ኢትዮጵያና ኬንያ ሕገ ወጥ ስደትን ለመከላከል በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ኤርትራውያን ስደተንች ታሰሩ

ከመጋቢት እስከ ሰኔ 2019 .. ባሉት ወራት የኬንያ ባለስልጣኖች ያለ ህጋዊ ማስረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ ለመግባት የሞኮሩት 55 ኤርትራውያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር አዋለ፡፡

በቅርቡ በሰኔ 4 በተካሄደው እስር ከኢትዮጵያ ወደ ናይሮቢ  በመጓዝ ላይ  በነበሩ ሶስት ኤርትራውያን ሴቶች ነው፡፡  ስደተኞቹ ሴቶች ጉዞኣቸው ወላጆቻቸውን ወደ ሚኖሩበት ኡጋንዳ መኖሩን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡

በዚህ አመት ሌሎች 44 ኤርትራውያን 17 ሴቶችን ጨምሮ በግንቦት ወር የመጀመርያዎቹ ሶስት ሳምንታት ለእስር ተዳርጓል፡፡ስድተንኞች ኢትዮጵያንና ኬንያን በሚያዋስነው በሞያሌ በኩል ለመሻገር ሲሞክሩ ተይዘዋል፡፡ በሕገ ወጡ የሰው ልጅ ዝውውሩ ላይ እጃቸው አለበት የተባሉ አራት ኬንያውያን ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ባለፈው መስከረም የተጀመረው ለአጭር ግዜ የቆየው የኤርትራና የኢትየጵያ ድንበር መክፈት በአስር ሽዎች የሚገመቱ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ አድርገዋል፡፡አሁን ደግሞ ብዙ ኤርትራውያን በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር በኩል ወደ ኡጋንዳ እና ወደ ደቡብ በኩል ለመሰደድ እየሞኮሩ ናቸው፡፡

በአሁኑ ግዜ ያለው ሊብያ የሱዳን አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ አውሮጰ ለመሄድ የነበራቸውን እቅድ በመተው ለስደተኞች የተመቹ ናቸው ብለው በሚገምትዋቸው አገሮች እንደነ ኡጋንዳ  ወደ መሳሰሉት ለመሄድ በማቀድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ  የኢትዮኬንያ መንገድ  በሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ቀለበት በመገኘቱ ለብዙ ኤርትራውያን ለመሻገር እጅግ አስቸጋሪ ሆነዋል፡፡ ለምሳሌ በህዳር ወር 2019 ..  የኬንያ ባለስልጣኖች በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ የገቡት ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ናቸው በሚል ጥርጣረ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጋለች፡፡

ኬንያና ኢትዮጵያ የጋራ ድንበራቸውን አያያዝ ለማጠናከርና  ሕገ ወጥ ስደትን ለመግታት  በጋራ እየሰሩ ናቸው፡፡  በዚህ አመት ሚያዝያ  ወር ላይ የተባበሩት መንግስታት የእድገት ፕሮግራም ከአፍሪካ በየነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን በመሆን የአከባቢው ስደትን ለመግታት በኢትዮኬንያ ድንበር የመጀመርያው የመስክ / ቤት ከፍተዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ /ቤት 900,000 በላይ ከነዚህም 235,000 የሚሆኑት የተመዘገቡ ስደተኞች በኢትዮጵያና ኬንያ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

TMP – 27/06/2019

ፎቶ : አዲሶርን ቼይስን/ ሹተርስቶክ

በሕገ ወጥ መንገድ የሚሰደዱ ኤርትራውያን ስደተኞች በኬንያ ባለስልጣኖች ይያዛሉ፡፡