በቱኒዝያ የባህር ጠረፍ ጀልባ በመሰጠምዋ ምክንያት በርካታ ስደተኞች ጠፍቷል
በሐምሌ 4 በቱኒዝያ የባህር ጠረፍ ስደተኞች ይጓዝባት የነበረችውን ጀልባ በመገልበጥዋ ምክንያት ከ80 በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች መጥፋታቸውና መሞታቸው የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
አራት ስደተኞች ለሁለት ቀናት አደጋ በደረሰባት ጀልባ ስብርባሪ ላይ በመጠጋት የቆዩ ሲሆን በመጨረሻ በቱኒዝያ አሳ አጥማጅ ህይወታቸው ድኗል። ከአደጋው የዳኑ ስደተኞች ወደ ስደተኛ መጠልያ ማእከል የተወሰዱ ሲሆን ሆኖም ግን ከአራቱ አንዱ በከፍተኛ የብርድ በሽታ ሳብያ በአካባቢው ሆስፒታል ሞቷል።
“ እኛ አራታችን በእንጨት ላይ ተቀምጠን ማእበሉ እየመታን ነበር። ለሁለት ቀናት እንጭት ቁራጭ ላይ ቁጭ ብለን ነበር። ብዙ ሰዎች ሞቷል። “ በማለት ከአደጋው ከዳኑት ስደተኞች አንዱ ለሮይተርስ ተናግሯል።
ከአደጋው የዳኑ ሰዎች ትንሿ ጀልባ 86 ሰዎች አራት ሴቶችና ሁለት ህፃናትን ጨምሮ ይዛ እንደነበረች ለቱኒዝያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ተናግረዋል።
በዚህ በደረሰው አሳዛኝ ክስተት በማዘን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ፅ/ቤት የሜዲተርያንያን ልዩ ልኡክ ቨንስንት ኮቼተል “ ነባራዊው ሁኔታ እንደዚህ ሊቀጥል አይችልም። ሌላ አማራጭ አጥተው ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም የራሳቸውና የቤተሰቦቻቸውን ህይወት በዚህ አደገኛ ተስፋ የሚያስቆርጥ የጀልባ ጉዞዎች ለአደጋ አይጋለጡም። በጀልባ የሚያደርጉትን ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት እኛ ትርጉም ያላቸው አማራጮች ልናቀርብላቸው ይገባል።” ሲሉ ተናግረዋል።
ይህን አደጋ የተፈፀመው በሊብያ የስድተኞች እስር ቤት በተካሄደው የአየር ላይ ድብደባ ቢያንስ 60 ስድተኞች ከሞትበት ቀን በሃላ ነው።
በሊብያ በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት በአገሪቱ የሚገኙ በሽዎች የሚገመቱ በእስር ቤት ላይ ያሉ ስደተኞች ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ከሊብያ የሚወጡበትን ሁኔታ እንዲፈልጉ እያደረገ ነው። ቡዙ ስደተኞች ከቱኒዝያ ጋር በሚዋሰነው የሊብያ ምዕራባዊ የባህር ጠረፍ በኩል ለማምለጥ እየሞኮሩ ናቸው። በሰኔ ወር ከሊብያ ተነስተው ወደ አውሮጳ ለመድረስ ባደረጉት ሙከራ ጀልባዋ በቱኒዝያ የባህር ጠረፍ በመገልበጥዋ ምክንያት ቢያንስ 65 ስደተኞች ሞተዋል።
ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ባወጣው አዲስ ዘገባ መሰረት ሜዲትሪያንያን አሁንም ቢሆን “የአለም አደገኛ የባህር መተላለፍያ ነው።” በማለት ገልፀዋል። ከጥር እስከ ሰኔ 2019 እ.ኤ.አ በቅርቡ በወጣው የአለም አቀፍ ስደተኞች መረጃ መሰረት ቢያንስ 597 የሚሆኑ ሰዎች ሜዲትራያንያንን ለመሻገር ሲሞክሩ መሞታቸው ያሳያል።
TMP – 10/07/2019
ፎቶ: አናዶሉ ኤጄነሲ ዌበሳይት /ፋይል ፎቶ
የቱኒዝያ የባህር ጠረፍ ጠባቂ በጥበቃ ላይ
ፅሑፉን ያካፍሉ