አንድ ሶማልያዊ ስደተኛ በሊብያ የስደተኞች ማቆያ ካምፕ ውስጥ ራሱን አጠፋ
ሶማልያዊ የ28 ዕድሜው ወጣት ራሱን እሳት ውስጥ በመክተት ራሱን አጥፍተዋል። ይህ የሆነው ኦክተበር 24/2018 ሲሆን በሊብያ ታሪቅ አልሲካ በተባለ ትሪፖሊ ውስጥ በሚገኘው የስደተኞች ማቆያ ማእከል ውስጥ መሆኑ ሌሎች የማእከሉ አባላት እና አይኦኤም ገልፀዋል።
አልጀዚራ ካነጋገራቸው በማቆያ ማእከሉ የነበሩ ስደተኞች እንደገለፁት ይህ አብዱልኣዚዝ የተባለው ስደተኛ ከጀነሬተር ጋዝ በመውሰድ እሳት ለኩሶ ራሱን ማቃጠል ችለዋል። ይህ የሆነው የኤንኤችሲኣር ሀላፊዎች ሊብያን በጎበኙበት ወቅት አብደልዓዚዝ ከሊብያ የመውጣት ተስፋ እንደሌለው በተደጋጋሚ ከነገሩት በኋላ ተስፋ በመቁረጡ ምክንያት ነው ተብለዋል።
ሙሉበሙሉ ተስፋ ቆርጦ ስለነበር ነው ራሱን ያጠፋው ተብለዋል።
የዩኤንኤችሲአር አባላት በበኩላቸው የአብዱልዓዚዝ ራስን ማጥፋት ከጉብኝታቸው ጋር ምንም ንኪኪ እንደሌለው ይገልፃሉ። ዓብደልዓዚዝ በመጪው ወር ወደ ኒጀር ለመጓዝ ዕቅድ የነበረው ሲሆን አሁን ራሱን ለማጥፋት ያስወሰነው ምክንያት ግልፅ አይደለም ይላሉ። እንደ አይኦኤም ገለፃ ዓብደልዓዚዝ በትሪፖሊ ሆስፒታል ህክምናዊ ክትትል ሲደረግለት የቆየ ቢሆንም ህይወቱ ሊተርፍ አልቻለም።
አብዛኛዎቹ በስደተኞች ማቆያ ማእከሉ ያሉ ስደተኞች ወደ ሊብያ በማለፍ ላይ እያሉ በሊብያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች አማካኝነት ባህር ላይ የተያዙ ናቸው። ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ዩኤንኤችሲኣር ሴፕተምበር 2018 ላይ ያወጣውን ስደተኞች ወደ የማትመች ሊብያ የመመለስ ተግባር ያወግዛሉ።
ትሪቅ አልሲካ ብዙ ግፍ የሚፈፀምበት በመሆኑ ምክንያት መጥፎ ከሚባሉ የስደተኞች ማቆያ ማእከላት አንዱ መሆኑ በብዙ ስደተኞች ይነገርለታል። ከ400 በላይ ስደተኞች የያዘ ይህ የስደተኞች ማእከል አብዛኛዎቹ በጨለማ ውስጥ ይኖራሉ።
ለአልጀዚራ ቃሉ የሰጠ አንድ ቀደም ብሎ በማእከሉ የነበረ ስደተኛ “ከሲኦል የማይተናነስ ነው!” ይላል። ስደተኞቹ በዋናነት ከኤርትራ እና ሶማልያ የመጡ ቢሆኑም ኢትዮጵያውያን፣ ሱዳናውያን፣ የመናውያን፣ ሶርያውያን እና ደቡብ ሱዳናውያንም ይገኙባቸዋል።
በስደተኞች ማቆያ ማእከሉ እስከ 30 የሚሆኑ ባለ ትዳር ጥንዶች አሉ። እነዚህ ጥንዶች በሳምንት አንዴ ለ10 ደቂቃ ብቻ ይገናኛሉ። ይህ አሁን ራሱን ያጠፋ አብደልዓዚዝ የተባለ ስደተኛም ባለ ትዳር ነበር። ሚስቱ አሁንም በማእከሉ ትገኛለች።
ስደተኞች በአስከፊው የስደት ጉዞአቸው ላይ የሚገጥሙ ፈተናዎች በብዙ መልኩ ይገለፃሉ። አንድ ለአልጀዚራ ቃሉ የሰጡ ስደተኛ እንዳለው በስደተኞች ማእከሉ ስደተኞች መጥፎ ነገር ማሰብ እና ሽንት ቤት ውስጥ አስነዋሪ ተግባራት ላይም መሳተፍ ጀምረዋል።
“እስርቤት ለሰው አእምሮ አደገኛ ነገር ነው። ለረጅም ጊዜ በእስር ስትቆይ እንደ እብድ ያደርግሃል። አልያም ራስን ታጠፋለህ። ይህ እስርቤትም በጣም በጣም አደገኛ ነው።” ብለዋል።
ቀደም ብሎ በማእከሉ የነበረ ሌላ ስደተኛ እንዳለው የማእከሉ ዘበኞች ለህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች አሳልፈው በመስጠት እንደሚሸጥዋቸው ይናገራል። “እነዚህ ሊብያውያን እኛን ልክ እንደ ኢንዳስትሪ ነው የምያስቡን።” ብለዋል።
እንደ ዩኤንኤችሲአር ገለፃ እስካሁን 5,400 ስደተኞችን በሊብያ ታጉረው እንደኖሩ ይገለፃል። የስደተኞች ኤጀንሲ ስደተኞችን የምያቆዩ ሃገራት ፍለጋ ላይ ብዙ ግዜ እንዳጠፋም ይነገራል።
ፎቶ ካብፕሽን፦ ከሚዲትራንያን ባህር በሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች አማካኝነት የሚመለሱ ስደተኞች በመብዛታቸው ምክንያት በስደተኛ ማቆያ ማእከሉ ተጨናንቀው ይታያሉ።
ፎቶ ክሬዲት: ኤምኤስኤፍ/ትዊተር
TMP – 11/12/2018
ፅሑፉን ያካፍሉ