በህገ ወጥ የሰዎች ድለላ የተጠረጠረ ቡድን በጣልያን ፍርድቤት የአስርት አመታት እስር ተፈረደበት

ኦገስት 2015 በአጋጠመው የጀልባ መገልበጥ አደጋ ምክንያት 49 ስደተኞች መሞታቸው ተከትሎ የተጠረጠረ በርክት ያሉ ሰዎች ያሉበት አንድ ቡድን ቅጣት ተፈረደበት። የጣልያን ከፍተኛ ፍርድቤት ሶስት ህገ ወጥ ደላሎች ለሁለቱ 20 ዓመት የእስር ቅጣት እንዲቀጡ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። የካታናው ፍርድቤት ይግባኝ አልቀበልም በማለት ፍርዱ እንዲፀና ሆነዋል። 

ሌሎች አምስት ግብረ አበሮች የተቀጡት የእስር ቅጣት ተደምሮ በቡዱኑ ላይ በአጠቃላይ 120 ዓመታት ፍርድ መተላለፉን ነው የተነገረው።

ስምንቱ ወንጀለኞች የተያዙት ኦገስት 15 ቀን 2015 ሲሆን ሲጎላ ፍሎግሲ የተባለ የጣልያን ወተሃደራዊ ጀልባ በደረሰው ጥቆማ መሆኑ ታውቀዋል። በግዜው ወተሃደራዊ ጀልባው ስደተኞቹ ወደቁበት በተባለ ቦታ ቢደርሱም 49 ስደተኞች በህይወት ሊገኙ አልቻሉም። የእነዚህ ህይወት መጥፋትም በቸልተኝነት ነው ተብለዋል። ጀልባዋ በምዕራብ የሊብያ ክፍል የምትገኝ ዝዋራ የተባለችውን ከተማ ቀደም ብሎ በሌሊት አልፋ ለመሄድ እንደሞከርችም ተነግረዋል።

አደጋው ከአጋጠመ በኋላ ሲጎላ ፍሎግሲ በህይወት የቀሩት 313 ስደተኞች እና የሞቱትን ሬሳ ይዞ ባለቤትነትዋ የኖርወይ ጃን ወደሆነችው ጀልባ ወስዶዋቸዋል። ስደተኞቹ ከአፍሪካ፣ ኤስያ እና መካከለኛ ምብራቅ የመጡ ናቸው።

በጣም በተጨናነቀ ሁኔታ ሰዎች ጭና የተነሳቸው ይህች ጀልባ ከተነሳች በአጭር ሰዓታት ውስጥ መስጠም የጀመረች ሲሆን ለማዳን በተደረገ ጥረትም ማዳን አልተቻለም። ከውስጥ ቃጠሎ በመነሳቱም ስደተኞቹ ለሞት መዳረጋቸው ተገልፀዋል። ሟቾቹ ያገቡ በመሆናቸው አደጋው ከመከሰቱ በፊት ለሚስቶቻቸው መልእክት እየሰጡ ነበርም ተብለዋል።

በተለይ ወደ ኢንጅኑ አከባቢ የነበረ እሳት መቋቋም የምትችለው አይነት አልነበረም። አንዳንድ ስደተኞች ለማቆም ሞክረዋል። ይሁንና ለመጠጥ የሚሆን ውሃ እንኳን አልነበራቸውም። ስለሆነም ወደ እንጅኑ አከባቢ የነበሩ ስደተኞች ምንም አማራጭ አልነበራቸውም። አንድ በአንድ እየተቃጠሉም ሊሞቱ ችለዋል። የህይወት አድን አካላት ሲመጡ ያጋጠማቸው የመጨረሻው አሳዛኝ ሁኔታ ነው።ብለዋል የአለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም ሰራተኛ ፋሊቮ ግያኮሞ።

እንደ ጣልያኑ አቃቤ ህግ ከሆነ ስደተኞቹን መተዋል። በቀበቶ ገርፈዋል።በጀልባዋ ውስጥ ታፍነው እንዲጓዙ በማድረግ በአደጋ ጊዜ መልእክት እንዳይሰጡ አድርገዋልያለ ሲሆን በመሆኑምበኦክስጅን እጦት የሰው ህይወት እንድያልፍ ምክንያት ሆነዋልብለዋል።

ሶስቱ የቡዱኑ አባላት ከሊብያ፣ ሞሮኮ እና ቱንዝያ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችለዋል። ተጠርጣሪዎቹ በህገ ወጥ የሰው ልጅ ድለላ እና ግድያ ወንጀል ነው የተፈረደባቸው። ይሁን እንጂ ሶስቱ አካላት ከደሙ ንፁህ ነን ብለዋል።  አምስቱ ግብረአበሮችም በፍርድ ሂደው ውስጥ መሆናቸው ተነግረዋል።

TMP – 25/04/2019

Photo credit: ሹተርስቶክ

Photo caption: የኖርወይጃን መርከብ ሲሆን 49 ሰዎች በሞቱበት አደጋ በህይወት የቀሩት 312 ስደተኞችና የሞቱትን ሬሳ ይዞ ይታያል፤ ካታንያ፤ ኦገስት 17 ቀን 2015