የአውሮጳ ህብረት በሜዲትራንያን ባህር ላይ የሚደረገው የስደተኞች የነብስ አድን ፍለጋ እቅድ ተቃወመ

ባለፈው ጥቅምት 24/2019 በዋለው የአውሮጳ ህብረት ስብሰባ ላይ የቀረበው በሜዲትራንያን ባህር ለሚጓዙት ስደተኞችና ተፈናቃዮች የነብስ አድንና የፍለጋ ስራ ማሻሻል እቅድ ውድቅ የተደረገው 288 የድጋፍና 290 የተቃውሞ በጠባብ የአብላጫ ድምፅ ነው፡፡

ለአውሮጳ ህብረት አባል መንግስታት ቆርቦ የነበረው እቅድ  “ የበርካታ ስደተኞች ህይወት ሊያድን በሚችለው በሜዲትራንያን የስደት መስመር በኩል፤ በቂ የጀልባና የነብስ አድን ትጥቆችን በማዛጋጀት፤ ስራውን በተጠናከረና አስቀድሞ በተጠና መንገድ መፈፀም”  የሚል ነበር፡፡

በተጨማሪም አባል አገሮቹ ወደቦቻቸው በነብስ አድን ተግባር ላይ ለሚንቀሳቀሱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጀልባዎች ክፍት ማድረጋቸውን የሚጠይቅ ነበር፡፡

በቀረበው ጉዳይ ላይ ውይይት ሲደረግ እነዚያ በአውሮጳ ህብረት ፓርላማ፤ አብላጫ ወንበርና የቀኝ ዘመም አመለካከት ያላቸው የፓርላማው አባላት በጥብቅ የተቃወሙት ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ የግራ ዘመም ሶሻሊሰት ሊበራልና ግሪን ፓርት አባላት ደግፈውት ነበር፡፡

ስፔይናዊ የአውሮጳ ፓርላማ አባልና የስብሰባው ቃል አቀባይ ዱአን ፈርናንዶ ሎፔዝ አጉዩላር ከድምፅ አሰጣጡ በሃላ እንደተናገሩትዛሬ ቀኝ ዘመም የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ቡዱኖች ከህጋዊና ሞራላዊ ግዴታቸው ሲሸሹ ተመልክተናል ፡፡ በባህር ላይ  የሚቀጠፈው የሰው ህይወት ከማዳን ሃላፊነት ሸሽቷልብሏል፡፡

ከምንገምተው በላይ እጅግ ቁጥሩ የበዛ ሰው በሜዲትራንያን ባህር ላይ ህይወቱን እያጣ ነውበማለት ጨምረው ተናግረዋል፡፡ 

አንዳንድ የአውሮጳ አገሮች፤ በሜዲትራንያን በኩል በሚደረገው የስደት ጉዞ ላይ የነብስ አድን ቅድመ ጥንቃቄና ዝግጅት ማድረግ ማለት ተጨማሪ ህገ ወጥ ስደትን ማበረታታት ነው  በማለት እንደዚህ አይነት ፖሊሲ ከማውጣት እንደሚታቀቡ  ይታወቃል፡፡ የጣልያን መንግስት ደግሞ ከዚህ አለፍ ብሎ ጭራሽ የግብረ ሰናይ አድን ጀልባዎች፤ በባህር ላይ ለጠለቁ ህገወጥ ስደተኞች እንዳይደርሱላቸው የሚከለክል ዘመቻ አውጃል፡፡

በርካታ ግብረ ሰናይ ሰብአዊ ድርጅቶች፤ የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ የሻረውን ውሳኔ ተቃውሞታል፡፡ ከነዚህ መካከል ኦክስፋም የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት፤ የአውሮጳ ህብረት አገራት፤ የነብስ አድንና የፍለጋ ስራው አጠናክረው መቀጠል ይጠበቅባቸዋል ካሉ በሃላ፤ “  በተለይም ከሊብያ የድንበር ጠባቂዎች በመተባበር ስደተኞችን ተመልሰው በሊብያ እስር ቤቶች መክተትና ማሰቃየት አስፈሪ ስራ ሊቆጠቡ ይገባልብለዋል፡፡

ድንበር የለሽ ሃኪሞች (MSF  ) በበኩሉ፤ የአውሮጳ ህብረት ወቅታዊ ፖሊሲ፤ የሊብያ የድንበር ጠባቂዎች በስደተኞች ላይ የሚደርሱት መጠነ ሰፊ ጥፋት እንዲቀጥል መፍቀድና ስደተኞችን ወደ ባሰ ስቃይ መክተት ነው ሲል ተችቶታል፡፡

 “  አሁን የተወሰነው መፍትሄ ዋና ትኩረቱ ስደተኞችን ለማገዝ፣ ለማዳንና ለማቆም የሚረዳ አይደለም፡፡ ይልቁንም በስደተኞችና ጥግተኝነት ጠያቂዎች ላይ በሊብያ የድንበር ጠባቂዎ አመካኝነት የሚደርሰው ኢሰብአዊ ጥፋት ወደ ከፋ ደረጃ የሚያደርስ ውሳኔ ነው”  ብሏል የድንበር የለሽ ሃኪሞች፡፡

አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ባለፈው ጥቅምት ወር የለቀቀው ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ 2014 ወዲህ እስካሁን 18,000 ሰው በሜዲትራንያን ባህር ህይወቱን አጥተዋል፡፡  በ2019 ደግሞ የ1,000 ሰው ህይወት ጠፍቷል፡፡

በዚህ አመት ብቻ 82,000 ህገ ወጥ ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር መስመር ብቻ ወደ አውሮጳ አገራት ገብቷል፡፡ ባለፈው አመት 100,000 በተመሳሳይ ጊዜ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

TMP 14/11/2019

ፎቶ ክረዲት፤- ሊብያ ስሎናሪ / ሽታርስቶክ

ፎቶ ካፕሽን፤- ወደ አውሮጳ ለመግባት ከተነሱት ስደተኞች ወስጥ በዚህ አመት ቢያንስ 1080 ሰው ሞቷል ወይ የት እንደገቡ ጠፍቷል፡፡