የነብስ አድን ኦፕሬሽን በሜዲትራንያን ባህር እንደገና ተጀመረ
ኤስ.ኦ.ኤስ ሜዲተራንያንና ድንበር የለሽ ሃኪሞች የተባሉት አለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፤ በሜዲትራንያን ባህር የሚከሰተው የህገ ወጥ ስድተኞች ነብስ አድን ስራ እንደገና መጀመራቸው አስታወቁ። እነዚህ ድርጅቶች የነብስ አድን ስራውን እንደገና የጀመሩት ላለፉት 7 ወራት ስራውን አቋርጠው ከቆዩ በኋላ ነው። በዚህም መሰረት አዲስቱ ኦሻም ቪክንግ (Ocean Viking ) የተባለች ያሳማሯት የነብስ አድን ጀልባ በአሁኑ ግዜ በባህሩ ላይ በተጠንቀቅ እየተንቀሳቀሰች ነው።
ግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ የነብስ አድን ስራው ሊያቋርጡ የተገደዱት፤ ስራው ከቀጠለ ሕገ ወጥ ስድተኞች ይበረታታሉ በማለት በተለይም የጣልያንና የማልታ መንግስታት ባሳደሩባቸው ተፅእኖ ነበር። ይሁን እንጂ ክልከላው የሕገ ወጥ ስድተኞች ፍልሰትና ሞት እንዳልቀነሰና ይልቅ በማይረቡ ጀልባዎች የተደገፈ ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደ ሰሜን አፍሪካ የባህር ዳርቻ የማራገፍ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አድርጓል።
በድንበር የለሽ ሃኪሞች የፍለጋና ነብስ አድን ቡዱን መሪ ሳም ቱሩነር እንደሚሉት” የአውሮፓ መንግስታት በጉዳዩ ላይ ሃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት እስከቻሉ ድረስ ፤ የሕገ ወጥ ፍልሰትም በሊብያ በኩል እስከቀጠለ ድረስ፤ በሜዲትራንያን ባህር ላይ የነብስ አድን ጀልባዎች ማዘጋጀት የግድ ይላል” ብለዋል።
የሁለቱም ግበረ ሰናይ ድርጅቶች ንብረት የሆነችው ዚ አኩረስ የተባለች መርከብ ፤ ኦሸን ቪኪንግ በተባለች አዲስና ዘመናዊ መርከብ ተቀይራለች። መርከብዋ ከነሃሰ 2/ 2019 በሜዲትራንያን ባህር እንቅስቃሴዋን የጀመረችው ከአውሮፓ መንግስታት ምንም ድጋፍ ሳይደረግላት ነው።
ኤስ. ኦ .ኤ ሜዲትራንያን የኦፕረሽን ዳይረክተር ፍሮዴሪክ ፔናርድ፤ ከእስፓንሽ አለም አቀፍ ዜና ወኪል ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለፁት” በሜድትራንያን ባህር ሰዎች እንዳይሞቱ ላለፉት 3 አመታት ከአውሮፓ መንግስታት ጋር መላ ፍለጋ ብዙ ያልተሳካ ውይይት አድርገናል። ችግሩ የጣልያንና የማልታ ብቻ ኣይደለም። የአውሮፓ መንግስታት በአጠቃላይ ነው።” ብለዋል።
በሊብያ እርስ በርስ ውግያና በሜዲትራንያን ባህር በርካታ ስድተኞች ተቀርቅረው በሚገኙበት ባህር ላይ የሚደርሰው ጥፋት እንደገና የነብስ አድን ስራው እንደገና እንዲጀምር ጎተጎቱት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወኪሎች ናቸው።
የሜዲትራንያን ባህር ወሽመጥ፤ በአለማችን ለህገ ወጥ ስድተኞች እጅግ አደገኛ የሞት ቀጠና ተብለው ከሚታወቁ አንዱ መስመር ነው። እንደ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ሪፖርት ከሆነ፤ በዚህ አመት ከጥር እስከ ነሃሴ ወር ብቻ በዚህ መስመር 700 ህገ ወጥ ስደተኞች ህይወት አልፏል።
TMP – 09/08/2019
ፎቶ፡ በ ኢልደር ኑርኮቨች
ፎቶ ክረዲት ፤ ከታሐሳስ 2018 እ.ኤ.አ ወዲህ ሜዲትራንያን ባህር ላይ በቂ የነብስ አድን ጥረቶች አልነበሩም
ፅሑፉን ያካፍሉ