ጀርመን አውሮጳዊ የሆነ ወጥ የጋራ የጥገኝነት ፖሊሲ እንዲቀረፅ ተማፀነች
የማእከላዊ ባህርን የጋራ ድንበር ወደሚጋራ የአውሮጳ ሃገሮች የሚሄደው የአዲስ ስድተኞች ብዛት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ የአውሮጳ አባል ሃገራት የጋራ የሆነ ወጥ የጥገኝነት ፖሊሲ በአንድነት እንደሚገባ የጀርሞን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስተር ሆርስት ሲሆፈር ተማፅኖ አቅርበዋል። ጀርሞናዊው ሚኒስተር ጨምረው በዚህ ዓይነት እየቀጠለ ያለው ሁኔታ (ክስተት) የአውሮጳ ሕብረት በ2015 እ.ኤ.አ. ያጋጠመውን የስድተኞች ቀውስ ዳግም እንዳይከሰት ስጋታቸው ገልፀዋል።
የአውሮጳ ህብረት የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተሮች በጥቅምት 8 በላግዘንበርግ ተሰብስበው በተለይም በግሪክ ዳግም እያንሳራራ ያለው የስደተኞች ፍልሰት ወደ አውሮጳ ተወያይተዋል።
“ ከአውሮጳ ሕብረት ውጭ ላሉት ሃገራትን ትተን ከተጓዝን አውሮጳዊና የጋራ የሆነና ወጥ የጥገኝነት ፖሊሲ ተግባራዊ ካልሆነም በዚህ ሕብረት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የስደት ቀውስ ዳግም ሊከሰት ከፍተኛ አደጋ እንዳለ አሳስበዋል።“ የጀርሞን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ጥሪ ለጋራ የአውሮጳዊ ሕብረት የጥገኝነት ፖሊሲ ስርዓት የጣልያንና የፈረንሳይ መሪዎች በሮማ ከተማ ተገናኝተው ግልፅ ያደረጉት ከአንድ ወር በፊት ሕብረት አባል ሃገራት አዲስ ለሚመጡ ስድተኞች በአስቸኳይ ሊከፋፈላቸው የሚያስችል አሰራር እንዲኖር ጥሪ የሚያደርግ ሓሳብ ነው እየተከተለ ያለው ።
በዚህ ዓመት ውስጥ ወደ 46,000 (አርባ ስድስት ሺ) ስድተኞች ባሕር ተሻግረው ወደ ግሪክ ገብተዋል። በዚህ ዓመት ሁለተኛዋ የላቀ የስደተኞች ቁጥር የተቀበለች አገር ስፔይን ስትሆን 30,000 ( ሰላሳ ሺ) ስደተኛች ገደማ ገብተዋል። ከዚህ ሌላ 8,000 ( ስምንት ሺ) ወደ ጣልያን፣1,600 ( አንድ ሺ ስድስት መቶ) ወደ ማልታ፣ሌሎች 800 ገደማ ደግሞ ወደ ቆጵሮስ እንደገቡ ይገለፃል፡፡
የአውሮጳ ሕብረት ከምስራቃዊ አቅጣጫ የማእከላዊ ባሕር የሚዋሰኑና በስደተኞች መጎረፍ እየተማረሩ ያሉት አባል አገሮች ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ቆጵሮስ፣ግሪክና ቡልጋርያ ጥሪ እያደረጉ ያሉት ጥሪ።
የማእከላዊ ባህር ገዳይ ከሚባሉት የጉዞ መስመሮች ሆኖ እየቀጠለ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በ2019 እ.ኤ.አ. ብቻ እስከ አሁን ከአንድ ሺ (1,000) በላይ የስድተኞች ህይወት በሶስቱም የጉዞ መስመሮች ማለፉ ይገልፃል።
TMP 29/10/2019
ፎቶ ክሬዲት፤- ፎቶ ቨርቨሪዲ ቫሲሊስ / ሻተርስቶክ.ኮም
ካፕሽን ግሪክ- ሚይዝያ 5, 2019 መቶዎች ስደተኞች ወደ አውሮጳ ልትደርሱ እስከ ሰሜናዊ የግሪክ ድንበር ተጓዝ ለሚለው የማህበራዊ ሚድያ መልእክት አማነው እየተሰባሰቡ
ፅሑፉን ያካፍሉ