በጣልያን ጎጅያ ያሉ ስደተኞች ያሉበት የኑሮ ሁኔታ እየከፋ ነው ተባለ

እንደ የጣልያን የሀኪሞች የግብረ ሰናይ ተግባር ተቋም (MEDU) አገላለፅ ከሆነ በደቡባዊ የጣልያን ክፍል በጎጅያ የሚገኙ ስደተኞች ያሉበት የኑሮ ሁኔታ እየከፋ ነው።

ተቋሙ  ፍትሀዊ መሬት፡  የጉጅያ ታሮኖ በእርሻ ላይ ያሉ ስደተኞች   የኑሮ እና የስራ ሁኔታ በተመለከተ የቀረበ አምስተኛ ሪፖርት  , በሚል ርእስ ያዛጋጀው ሪፖርት እንደምያመለክተው ወደ 2,000 የሚጠጉ ወጣት ከአፍሪካ የመጡ ስደተኞች በእርሻ ስራ ላይ የጉልበት ብዝበዛ እየደረሰባቸው  ይገኛል።

ታላቁ የፒያና ጉጂዮ ቱራኖ የእርሻ ቦታ በእነዚህ ስደተኞች ጫንቃ ላይ ወድቀዋል።  ስደተኞቹ የሚያዝበት አገባብም አንድ በስልጣኔ ማማ ላይ አለሁ ከሚል ሀገር እና ዜጎችን መሰረታዊ መብታቸው ይጠብቃል ተብሎ ከሚታሰብ ሀገር የማይጠበቅ ነው።ብለዋል ተቋሙ በማርች መጀመርያ አከባቢ ባወጣው መግለጫ። 

በየአመቱ በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች እንደ እነ ብሪንካፋሶ፣ ማሊ፣ ጋና፣ አይቬሪኮስት እና ሴኔጋል ከመሳሰሉ ሀገራት በዚህ በኩል ወደ ጣልያን ይገባሉ። የአሁኑ ሪፖርት እንደሚለውየጉልበት ብዝበዛ፣ ማባረር እና ሌሎች ተስፋ አስቆራጭ ግፎች ይፈፀምባቸዋል።ሪፖርቱ አያይዞ እንደገለፀውስደተኞቹ በስራ ቦታው ከፍተኛ የሆነ ብዝበዛ፣ በጣም አስከፊ የንፅህና ችግር፣ መጥፎ የኑሮ ሁኔታ፣ ህገ ወጥነት እና የህክምና እርዳታ ለማግኘት የማያስችል ችግር ውስጥ ናቸው።ብለዋል።

ይህ ተቋም የህክምና እርዳታ ከሰጣቸው 438 በሽተኞች 90% በህገ ወጥ መንገድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ ከእነዚህ ሰዎች  ሁለት ሶስተኛዎቹ ደግሞ በቀን 25 ዩሮ ይከፈላቸዋል። ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው እነዚህ ላለፉት ሶስት ወራት በስራ ላይ የነበሩ ስደተኞች ከሶስተኛ እጅ ያነሰ ቁጥር ብቻ ናቸው ውል ተዋውለው በመስራት ላይ ያሉ።

አብዛኞቹ የበሽታ አይነቶች በመጠልያ እጦት እና በፅዳት ምክንያት የመጡ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል። በገጠሩ ክፍል እስከ 40 የሚደርሱ ስደተኞች በአንድ ሩም ውስጥ ታጉረው ይኖራሉ።

የቻሪቲ ተቋሙ በአጋጠመ አደጋ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ አራት ሰዎች አሳዛኝ በሆነ መልኩ በተንቀሳቃሽ ድንኳኖች ውስጥ ወይም መንግስት በሰጣቸው መጠልያ ውስጥ በእሳት ተቃጥለው ሞተዋል።ብለዋል።

በመጀመርያ አከባቢ ባለስልጣናቱ ስደተኞች ሰብአዊነት በሌለው መልኩ ሲሰሩባቸው የነበሩ የእርሻ ቦታዎች ላይ የነበሩ ካምፖች አፈራርሰዋል።  ሪፖርቱ በቅርቡ ማርች 6 ቀን ላይ የተደረገ ፍተሻ ውጤት ትክክል አልነበረም። ምክንያቱም አማራጭ ሳይያዝ  በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ ሌሎች ካምፖች ተወስደዋል። ሌሎችም በራሳቸው ጥረት  ቦታውን ለቀዋል።ብለዋል።

TMP – 10/06/2019

Photo credit: ኤምኢዲዩ (MEDU)

Photo caption: በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች የእርሻ ስራ የሚሰሩበት በደቡባዊ የጣልያን ክፍል የሚገኝ የሳን ፈርዲዳንዶ ካምፕ