ከህገ ወጥ ደላሎች ለማምለጥ በሞከሩ የምስራቅ አፍሪካ 140 ስደተኞች ጉዳት ደረሰ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣው ዘገባ እንደገለፀው በሊብያ ከህገ ወጥ ደላሎች ለማምጥ ሲሉ ባጋጠመ አደጋ ብያንስ 15 ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉ ተገልፀዋል። ይህ አደጋ የተከሰተው በሊብያ ባንወሊድ በተባለች ከትሪፖሊ ወደ ደቡባዊ ምስራቅ 145 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው። በአደጋው ብዙዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ይህ አደጋ ያጋጠመው በግንቦት 23 ሌሊት ሲሆን በግምት ወደ 140 የሚደርሱ አብዛኛዎቹ በአፍላ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ከኤርትራ፣ ኢትዮጵያ እና ሶማልያ በመጡ ስደተኞች ላይ ነው። እነዚህ ስደተኞች ባንዋሊድ ላይ ሰብስቦዋቸው ከነበረ ሙሳ ድያብ በመባል ከሚታወቀው እውቁ ደለላ ለማምለጥ ባደረጉት ሙከራ ነው ይሄንን አደጋ የተከሰተው።
እንደ ድንብር የለሽ ሀኪሞች (Doctors without Borders) ገለፃ ከሆነ እነዚህ ስደተኞች በባንዋሊድ እና ነስማ ከተሞች ላይ በተደጋጋሚ ተሽጠዋል።
የሞቱት ስደተኞች ከደላላው እጅ አፈትልከው ለማምለጥ ሲሞክሩ የተገደሉት ሲሆን ብዙዎችም ለጉዳት ተዳርገዋል። ብያንስ 25 ስደተኞች ወደ ሆስፒታል ሪፈር እንደተባሉ እና ባንዋሊድ ላይ በሚገኝ ሆስፒታል በኤምኤስኤፍ ቴክኒካዊ ድጋፍም ጭምር እየታገዙ ህክምና እያገኙ ነው ተብለዋል።
ጉዳት ከደረሰባቸው ስደተኞች መካከል 18ቱ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ቀላል የህክምና እርዳታ አግኝተዋል። ሰባት በሽጉጥ ጥይቶች ክፉኛ የተጎዱ ወገኖች በየተላለዩ የሰውነታቸው ክፍሎች ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው እና አልጋ ይዘው እየታከሙ መሆናቸው ታውቀዋል።
የባንዋሊድ ሆስፒታል እንደገለፀው ደግሞ ወደ 20 ስደተኞች በቶርቸር ተጎድተው የመጡ ሆነው ህክምና እየተደገረላቸው ነው።
በህይወት የቀሩ ስደተኞች ለኤምኤስኤፍ በሰጡት የአይን ምስክርነት እንደአብራሩት በጥቂቱ 15 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በአብዛኛው ሴቶች የሚገኙበት ወደ 40 የሚጠጉ ስደተኞች የያዘ ቡድንም ወደኋላ ቀርተዋል።
ከእነዚህ የአይን ምስክሮች የተገኘ መረጃ እንደምያሳየው ብዙዎቹ ለሶስት አመታት ለሚደርስ ጊዜ በእስር አሳልፈዋል። የኤምኤስኤፍ የህክምና ቡድን እንደገለፀው እነዚህ ስደኞች እጃቸውን ጨምሮ በተለያዩ የሰውነታቸው ክፍሎች ታስረው እንደነበሩ የምያሳዩ በርካታ ምልክቶች አይተንባቸዋል ብለዋል። ብዙዎቹ ላይ የኤሌክትሪክ ቶርች ጠበሳዎች ተገኝቶባቸዋል። ይህም የስደተኞቹ የስቃይ ብዛት እና መጠን የምያሳይ ነው ተብለዋል።
እነዚህ በህይወት የቀሩ ስደተኞች ባንዋሊድ ከተማ ውስጥ የደህንነት ድጋፍ እና እርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ግንቦት 24 ላይ ወደ ትሪፖሊ አከባቢ የሚገኙ የስደተኞች መጠልያ ማእከላት እንዲዘዋወሩ ተደርገዋል።
ትሪፖሊ የስደተኞች መጠልያ ማእከል ከደረሱ በኋላም ለ117 ስደተኞች የህክምና እና የስነ ልቦና ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን መሰረታዊ የምግብ እርዳታ እንድያገኙም ተደርገዋል። 14 በሽጉጥ ተመትተው አደጋ ላይ የነበሩ ስደተኞች ለተጨማሪ የህክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎላቸዋል።
ስደተኞቹ እንደሚሉት በአሁን ሰዐት እነዚህ በህገ ወጥ የሰው ልጅ ድለላ የተሰማሩ ወንበዴዎች በተለይ በባንዋሊድ በመሳሰሉ አከባቢዎች ህገ ወጥ ስራው በከፍተኛ ደረጃ እያጧጧፉት ነው። በመሆኑም ወደ 20 የሚጠጉ ከመሬት በታች ተቆፍረው የተሰሩ (አንደርግራውንድ) እስርቤቶችም ገንብተዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው በተደጋጋሚ ቶርች የተደረጉ እና በተደጋጋሚ የተደፈሩ ስደተኞች በእነዚህ እስርቤቶች እንዲቆዩ ይደረጋል። ከቤተሰቦቻቸውም ገንዘብ እንዲላክ ይደረጋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ አሁንም በእነዚህ እስርቤቶች እና በህገ ወጥ ደላሎቹ እጅ ወድቀው እንደሚገኙ ይታመናል።
TMP – 18/06/2018
ፎቶ: በኤምኤስኤፍ. በኤምኤስኤፍ ለስደተኞች ድጋፍ የሚሰጥ ተቋም ነው።
ፅሑፉን ያካፍሉ