በእንግሊዝ ባህረ ሰላጤ ስድተኛ ህፃናት ከአቅም በላይ ከጫኑ ጀልባዎች ወደ ባህር ይወድቃሉ

በርካታ ስደተኞችን አሳፍረው በእንግሊዝና ፈረንሳይ መካከል በሚገኘው የባህር ወሽመጥ ሲጓዙ ከነበሩት ጀልባዎች ላይ ወደ ባህር ከወደቁት ስደተኞች መካከል ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህፃናት እንደሚገኙባቸው የግብረ ሰናይ ተቋማት እየገለፁ ነው።

በሰሜናዊ ፈረንሳይ የሚንቀሳቀሰውና በ300 ስደተኛ ህፃናት ጉዳይ ላይ የሚሰራው “  ፕለይ ፕሮጀክት” የተባለ ምግባረ ሰናይ ተቋም አባል የሆነችው ራቸል ስካይስ እንደገለፀችው፤ ከጀልባ  ወደ ባህር ከሚወድቁ ህፃናት መካከል አንዳንደቹ በጣም ስለሚጎዱ ወድያውኑ ወደ ሆስፒታል እንደሚላኩ ተናግራለች።

 “ከፕለይ ፕሮጀክት”  መስራቶች አንዱ ክሌር ሞሪስ በበኩሉዋ፤ በርካታ ቤተሰቦች ህፃናት ልጆቻቸውን ይዘው፤ በዚህ የባህር ወሽመጥ ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ ለመሻገር በተደጋጋሚ ይሞክራሉ ብሏል። 

በፈረንሳይና እንግሊዝ የፀጥታ ሃይሎች አመካኝነት  በዚህ መስመር የሚታገቱ ጀልባዎች ሊጩኑት ከሚገባ ከ5 እጥፍ በላይ ሰዎችን አጭቀው እንደሚገኙ ተገልፃል። አሁኑም የሰው ልጅ አሸጋጋሪዎች 6 ሰዎችን ብቻ የመጫን አቅም ያለው  የፕላስቲክ ጀልባ እሰከ 30 ሰዎችን እየጫኑት ይገኛሉ።። ከዚህ ቀደም እስከ 8 ሰዎች ብቻ ይሳፈርባቸው ነበር።

ባለፉት ጥቂት ወራት፤ በዚህ መስመር በሚደረጉ ጉዞዎች ላይ የሟቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። የእንግሊዝ ፖሊስ በዚህ መስመር ላይ ነሃሴ 9 ከጀልባ ወድቃ የሞተችው ስድተኛ ጉዳይ እየመረመረ ሲሆን፤ የቤልጂም ፖሊስ ደግሞ፤ ከወደቀበት ጀልባ የህይወት አድን ጃኬት አጥልቆ ወደ እንግሊዝ የባህር ዳርቻ እየዋኘ በመሃል ላይ ህይወቱን ያጣው የኢራቃዊ ስደተኛ ሬሳ አግኝቷል

እንዲሁም ሆኖ፤ በዚህ መስመር የሚሞክሩ የህገ ወጥ ስደተኞች ቁጥር አሁንም እየጨመረ ነው ተብሏል። በ2019 ብቻ 1000 ህገ ወጥ ስድተኞች ወደ እንግሊዝ ገብቷል። ይህ አሃዝ በ2018 ከተመዘገበው ቁጥር በሶስት እጥፍ ይበልጣል። በመስከረም ወርም ቢሆን ሰዎች (ስድተኞች) በየቀኑ በእንግሊዝ ባህር ዳርቻ እየደረሱ መሆኑ ተመልከቷል።

እንግሊዝ ከአውሮጳ ህብረት ከወጣች ወደ አገሪቱ የሚደረገው ጉዞ በጣም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል የሚለው መላምት፤ ከወዲሁ ወደ እንግሊዝ የሚደረገው ጉዞ እንዲበረታ ሰበብ ሆኗል። በሰሜናዊ የፈረንሳይ ግዛት ያለው  አስቸጋሪ የስደተኞች ኑሮም፤ ወደ እንግሊዝ የሚደረገው የስድተኞች ፍልሰት አባብሶታል። የምግባረ ሰናይ ድርጅቶች እንደሚገለፁት ከሆነ፤ በሰሜናዊ የፈረንሳይ ግዛት በሚገኙት ስደተኞች ላይ፤ ካሁን በፊት ታይቶ በማይታወቅ አኳሃን የስነ አእምሮ ጭንቀት በዝቷል። የራስን መጥፋት ኣጋጣሚዎችም እየተበራከተ መምጣቱ ተናግረዋል።

የፈረንሳይና የእንግሊዝ ባለስልጣናት ባለፈው ነሃሴ ወር ፓሪስ ከተማ ላይ ተገናኝተው በሁለቱም አገራት የጋራ ድንበር ላይ ስላለው እንቅስቃሴ የጋራ ምክክርና የመተጋገዝ መድረክ ካዘጋጁ በኋላ፤ እንግሊዝ በፈረንሳይ በኩል ለሚገቡባት ስደተኞች ለመግታት ለፈረንሳይ ፋይናንሳዊ እገዛ ለማድረግ ተስማምታለች።

TMP 03/10/2019

ፎቶ ክሬዲት፤- ማሪን ናሽናል / ጌቲ ኢሜጅን/

በእንግሊዝ የባህር ወሽመጥ ስደተኞችን ጭና በመጓዝ ላይ የነበረችውና ነዳጅ ጨርሳ የታገተችው ጀልባ ላይ የነበሩ ሰዎች በፈረንሳይ የባህር ኋይሎች እየዳኑ።