እንግሊዝ ህገወጥ ስደተኞችን ወደ ፈረንሳይ መለሰች

የእንግልዝ ባለስልጣናት ወደ ሀገራቸው የገቡትን ህገ ወጥ ስደተኞች ወደ ፈረንሳይ የመመለስ ስራ ጀመሩ። ባለፈው የፈረንጆች አመት መጨረሻ በትንሽ ጀልባ  የእንግሊዝ ምድር የረገጡት የመጀመርያ ቡድን ጃንዋሪ 24/ 2019 ወደ ፈረንሳይ እንዲመለሱ ተደርገዋል።  

የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ጽ/ቤት እንደገለጸው በ2018 የፈረንጆች አመት 539  ህገወጥ ስደተኞች በትንሽ ጀልባ ወደ እንግሊዝ ለመግባት አስበው ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል።  

ከእነዚህ ስደተኞች 80%ቱ በኦክተበር ወር ብቻ የእንግሊዝ ቻናል ለማቋረጥ አስበው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸውን ተገልጸዋል።   ይህ ቁጥር በስካይ ኒውስ “ታላቁ ሁነት” ተብሎ ተመዝግበዋል። እንግሊዝ ከፈረንሳይ ጋር በመሆን በወሰን አከባቢ ያለ የጸጥታ ጉዳይ የተሻለ ለማድረግ እየሰሩ ነው ተብለዋል።

ጽ/ቤ ቱ በመግለጫው እንዳወሳው ከሆን ይህ ህገወጥ ስደተኞችን በሀይል የመመለስ ስራ “በአደገኛው መስመር የሚደረግን ጉዞ ለመከላከል ያስችላል።” እንግሊዝ ህገ ወጥ ስደተኞች እየመለሰች ያለችው ዱብሊን ረጉሌሽን የሚባለው የአውሮፓ ህብረት ያስተላለፈው ህግ ስር በመሆን ነው። ህጉ አባል ሀገራት እንዲፈጽሙት የምያዝዝ ነው።   

እንግሊዝ በድንበር አከባቢ ለሚደረግ ጥበቃ የምታደርገው ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል እየተነገረ ነው። የፈረንሳይ መንግስት በወሰን አከባቢ፣ በወደቦች እና የባህር ዳሮች ላይ ለምያደርገው የባህር እና የምድር ላይ ጉዞ ጥበቃ የሚውል ከ6 ሚልዮን በላይ ገንዘብ ተለቀዋል። ሌላ 3.2. ሚልዮን ደግሞ በሌሎች ዲጂታል የሆኑ መሳርያዎች ማለትም ምስጢራዊ ካሜራና የሌሊት እይታ መሳርያዎችን ለመግዛት እንደሚለቀቅ ተገልጸዋል።

ጃቩድ ለኢንደንደት የተባለ ሚድያ  “ምስኪን ስደተኞችን ከአደገኛው ጉዞ ለማትረፍና በእነዚህ ህይወት ለመበልጸግ በምያስቡ ህገ ወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ከፈረንሳይ አጋሮቻችን በጋራ እንሰራለን።” ብለዋል።

ሀልፕ ሪፊጅስ በተባለው ድርጅት የፊልድ ሰራተኛ የሆነውን ጆሽ ሃላም እንደገለጸው ስደተኞቹ ፈረንሳይ ዊንተር ወቅት በሚኖር ያልተመቸ የአየር ሁኔታ ምክንያት ተገፍተው እንዲሰደዱ ሌላ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል።  

ባለሙያው አክሎ ትክክለኛ እና ይፋዊ የመረጃ እጥረት አለ” ብለዋል። “ይህ ክፍተት እየተሞላ ያለው ሊጠቀሙብህ በምያስቡና አደገኛ በሆኑ ግለሰብዎች ነው።” ብለዋል።

ሃለም እንደሚለው እነዚህ ህገ ወጥ ደላሎች ስደተኞችን ከ 3,000 እስከ 10,000 የእንግሊዝ ፓውንድ ያስከፍላሉ። ይሄም በጣም  አስጊና አደገኛ በሆነው የጀልባ፣ የባቡርና የመኪና ጭነቶች ላይ ለመውሰድ ነው።

 

ፎቶ ክሬዲት: ፊሊኦ ሁገን / አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ኦየፕላግ የባህር ዳር ካሊስ በተባለ የፈረንሳይ ሰሜናዊ ክፍል ትታየለች። ቀኑም ጃንዋሪ 9/2019 ነው።  ወደ ፈረንሳይ ለመግባር በሙከራ ላይ የነበሩ ስደተኞችን ሲዩዟቸው ያሳያል።

TMP – 02/02/2019

የፎቶ መልእክት: የፈረንሳይ ፓትሮል በFrench gendarmes patrol on the beach of Oye-Plage, near Calais,