ዶኩሜንት በሌሎች ስደተኞች ላይ የሚፈጠር ከፍተኛ የጭንቀት፣ የድብርትና በድህረ አደጋ የሚፈጠር የአእምሮ መዛባት በስዊድን
በቅርብ በስዊድን አገር በሚኖሩ ስደተኞች ላይ የተደረጉት ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከአስር ዶኩሜንት አልባ ስደተኞች መካከል ሰባቱ በከፍተኛ ጭንቀትና ድብርት ችግሮች ይሰቃያሉ።
በስዊድን ጉተምበርግ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች 2014-2016 እ.ኤ.አ በተደረገው በዚሁ ጥናት ላይ፤ ተመራማሪዎች ስዊድን ለሚኖሩ ስደተኞች የጭንቀት ፣ ድብርት ወይም የድህረ አደጋ የአእምሮ መዛባት ችግር ካለባቸው ጠይቀዋቸዋል።
ተመራማሪዎች ፤ በጥናታቸው በስዊድን ከተሞች (ስቶኮልም ፣ ጉተምበርግና ማሊሞ) በሚኖሩ 88 ወጣት ወንድና ሴት ዶኩሜንት አልባ ስደተኞችን ለመዳሰስ ሞክረዋል። 15% (በመቶ) የጥናቱ ናሙና የተደረጉት አፍሪካውያን ስደተኞች ነበሩ።
የምርምሩ ናሙና የሆኑት ስደተኞች ፤ በተለያዩ ምክንያቶች እሰካሁን የሌላቸው ናቸው። ገሚሶቹ የጥገኝነት ጥያቂዎች ተቀባይነት ያጣ ነው ፣ አንዳንዳቹ ደግሞ መጀመርያ ሲገቡ አስፈላጊው ማመልከቻ ያላቀረቡ ወይም የቪዛቸው ቀን ያለፈበት ናቸው። ከናሙናዎቹ 1/3 ኛ ለሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ህጋዊ ዶኩሜንት ሳይኖራቸው የሚቀመጡ ናቸው።
ውጤቱ እንደሚያመላክተው ፣ እነዚያ ከ25-39 የእድሜ ደረጃ ያሉት ዶኩሜንት አልባ ስደተኞች በእድሜ ከነሱ ከሚያንሱ ወጣቶች በላይ ጭንቀትና ድብርት አላቸው። ከ40 ዓመት በላይ ያሉት ደግሞ ከሁሉም በላይ በድብርት ጭንቀት ይጠናወታቸዋል ብሏል። ቢያንስ 60% ስደተኞቹ በድህረ አደጋ የሚፈጠር የአእምሮ መዛባት ችግር እንደለባቸው ሲናገሩ ፤ ግማሾቹ ደግሞ እንደሚራቡ ገልፀዋል።
የምርምር ናሙና የሆኑት ስድተኞች በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን በሲዊድን የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸው ናቸው። ገሚሶቹ የጥግተኝነት ጥያቂቸው ተቀባይነት ያጣ ነው። አንዳንደቹ ደግሞ መጀመርያ ሲገቡ አስፈላጊው ማመልከቻ ያላቀረቡ ወይም የቪዛቸው ቀን ያለፈበት ናቸው። ከናሙናዎች 1/3ኛ ከሁለት አመትና ከዚያ በላይ ሃጋዊ ዶክመንት ሳይኖራቸው የሚቀመጡ ናቸው።
ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያጣ ዶኩሜንት አልባ ስደተኞች በስዊድን ለመቆየት ይመርጣሉ። ምክንያቱም ከአራት ዓመት በኋላ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን በአዲስ መልክ ማቅረብ ስለሚችሉ ነው። ይሁንና ብዙዎች ደግሞ ፤ በመሀል ላይ ህገወጥ ናችሁ በሚል ከስዊድን የመባረር እጣ ሊደርስባቸው ይችላል። በ2015 እ.ኤ.አ ብቻ ከ160 ሺ በላይ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ወደ ስዊድን ገብቷል።
TMP 25/03/2019
ፎቶ ክረዲት፣ ኦቪ ኖርዳስትሮም
ፎቶ ካፕሽን ፤ ዶኩሜንት አልባ የሆኑ ስደተኞች በስዊድን ውስጥ መሰረታዊ አቅርቦት በቀላሉ አያገኙም።
ፅሑፉን ያካፍሉ