ያልተገመተ የእንግሊዝ ቻናልን የማቋራጥ ህገ ወጥ ስደት
በሱዳን የተከሰተ የህገ ወጥ ስደት መጨመር ባስከተለው ችግር ምክንያት ስደተኞች የእንግሊዝ ቻናልን በብዛት ለማቋረጥ እየመኮሩ በመሆኑ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ የቁጥጥር ኬላአቸው እያሰፉ መሆናቸውንኑ ተነግረዋል። ይህ ሁነት የታየው በ2008 የማገባደጃ ዓመት ላይ ነው።
ይሄንን ያልተገመተ የስደተኞች ጭማሪ ተከትሎ እንግሊዝ ተጭማሪ የቁጥጥር ስርዓት ዘርግታለች። ህገ ወጥ ስደተኞችም ወደ ፈረንሳይ በመመለስ ወደ ሌላ የማቋረጥ ቦታ እንዳይደርሱ በማደረግ ላይ መሆንዋ ተነግረዋል። የፈረንሳይ የጸጥታ ሃይልም ህገ ወጥ ደላሎችን የሚይዙበት ስልት እያደራጁ ናቸው። ስደተኞችም አደገኛው ጉዞ እንዳያደርጉ እያደረጉ ነው ተብለዋል። የፈረንሳይ የአየርና የወሰን የጸጥታ ሃይል አባል የሆነውን ፍራንክ ቶልዩ ለሮይተርስ እንደገለጸው በ2018 በሰሜናዊ የሀገሪቱ ወሰን 26 የህገወጥ ደላሎች ኔትወርኮች ተበጣጥሰዋል።
የእንግሊዝ ቻናል ብዙ ጊዜ የተጨናነቀ ከመሆኑ በተጨማሪ ህገ ወጥ ደላሎቹ የሚጠቀሙባቸው ጀልባዎች ለጉዞው የማይመጥኑ በመሆናቸው ለአደጋ ያለው ተጋላጭነት የላቀ ነው። ሮይተርስ፡ ሰሜናዊ ፈረንሳይ የምትገኘውን ግራንዴ ሳይንቴ የምትባለዋን ከተማ በከንቲባነት የሚመሩት ዳሚን ካርሚ ያሉትን በእንደዚህ መልኩ ጠቅሶታል። “ቻናሉ ከሜዲትራንያን ቀጥሎ ሁለተኛው የሞት ዜና የሚሰማበት እንዲሆን አንፈልግም”
የፈረንሳይ ባለስልጣናት እንደገለጹት በ208 ብቻ 71 ትናንሽ መርከቦች ቻናሉ ለማቋረጥ ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህ ቁጥር በ2017 ካጋጠመ ተመሳሳይ ሙከራ ብስድስት እጥፍ የሚልቅ ነው። ከዚህኛው ቁጥር ደግሞ 57ቱ በ2018 በኖቨምበር እና ደሰምበር ወሮች ብቻ ያጋጠሙ ናቸው፡ እንደ አሶሸቲድ ፕሬስ ዘገባ።
ከአሁን በፊት ህገ ወጥ ስደተኞች የእንግልዝ ምድር ለመድረስ ሲጠቀሙበት የነበረ ስልት በትላልቅ እቃዎች ስር ተደብቀው መሄድን ነው። በዚህም ምክንያት እንግሊዝና ፈረንሳይ የቁጥጥር ስርዓታቸው እየከረረ መጥተዋል። በአሁን ሰዓት ባለስልጣናቱ ተሽከርካሪዎችን በቴክኖሎጂ ታግዘው ምርመራ በማድረግ ነው የምያሳልፉዋቸው። በ2018 ብቻ በተለያዩ ተሽከርካሪዎች ውስጥ ተደብቀው ሊገቡ የነበሩ ወደ 3,000 የሚጠጉ ስደተኞች በሰሜናዊ የፍራንስ ክፍል ተይዘዋል።
የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር እንደገለጸው አብዛኛዎቹ በህገ ወጥ መንገድ ወደ እንግሊዝ ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ስደተኞች ኢራናውያን ነን ብለዋል። የሰርብያ የስደተኞች ድጋፍ አሰተባባሪ የሆነውን ሚዮድራግ ካኪክ ለቢቢሲ እንደገለጹት ይህ ጉዳይ ምናልባት ባላፈው ዓመት የባልካን ሃገራት ለአጭር ጊዜ ለኤራናውያን ፈቅደውት ከነበረ ነጻ ቪዛ ጋር ተያያዥነት ይኖረዋል ብለዋል።
ከ1979 ጀምሮ በተቀጣጠለ የሙስሊም አብዮት ምክንያት ከ 50,000 እስከ 200,000 የሚገመቱ ኢራናውያን በየአመቱ ሀገራቸው ትተው እንደሚሰደዱ ተገልጸዋል። የሀገሪቱ ይፋዊ ዳታዎች እንደምያሳዩት እንግሊዝ ላለፉት ሁለት አመታት ከማነኛውም ሀገር በላይ ብዛት ያላቸው ስደተኞች የተቀበለችው ከኢራን ነው።
TMP – 06/02/2018
ፎቶ ክሬዲት: ሱሳን ፊልቸር/ Shutterstock.com / አይዲ: 1277326699
ፎቶ ካፕሽን: ግሬትስቶን, ከንት, ታላቅዋ ብሪታይን- ደሰምበር 31 2018. የወሰን ፖሊስና የምርመራ የጸጥታ ሀይል ያገኙት ትንሽ ጀልባ ይታያል።
ፅሑፉን ያካፍሉ