(AMHARIC) The Migrant Project Data Protection Policy

(AMH)የስደተኞች ፕሮጀክት መረጃ ጥበቃ ፖሊሲ

ዝርዝሮችዎን ከስደተኛ ፕሮጀክት ጋር በፌስቡክ ስለማካፈል

ይህ የግላዊነት ፖሊሲ የስደተኛ ፕሮጄክት (ዘምፖ) በሜታ ቅጽበታዊ ቅጾች በኩል የሚያጋሩትን ማንኛውንም የግል መረጃ እንዴት እንደሚጠቀም እና እንደሚጠብቅ ያስረዳል።

ምን አይነት መረጃ ተሰብስቦ ነው የሚሰራው?

በፌስቡክ/ኢንስታግራም፣ በፈጣን ቅጽ  የሰጡንን ግላዊ መረጃ እንሰበስብ እና እናስኬዳለን። በተለይም ስምዎ ፣ እድሜዎ ፣ ስልክ ቁጥርዎ ፣ የምትኖሩበት አካባቢ እና ራስዎ እንዳሉት በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ያሎት ፍላጎት የመሳሰሉ ናቸው። እንዲሁም ቅጹን ስላስገቡበት ሰዓት እና ቀን እና ቅጹን ስለሚያስገቡበት የገጽ ቋንቋ መረጃ እንሰበስባለን።

መረጃው ከማን ጋር ነው የተጋራው?

የእርስዎን መረጃ የሚጠይቁትን አገልግሎት ለማስተባበር እና ለመምራት ለሚፈልጉ የዘምፖ ሰራተኞች ብቻ እናጋራዋለን (ይህም ስለ ስደት ምክክር) ። ይህ የዘምፖ መረጃ አስተዳዳሪን ፣ የዘምፖ ስደት አማካሪዎችን እና የስደት አማካሪዎች  ተቆጣጣሪዎችን   ያካትታል። መረጃዎን ለሶስተኛ ወገኖች አናጋራም።

መረጃው እንዴት ጥቅም ላይ ይውላል?

የእርስዎን መረጃ የምንጠቀመው እርስዎ ፈቃድ ለሰጡበት ዓላማ ብቻ ነው። በዚህ ሁኔታ ቅጹን ከዝርዝሮችዎ ጋር በማስገባት እርስዎን አግኝተን  ከዘምፖ የስደት  አማካሪ ጋር የነፃ ምክር እንድንሰጥዎት ተስማምተዋል።

መረጃው የት ነው የሚቀመጠው?

መረጃው ደህንነቱ በተጠበቀ የጎግል ሺት ላይ ተከማችቷል አስፈላጊ ለሆኑት ሰዎች ብቻ። በዚህ ቅፅ  ላይ ያለ ሰነድ ባልተፈቀዱ ወገኖች በማንኛውም መንገድ አይታተምም አይገለበጥም።

መረጃው ለምን ያህል ጊዜ ይከማቻል?

መረጃዎ የሚቀመጠው ከእርስዎ ጋር በመመካከር የማማከር ጥያቄዎን እስክንፈታ ድረስ ወይም ጥያቄዎትን በመሰረዝ እርስዎን ማግኘት ስላልቻልን ወይም እርስዎ በስልክም ሆነ በፌስቡክ መመካከር እንደማትፈልጉ እስኪያሳውቁን ነው።

የመረጃዎን ሂደት በተመለከተ ምን መብቶች አሎት?

በማንኛውም ጊዜ በፌስቡክ በኩል በማነጋገር መረጃዎን እንድናስተካክል ወይም እንድንሰርዝ የመጠየቅ መብት አለዎት። እንዲሁም ስለእርስዎ ምን አይነት መረጃ አሁን እንዳከማችን ሊጠይቁን ይችላሉ።