የአውሮፓ ህብረት ጉባኤ ኣጀንዳ ብስደነኞች ጉዳይ ይሸፈናል
28 የአውሮፓ ህበረት አባል ኣገሮች መሪዎች በኦስትርያ በከተማ ሳልዘበረግ ከመስከረም 19 እሰከ መስከረም 20 በመሰብሰብ ወደ አውሮፓ አገሮች የሚደረግ የስደተኞች ፍሰት የሚቀንሱበት አማራጮች ላይ ተወያዩ፡፡
ወደ አውሮፓ የሚደረግ የስደተኞች ፍሰት ለመቀነስ ከ2015 ጀምሮ በህብረቱ የተለያዩ እርምጅዎች እየተወሰደ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ እንደሚታወቀው በ2015 ከአፍሪቃና ማእከለኛ ምስራቅ አገሮች ከ 1ሚልዮን በላይ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ከገቡ፤ የአህጉሩ በርካታ አገሮች በስደተኞች ጉዳይ የወሰዱት አቋም ሊከፋፈልና በስደተኞች አውሮፓ ላይ ጥላቻ ሊስፋፋ ታይተዋል፡፡ ከዚህ ውጭ የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ከነሊብያና ቱሪኪ በገንዘባዊ ድጋፍ አገሮቹ ድንበራቸው እንዲጠቡቁና ከነሱ የሚነሱ ስደተኛች ለመግታት እንዲገደዱ ስምምነታቸው በፊርማ ማረጋገጣቸው ታውቋል፡፡ ሜድትራንያን ባህር አቋርጠው ወደ አውሮፓ የሚገቡ የስደተኞች ቁጥር እየቀነሰ ነበር፡፡በዚህ አመት ከ100000 /አንድ መቶ ሺ በታች ብቻ ስደተኞች ነሕገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ገብቷል፡፡
እንደ የአውሮፓ ህበረት ተቋም ሕገ ወጥ ፍልሰት ለመግታት የሚደረግ ጥረት፤ ህበረቱ ባለፈው ቅርብ ግዜ ለአባላት ብዛት በፍሮንቴክስ (Frontex) የሚታወቅ አውሮፓዊ የባህርና የምድር ጥበቃ ወደ 10 ሺ ከፍ እንዲል ቢወያዩም፤ እንደ ጣልያን የመሳሰሉ የባህርና የመሬት አከባቢ ያላቸው በመከታተል መሪ ሚና እንዲኖራቸው የመረጡ አገሮች ሕብረቱ እስከ አሁን መረዳዳት አልቻለም፡፡
ከአውሮፓ ህብረት ውጭ ከግብፅ ጋር የሕገ ወጥ ስደት ፍሰት ለመግታት በጋራ ለመስራት እየጣሩ ነው፡፡ የአውሮፓ ህበረት ፕረዚዳንት ዶናልድ ታስኮን ቻንስለር ኦስትርያ ስባስትያን ኩርዝን ከየግብፅ መሪ ዓብደል ፋታሕ ኣልሲሲ በካይሮ ከተማ መስከረም 16 በተገናኙበት ግዜ፤ ግብፅ ሕገ ወጥ ስደትን በመግታት ያስመዘገበችው ድሎች አድንቀዋል፡፡
ህበረቱ ከግብፅ መንግስት ያለው ዝምድና እንዲጠናከር እየሰራ መሆኑን፤ አውሮፓ ህበረት ደግሞ እንደ ግብፅ የመሳሰሉ ሕገ ወጥ ስደትን ለመግታት በሚገባ ሃላፊነታቸው የሚዋጡ ወዳጅነት እንደሚያስፈልጋቸው አንድ የአውሮፓ ህበረት ባለስልጣን መስከረም 18 ለተናገው ቃል ዋቢ በማድረግ ኢዩ ኦስርቨር የሚባል የመረጃ ማእከን ገልፀዋል፡፡
በአውሮፓ ህበረት በዚህ አጋማሽ ኣመት የተነሳ ግብፅ በመሬትዋ ስደተኞች የሚጠለሉበትና እሰከ ሚባረሩ የሚታሰሩበት መጠልያ/ማቆያ/ እንድሰራ የሚል ሃሳብ የግብፅ መንግስት እሰከ አሁን አየተቃወመች መሆንዋ ይታወቃል፡፡
የግብፅ መንግስት ሕገ ወጥ የስደተኞች ፍሰትና የሰዎች ንግድ ለመግታት የተለያዩ እርምጃዎች እንደወሰደች ይታወቃል፡፡ መንግስት አዘዋዋሪዎችና ተዘዋዋሪዎችን በሚገባ የሚቀጣ ሕግ ስለኣወጣችና የድንበር ጥበቃን ስለአጠናከረች ከግብፅ የሚነሳ የሕገ ወጥ ስደት ፍሰት በቅርቡ ወደ ዜሮ ወርዶ ይገኛል፡፡ የተባበሩት መንግስታት መረጃ እንደሚያስታውቀው፤ በ2018 እስከ አሁን ከ30 በታች ብቻ ሕገ ወጥ ስደተኞች ከግብፅ ጫፍ ተነስተው ወደ ጣልያንና ግሪክ እንደገቡ ነው፡፡
ይህ በ2016 መገባደቻ የወጣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀለኛ ሆነው ለተገኙ ወገኖች ከ2796 እስከ 11000 ዶላር የአመሪካ ገንዘብ ቅጣትና እሰከ ዕድሜ ልክ እስራት ለመቅጣት ያስገድዳል፡፡በዚህ ግዜ ከ 58 አገሮች መሆናቸው የሚነገርላቸው 230000 የተመዘገቡ ስደተኞች በግብፅ ይኖራሉ፡፡
TMP – 25/09/2018
ስእል፥ ጆኤል ካሪለት፣ ኣይስቶክ ስደተኞች የጫነ መርከብ በለስቦ ግሪክ እየተጠጋ
ፅሑፉን ያካፍሉ