በሊብያ የባህር ጠረፍ አከባቢ የአደጋ መድን ማተርያል እና ሁለት በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎችን ጎንለጎን ተገኙ!

ጁላይ 17 ላይ ከሊብያ ባሀር ጠረፍ በ150 ኪ.ሜ ርቀት   የጀልባ የአደጋ መድን ማተርያል እና የአንድ ሴት እንዲሁም የአንድ ወጣት ወንድ በሞት አፋፍ ላይ   ተንሳፍፈው ተገኝተዋል።  

የ40 ዐመት ዕድሜ ያላቸው ካሜሮናዊ ሴት “ፕሮአክቲቭ ኦፕን አርምስ” በተላው የስፔናዊያን የምግባረ ሰናይ ተቋም አማካኝነት ተገኝተው ፎቶአቸው እና ቪድዮዎችን በሶሻል ሚድያ በመሰራጨቱ ምክንያት  በመላው አውሮፓ ቁጭትን ቀስቅሰዋል።

ይህ ሁኔታ ከአጋጠመ ከአራት ቀናት በኋላ እነዚህ በሞት እና ህይወት መካከል ያሉ ሰዎች  ወደ ስፔን ማሎርካ ደሴት ደርሰው ካሜሮናዊትዋ ሴት የህክምና እርዳታ እንዲሁም አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ ተደርጎላታል።

ይህ የምግባረ ሰናይ ተቋም ጣልያን ፊት ከነሳችው በኋላ   ስደተኞቹ ወደ ስፔን የወሰዱበት ምክንያት ስያስረዱ፤ የጣልያን የመንግስት ሀላፊዎች ሴትዮዋ ብቻ ካልሆነ ሁለቱም በጉዳት ላይ ያሉ ስደተኞች አንቀበልም በማለታቸው ምክንያት ነው። ተቋሙ እንዳለው ይሄንን ውሳኔ የወሰነበት ምክንያት “የሴትዮዋ ሙሉ ድህንነት እና ነፃነት ታሳቢ በማድረግ እና ጣልያን ላይ ከተውናት በጣልያን ባህር አከባቢ ሊደርሳት ስለሚችል ችግር በማሰብ ነው።”

ሜትሮ ኒዊስ ፔፐር ላይ የወጣውን ዳታ በመጥቀስ  የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ቃል አቀባይ የሆነውን አዩብ ቃሲም እንደሚለው ከሆነ ጁላይ 16 ላይ 34 ሴቶች እና ዘጠኝ ህፃናት የሚገኙባቸው 158 ስደተኞችን ጭና ልትጓዝ የነበረችውን ጀልባ መልሰዋል። ቃል አቀባዩ እነዚህ ከጥፋት የዳኑ ሰዎች እንዴትለመዳን እንደቻሉ ሳይገልፁ ቀርተዋል።

የ “ፕሮአክቲቭ ኦፕን አርምስ” ዳይሬክተር የሆነውን ኦስካር ካምፕስ ለሮይተርስ እንደገለፀው እነዚህ ከሞት የቀሩት ሰዎች የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ጀልባዋ ሲመልሱ ጊዜ አንመለስም በማለታቸው ምክንያት ጀልባዋ በመመታትዋ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል።    

 ዳይሬክተሩ የጣልያን የስደተኞች ፖሊሲ መሰረት በማድረግ  አያይዘው እንዳሉት የዚህ ችግር ምንጭ ወደ ጣልያኑ የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ያያይዙታል። ካምፕ እንደሚሉት “የዚህ ወንጀል ተጠያቂ የማቲው ሳሊቪኒ ፖሊሲ ነው።” ብለዋል።  

ካምፕ በቲዊተር ገፃቸው በቪድዮ እንደገለፁት  “ይህ ሊብያ ራስዋን የቻለች ስርዐተ መስንግስት፣ መንግስት እና ድህንነትዋ የተጠበቀ ሀገር በመሆንዋ ከሷ ጋር የሚደረግ ወተሃደራዊ ዲፕሎማሲ ያስከተለው  መዐት ነው።”

ሳሊቪኒ ለዚህ በሰጡት ምላሽ ደግማ ለሀገራቸው የሚሰጥ ማነኛውም ሂስ የሚመሰክረው  የሚከተሉትን ፖሊሲ ትክክለኛነትን ነው። “ከውጫዊ የምግባረ ሰናይ ድርጅት የሚፈበረክ ውሸት እና የሚሰነዘሩ ስድቦች የምያሳዩን  ልክ መሆናችንን ነው። ይሄም ብዙ ስደተኞች አለመቀበልን የምያሳየው የሞት ቅነሳን እና ስደትን ምክንያት እያደረጉ የሚሰሩ ሴራዎችን ነው።” ብለዋል ሳሊቪኒ ፌስቡክ ገፃቸው ላይ በለጠፉት ፅሁፍ።  

ካምፕስ  ይሄንን ሁነት ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ ፕሬስ ኮንፈረንስ ላይ እንደገለፁት ድርጅታቸው በተለይ በሊብያ የባህረር ጠረፍ ጠባቂዎች እና በንግድ ጀልባዎች ላይ ያላቸው ቅሬታ ገልፀዋል።  ክስ እና አቤቱታም አቅርበዋል።

“እኛ  በሰው ግድያ ወንጀል የትራይዴስ ካፕቴኑ እንከሳለን። እንዲሁም የሊብያዋ ፓትሮል ካፕቴን የሆነውን ሰውዬም እንከሳለን።” ብለዋል እንደ ሮይተርስ ዘገባ።   

“ፕሮአክቲቭ ኦፕን አርምስ” የምግባረ ሰናይ ተቋም ሲሆን     አሁንም በሜዲትራንያን ባህር ላይ ጥናት እያደረገ ያለ ተቋም ነው።  

TMP – 12/08/2018