’ ብለዋል

 “አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች ደግሞ ከቱኒዝያና ከሰሃራ በታች ካሉት የአፍሪካ አገሮች የመጡ ናቸው።’’ ብሏል ጠበቃው ቪላ።

የካምፖዶሳ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ጀልባው ከሰመጠበት ጥቂት ኪሎ ሜተሮች ርቀት ላይ ቢኖርም፤ የነብስ አድን ጥሪ ከተደወለላቸው ከረጅም ሰአት በኋላ ነበር በቦታው የደረሱት። በደቡባዊ የጣልያን ግዛት የምትገኘው የካምፖዶሳ ደሴት ፤ ወደ አውሮጳ የሚሻገሩ ሕገ ወጥ ስደተኞች የሚሸጋገሩባት መሬት ነች።

ከቱኑዝያ ወደ ጣልያን ያለው የባህር መስመር አጭር ቢሆንም፤ እጅግ በጣም አደገኛ መስመር ግን እሱ ነው። አንድ ጉዳይ የሚመረምር የሲሲሉ  ጠበቃ እንደተናገረው፤ በቱኒዝያ ወደ ጣልያን ያለው ይኸው መስመር እጅግ አደገኛ ቢሆንም፤ በአሁኑ ግዜ በርካታ ወደ አውሮጳ የሚጓዙ ስደተኞች በዚህ መንገድ መጓዝን መርጧል ብለዋል።

 “ በቱኒዝያ መስመር የመረጡበት ምክንያት፤ ከጥበቃ እይታ ተሰውረው ቶሎ ሲሲሉ ለመድረስ ነው።”

ይህ በቅርቡ የገጠመው አሰቃቂ አደጋ፤ በዚህ መስመር በዚህ አመት ብቻ የነበረው የሟቾች ቁጥር ወደ 1000 ከፍ ያደረገው ሲሆን፤ ሁኔታዎች ደግሞ አዳዲስ የመንግስታት እርምጃዎች የሚጠይቁበት ደረጃ ላይ ደርሷል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮምሽን ቃል አቀባይ ቻርሊ ያዚሊ፤ የአውሮጳ ህብረት በዚህ የሜዲትራንያን መስመር የነበረው የነብስ አድን እንቅስቃሴ መልሶ እንዲያስብበት ጥሪያቸውን አቅርቧል።

TMP 17/10/2019

ፎቶ ክረዲት፤  ነሲብ ዳምሊት

በጣልያን የባህር ዳርቻ / ላምፖዶስ/ ስደተኞች የጫነች ጀልባ በመስመጥዋ 13 ሴቶች ሞተዋል። 8 ህፃናት ደግሞ የደረሱበት ጠፍቷል።