በባህረ ሰላጤው መስመር ኢትዮጵያውያን ስድተኞች ላይ ጥቃት ደረሰ

በአደገኛው የኤደን ባህረ ሰላጤ መስመር በሚጓዙት ኢትዮጵያውያን ላይ በህገ ወጥ ደላሎችና የሰው አዘዋዋሪዎች አመካኝነት ከፍተኛ ሰብአዊ በደልና ብዝበዛ እየደረሰ መሆኑን፤ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት (HRW ) ባለፈው ነሃሰ 15 ገልፀዋል። ድርጅቱ አክሎ እንደገለፀው፤ ከባህር ላይ ብዝበዛና በደል ተሻግረው ስዑዲ ዓረብያ ላይ የገቡት ስደተኞችም ለእስርና እንግድልት ይደረጋሉ።

12 ከስዑዲ ዓረብያ የተባበሩ ኢትዮጵያውያንን አነጋግሬለሁ ያለው የሰብአዊ መብት ድርጅት፤ በህገ ወጥ መንገድ ስዑዲ የገቡና ገና ያልገቡ ኢትዮጵያውያን ሰብአዊ ግርፋት፣ጉልበት ብዝበዛ፣ በቀጥታ ከአገር ማባረርና ለሞት እንደሚደረጉም ገልፀውልኛል ብለዋል።

ድርጅቱ ካነጋገራቸው 12 ሰዎች መካከል አስራ አንዱ በቀጠናው ተባብሶ ባለው  የህገ ወጥ ስደት ደላሎችና የሰው አዘዋዋሪዎች አመካኝነት የተሰደዱ ናቸው። 12 አንዱ ስደተኛ በህጋዊ መንገድ ስዑዲ ገብቶ ሲሰራ የነበረ ሲሆን፤ ወደ ነበረበት ስዑዲ በህገ ወጥ መንገድ ተሰዳ የመጣችው እህቱን ለመቀበል በሞከረበት ግዜ ተይዞ አብሯት ተባሯል።

እንደ ሰብአዊ መብት ድርጅት ገለፃ፤ በስድተኞች ላይ የሚደርሰው አረሜናዊ ግፍና ብዝበዛ ከመነሻ የመን ጀምሮ ባህር ላይ፣ ወደብ ከደረሱ በኋላ፣ አገር ውስጥ ከገቡና ስራ ከጀመሩም በኋላ የሚቀጥል የማያበራ ግፍ ነው ብለዋል። በህይወት ለተረፉት ስደተኞችም እየተለቀሙ ያለ ምንም ገንዘብና ተስፋ ወደ መጡበት እየጫኑ ያራግፋቸዋል።

ቃለ መጠይቅ የተደረጉ ስደተኞች ጨምረው እንደገለፁት፤ በተለይ የመን ላይ የሚገጥማቸው ህገ ወጥ ወረበሎች፤ በብትር እየቀጠቀጡ ወደ ቤተሰብ እየደወሉ ገንዘብ እንዲላክላቸው ያስቸግራሉ ብለዋል እንደ ስደተኞቹ አገላለፅ በየመን በኩል በአሁኑ ግዜ ስደት መሞከር በባህር ውስጥ በሰው በታጨቀ ጀልባ ያለ ምንም ምግብና ውሃ ራስህን ማግኘትናበራስህ ፍቃድ ህይወትህን ወደ አደጋ መክተት ማለት ነውብለውታል። አንድ ስደተኛደላሎቹ ሰውን ለመቀነስ ከታጨቁ ጀልባዎች ላይ ወደ ባህር ውስጥ ስወረውሩ አይቻለሁብለውታል።

መጀመርያ ጉዞ ስንጀምር 180 ሰው በጀልባው ነበርን። ከኛ ውስጥ 25 መንገድ ላይ ሞቱይላል አንዱ ተጓዥ።  ማእበሉ ኩፍኛ ጀልባዋን መምታት ሲጀምር ልትሰጥም ሆነ። በዚህ ማከል ደላላው 25 ሰዎች እያነሳ ወደ ባህር ጣላቸውብለዋል።

ደላለዎቹ የጀልባዋን ጭንቅ ለመቀነስ ሰዎች ከነህይወታቸው ወደ ባህር የሚጥሉበት ተሞክሮ ይህ የመጀመርያ አይደለም።

የመን ላይ ከደረሱም በኋላ፤ ስደተኞቹ ተጠልፎ ለመጥፋት፤ ከግርፋት እንዲሁም ወደ ስዑዲ እንዲሳገሩ ለተጨማሪ የገንዘብ ክፍያ እንደሚገደዱ ይታወቃል። በየመንና በሱዑዲ  ዓረብያ መካከል ባለው ግጭት አመካኝነት ደግሞ ህገ ወጥ ስደተኞች ለከፋ የሞት አደጋ እንደሚጋለጡ ይታወቃል።

የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት የጠየቃቸው ስደተኞች እንዳረጋገጡት፤ በየመንና በስዑዲ ድንበር በረሃ ላይ በርካታ የሞቱ የስደተኞች አስከሬን አይተናል ብለዋል። አንድ ስደተኛ እንደአረጋገጠውይህ መስመር ልክ የመቃብር ስፍራ  ይመስላል።ሲል አስከፊ ሁኔታውን ገልፆታል።

በአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተከራካሪ ከፍተኛ የምርምር ባለሞያ ፍሊክስ ሆርኔ እንዳሉትየተሻለ ህይወት ፍለጋ ከአገራቸው የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን፤ ወደ ሱዑዲ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ እጅግ የከፋ ግፍና እንግልት ይደርስባቸዋል። ይህም ቶርች( ግርፋት) በባህር ውስጥ ሞት እንዲሁም ሁሉን አይነት ሰብአዊ ጥሰትን ያካትታልብለዋል። እንደ ድርጅቱ ገለፃ ከሆነ፤ኢትዮጵያ  የመንና ስዑዲ ዓረብያ በስደተኞች ላይ የሚደርሰውን ግፍና አደጋ ለመቀነስም ሆነ በደላላዎች ላይ  እሰፈላጊው እርምጃ ለመውሰድ ብዙም ጥረት አያደርጉም።

.. . ከግንቦት 2017-መጋቢት 2019 ባለው ግዜ ውስጥ ለግማሽ ሚልዮን(500000) በላይ ኢትዮጵያውያን ስዑዲ ዓረብያ ከመግባት እንደተከለከሉና በህገ ወጥ መንገድ ገብተው የነበሩም እንደተባረሩ አለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት አስታውቋል።

TMP – 30/08/2019

ፎቶ ክረዲት በአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት

በኢትዮጵያና ሱዕዲ ዓረብያ መካከል ያለው የስደት መስመር