የኖርወይ መንግስት፤ ኤርትራ ውስጥ ለሚደረገው የብሄራዊ ውትድርና በሚደግፉ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ዳግም ማጣራት እንደሚያካሂድ ገለፀ

የኖርወይ መንግስት፤ 150 ኤርትራውያን ስደተኞች በአገሩ ውስጥ ያቀረቡት የጥግተኝነት ጥያቄ የውሸት እንዳይሆን ደግሜ አጣራለሁ አለ። የኖርወይ መንግስት ይህንን ማጣራት ለማድረግ የወሰነው፤ ጥግተኝነት ከጠየቁት በርካታ ኤርትራውያን መካከል፤ አስሎ በተካሄደው የኤርትራ ብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት በሚደግፉ ስብሰባ ላይ መገኘታቸው በማረጋገጡ ነው።

ይህ ባለፈው ነሀሴ ወር በአስሎ የተደረገው የኤትራውያን ስብሰባ፤ ኤርትራ የወጣቶች የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት የተጀመረበት 25 ዓመት ለማክበር ነበር። በበአሉ ላይ የፕረዚዳንት ኢሰያስ የቅርብ አማካሪ የሆነው የማነ ገብርኣብ ተገኝቶ ነበር። ተሳታፊዎችም መድረኩን በሚሊተሪ  ሙሉ ልብስና በወታደራዊ ቋንቋ አጅበው አድምቀውት ነበር።

የኖርወይ የፍትህ ክፍል( ዲፓርትመንት) ሁኔታውን እስመልክቶ እንደገለፀው፤ማነኛውም ጥግተኝነት ተፈቆደለት የነበረ ኤርትራዊ፤ ቀደም ሲል የግዴታ የውትድርና አገልግሎት ሄዶ በነበረ ወይም አሁን በአገሪቱ ለሚደረጉ ተመሳሳይ አፈሳዎች መንግስቱን በመደገፍ የተንቀሳቀሰ ከሆነ፤ የተሰጠው የጥግተኝነት ፍቃድ ተመልሶ ይጣራልብሏል።

 ‘ ማነኛውም ስደተኛ በእሱ በራሱ ላይ ይደርስበት የነበረውን ቅጣት ፈርቶ የሸሸበትን የባለስልጣናት እርምጃ፤ ከተሰደደ በኋላ ድጋፉን የሚሰጥ ከሆነ የጥግተኝነቱ ጥያቄ ተመልሶ መጠራት ይገባዋል። ‘  ሲል የፍትህ ዲፓርትመንቱ በመስከረም 6 ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

የፍትህ ዲፓርትመንቱ ከዚህ ባሻገር፤ በአርትራ ውስጥ ለሚደረገው የአስገዳጅ የውትድርና አፈሳ ሂደቱ ደግፈው በስብሰባው የተሳተፉቱን ኤርትራውያን ስደተኞች ጉዳይ እንዲያጣራ ለስደተኞች ዲፓርትመንት ትእዛዝ መስጠቱን ታውቋል። የስደተኞች ዲፓርትመንት ከሚያደርገው ጥናት በኋላ፤ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ያለው መንፈስ ተጣርቶ መኖርያ ፍቃድ የመስጠትና የመከልከል ተግባር ይወስናል ብሏል።

ማነኛውም ህጋዊ ጥበቃ የሚያስፈልገውና ቀደም ሲል ጥግተኝነት የተፈቀደለት ስድተኛ በአሁኑ ሂደት እንደሚጣራ የገለፀው የኖርወይ መንግስት፤ ህጋዊ ሆነው የተገኙ ስደተኞች የመኖርያ ፍቃዳቸው ታድሶ  አዲስ እንደሚሰጣቸው አስታውቋል።

እንደሚታወቀው 22,000.00 ( ሃያ ሁለት ) ገደማ ኤርትራውያን ስደተኞች በአሁኑ ጊዜ በኖርወይ አገር ይኖራሉ። ከነዚህ አብዛኛዎቹ 2001 የኤርትራ አስገዳጅ የውትድርና አፈሳን በመሸሽ የገቡ ናቸው።

TMP 25/03/2019

ፎቶ ክሬዲት፤ህይወት በኖርወይ

ፎተፐ ካፕሽን የኖርወይ ስደተኞች አገልግሎት ክፍል