ኢትዮጵያ በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ደላሎች የሞት ቅጣት እንዲኖር ትፈልጋለች

የኢትዮጵያ ህግ አውጪዎች በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችና ደላሎች ላይ ከባድ ቅጣቶችን የሚደነግግ፣ የሞት ቅጣትን ጨምሮ እንዳረቀቀች አስታወቀች፡፡ ይህ ህግ የተረቀቀው በቀጠናው ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል፣ ህገ ወጥ የውጭ ሃገር የስራ ስምሪትና የተደራጁ የወንጀል ብዱኖችን ለመቆጣጠው እንዲረዳ ተብሎ ነው፡፡

ብዙ ስደተኞች እና የኢትዮጵያ ዜጎች መደበኛ ባልሆኑ መንገዶች አማካይነት ወደ አውሮፓ ፣ መካከለኛው ምስራቅ ፣ ወደ ባሕረ ሰላጤ ግዛቶች እና ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመድረስ ለሕገወጥ አዘዋዋሪዎችን ይከፍላሉ ፡፡ በነዚህ ህገ ወጥ የጉዞ መስመሮች ተጓዦች (ስደተኞች) አስቸጋሪ ፈተናዎች እንደሚገጥሟቸውና እነዚህም ችግሮች ረሃብ፣ የውሃ ጥምና ድርቀት፣ አካላዊና ወሲባዊ ጥቃቶችና እስከ ህይወት ማለፍ (ሞት) እንደሚደርስባቸው ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያ በሶስቱም አቅጣጫዎች፤- ወደ አረብ ባህረ -ሰላጤ፣ ደቡብ አፍሪቃና አውሮጳ ለመሄድ በሚነሱባቸው ዋና የአፍሪቃ ሃገራት አንዷ ስትሆን ፤ ዋና የህገ ወጥ የመተላለፍያ ቦታ (ሃገር) መሆኗ ይታወቃል፡፡ አሃዛዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በየዓመቱ ከአንድ መቶ ሺ በላይ ( 100,000 ) ስደተኞች ከኢትዮጵያ፣ኤርትራና ሱማልያ ወደ የመን በህገ ወጥ መንገድ እንደሚጓጓዙና በመንገድም ችግር እንደሚገጥማቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪም 700,000 የአፍሪቃ ስድተኞች ኢ-ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ በሊብያ ታግተው እንደሚገኙና አብዛኛዎቹም ከኢትዮጵያና ከኤርትራ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ረቂቅ ህጉ በካቢኔ አባላት በነሃሴ ወር ፀድቆ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ ይሰጣል፡፡ የጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት  ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱሉ “ አሁን ያሉት ህጎች ችግሩን ለማስወገድ በቂ አይደለም “ ሲሉ በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ በለስልጣናት ከ2015 እ.ኤ.አ ጀምሮ የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ለማስቀረት በአዋጅ ቅጣቶችን ለማካበድ ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ አዋጁ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙትን ሰዎች ከ15 ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ ቅጣት ደግሞ እስከ 10 ሺ የአሜሪካን ዶላር የሚደርስ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ሌላው ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ለማስቀረት የሚደረገው የመንግስት ጥረት የግንዛቤ ማሳደግያ ስራዎችና ዘመቻዎች ሲሆኑ ከጎረቤት ሃገሮች ጋር የሚደረጉ የድንበር አስተዳደር የማጣናከር ስምምነቶችም ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ጥረቶች ቢደረጉም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገሮች  ይሰደዳሉ።

TMP 29/10/2019

ፎቶ ክሬዲት ስእል – ኢክፕሮ/ ሻተርስቶክ ሸኮም

ካፕሽን የኢትዮጵያ ወታደር በድንበር ላይ