ሊብያ: በእስር በየቶች የሚገን ስድተኞች በአየር ድብደባ ተገደሉ

በሓምሌ 3 .. በሊብያ በሚገኝ የስደተኞች እስር ቤት ላይ በተካሄደው የአየር ድብደባ ቢያንስ 53 ስደተኞች ሲሞቱ 130 በላይ ደግሞ ቆስለዋል።

በትሪፖሊ አቅራብያ የሚገኘው የታጁራ እስር ቤት 600 በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች የሚገኙበት ሲሆን አብዛኛዎቹ ከኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ሶማሊያ የመጡ ናቸው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥቃቱ በገለልተኛ እንዲመረመርና የጦር ወንጀል ሆኖ ሊቆጠር እንደሚችል አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት የስድተኞች ኤጀንሲ (UNCHR) እና የአለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ /ቤት (IOM)   ጥቃቱ በጋራ ያወገዙት ሲሆን ሁለቱ ድርጅቶቻችን ይህንና ሌላ በሲቪሎች ህይወት ላይ የሚደረግ ጥቃት በፅኑ ያወግዛሉ። በስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ የሚደረግ እስር  በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን በማለት ተናግረዋል።

ቢያንስ 6000 የሚሆኑ ጥገኝነት ጥያቂዎችና ስደተኞች ያለ በቂ የጤና እንክብካቤ ምግብና ንፁህ ውሃ በአስጊ ሁኔታ በሊብያ እስር ቤቶች ታጉረው ይገኛሉ። ከመስከረም 2018 .. ጀምሮ በቂ ሕክምና ባለማግኘታቸው በቀላሉ ሊታከሙ በሚችሉ ህመሞች ሳብያ 20 እስረኞች ህይወታቸው አልፈዋል። ሌሎችም ተይዘው በግድ በውግያ እንዲሳተፉ ተደርጓል።

በሊብያ የድንበር የለሽ ሓኪሞች አስተባባሪ ፕሪንስ አልፋኒ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች ከሊብያ በአፋጣኝ እንዲወጡ ጥሪ ያቀረበየ ሲሆን አሁን የሚፈለገው ባዶ ውግዘት ሳይሆን በሊብያ እስር ቤቶች ውስጥ  ተይዘው የሚገኙ ሁሉም ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች በአስቸኳይ እንዲወጡ ማድረግ ነው። ብለዋል

ከጥር እስከ ግንቦት 2019 ... ጀምሮ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ /ቤት ።በተደገረው እርዳታ 1000  የሚበልጡ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች ከሊብያ ወጥተው በሌላ እንዲኖሩ ተደርጓል። ይሁን እንጂ እስከ አሁን ድረስ 3300 የሚሆኑ ስደተኞች አደገኛ ተብሎ በሚታሰብ ቦታ  በሊብያ በተለያዩ እስር ቤቶች እንደሚገኙ አለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ አስታውቋል።

በሊብያ በመካሄድ ላይ ያለው ግጭትና የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ስደተኞች በባህር ወደ አውሮጳ የሚያደርጉትን ጉዞ ክልክላ ጋር ተደምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞች መውጫ አጥቷል። 2019 ...  3000 በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች በባህር የሚያደርጉት የነበረው ጉዞ ተሰናክሎ ወደ ሊብያ እንዲመለሱ ተደርጓል። ጣልያን የስድተኞች ጃልባዎች ከሊብያ ወደ ጣልያን ወደቦች እንዲገቡ በመከልከልዋ ደህንነታቸው ባልተጠበቀ ጃልባዎች ከሊብያ ለማምለጥ የቻሉት ስድተኞች ለመገልበጥና በባህር ላይ ለመጥፋት አደጋ የተጋለጡ ናቸው። በሰኔ 29 ...  የጀርሞን የስደተኞች አድን መርከብ ካፕቴን 42 ስደተኞች በመያዝ ከሊብያ ወደ ጣልያን የባህር  ክልል በሕገ ወጥ መንገድ በመግባቱ ታስሮ ከዚያም እንዲለቀቅ ተደርጓል።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ /ቤት በሊብያ የሚደረገው የስደተኞች የጥገኝነት ጠያቂዎች እስር እንዲያበቃ ጥሪውን አስተላልፈዏል።

TMP – 04/07/2019

ፎቶ: @penlibya/Twitter