የተባበሩት መንግስታት ወኪሎች ስደተኞችን የማዳን ስራ እንደገና እንዲጀምሩ ለአውሮጳ ህብረት ጥሪ አቀረቡ

የአውሮጳ አገራት በሜዲትራንያን ባህርና በሊብያ ተይዘው የሚገኙትን ስደተኞች ለመርዳት በመንግስት የሚደረጉ የማዳን ስራዎች እንደገና  መጀመር አለባቸው ሲሉ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM)  የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጄንሲ (UNHCR)  በሐምሌ 21 ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

“ ባለፈው ግዜ የአውሮጳ መንግስታት መርከቦች/ጀልባዎች ህይወት አድን ስራዎች በማከናወን በሺዎች የሚገመቱ ሰዎች እንዲዱኑና ደህንነታቸው ወደ ተጠበቀ ወደቦች እንዲሄዱ አድርገዋል”  ይህን ዋና በጣም አስፈላጊ ስራና በግዝያዊ ድህንነታቸው ወደ ተጠበቀ ወደቦች እንዲሄዱ ማድረግ በአውሮጳ በአስቸካይ በመጀመር ሃላፊነታቸውን መጋራት አለባቸው፡፡ “ የበጎ አድራጊዎች ጀልባዎችም በተመሳሳይ መንገድ በጣም ወሳኝ የሆነ ሚና ተጫውተዋል፡፡  በባህር ላይ ያሉትን የሰዎች ህይወት በማዳናቸው መቀጣት የለባቸውም” በማለት ሁለቱም የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡

ከ2018 እ.ኤ.አ ጀምሮ በአውሮጳ ህብረት ህይወትን የማዳን ተልእኮ አልነበረም፡፡ የበጎ አድራጊዎች ጥቂት መርከቦች ብቻ ስደተኞችን ከመስጠም አደጋ ለማዳን ተሳትፈዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን የበጎ አድራጊዎች ስራ እንደ ጣልያን ያሉት አገሮች በማእከላዊ ሜድትራንያንን የሚካሄደውን ስደተኞችን የማዳን ስራ በመቃወም ጠንካራ አዲስ ፖሊሲ በማውጣታቸው ስራውን ለማካናወን ወደ ማይቻልበት ደረጃ ለመድረስ ተችለዋል፡፡ በዚህ አመት ቢያንስ 682 ስደተኞች ሜድትራንያንን ለመሻገር ሲሉ መስጠማቸውን አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM)   አስታውቀዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲና (UNHCR)   አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM)   በሺዎች የሚገመቱ በሊብያ ተይዘውና በእስር ቤቶች በአስከፊ ሁኔታ የሚገኙ ስደተኞችን እንድያግዙ ለአውሮጳ ህብረት ጥሪ አቀረቡ፡፡ በተጨማሪም የአውሮጳ ህብረት አገሮች የጥገኝነት ጠያቂዎችና የስደተኞችን ሰብኣዊ መብቶች እንዲጠብቁ የተባበሩት መንግስታት ወኪሎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

“ በቅድሚያ በአሁኑ ግዜ በሊብያ ተይዘው የሚገኙትን 5600 ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች ስርአት ባለው መንገድ ነፃ እንዲወጡና አስተማማኝ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ወይም ወደ ሌሎች አገሮች ወጥተው እንዲኖሩ እንጠይቃለን”  ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጄንሲ (UNHCR)    አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM)   ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ጀርመን ከአደጋ የዳኑትን ስደተኞች ለመቀበል አውሮጳውያን የጋራ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አአቀረበች፡፡ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሄይኮ ማስ የአውሮጳ ህብረት ከተቀሩት ቡዱን ስምምነት ሳይጠብቁ ስደተኞችን በማዳን ስራ ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረቡ፡፡

“ እኛ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአስገዳጅ ድርሻ /ኮታ ህብረት ደምብ እንፈልጋለን፡፡ አገራችን ሁሉ ግዜ የስደተኞች ድርሻዋን ለመውሰድ ዝግጁ ናት”  ሲሉ ለጀርሞን ክልላዊ ጋዜጣ ቡዱን ተናግረዋል፡፡

ጣልያን በባህር አደጋ ላይ ያሉትን ስደተኞችን በማዳን ስራ ላይ በቀረበው ሀሳብ ግምት ውስጥ በማግባት ላይ ስትሆን ይሁን እንጂ ብቻዋን ከአደጋ የዳኑትና በባህር ዳርቻዋ የደረሱትን ሰዎች የመቀበል ሃላፊነት እንደሌላት አስታውቃለች፡፡ የጣልያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ኤንዞ ሞቬሮ ሚላኔሲ ኮርየሪ ዴላ ሴራ የተባለው ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ “ ሁሉም ከባህር አደጋ የዳኑት ሰዎች ወደ ጣልያን ብቻ የማሄዱ ከሆነ ስደትን ለመከላከል ለሚደረገው አዲሱ የአውሮጳውያን የባህር ሃይል ጥረት እንደምትደግፍና ስደተኞች ጣልያን፣ ግሪክ ወይም የማልታ የባህር ዳርቻዎች ብቻ አይደለም የሚፈልጉት፡፡ እነርሱ አውሮጳን ነው የሚፈልጉት፡፡ ስለዚህ በአውሮጳውያን አሰራር/ስርአት መፍትሄ ማግኘት አለብን”  ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጣልያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ አውሮጳ ከመግባታቸው በፊት በአውሮጳውያን የቀረበውን በሰሜን አፍሪካ ለሚከፈቱት ክልላዊ የጥገኝነት ጠያቂዎች ማእከላት ያላትን ድጋፍ ገልፃለች፡፡ እነዚህ ማእከላት ስደተኞች በሜዲትራንያን የሚያደርጉትን አደገኛ ጉዞ ለመግታት ያስችላል፡፡ በተጨማሪም ጣልያን የአውሮጳ ህብረት ያደራጀውን ተቀባይነት ያገኙትን ጥገኝነት ጠያቂዎች ከአገራቸው ተነስተው በቀጥታ በረራ ወደ አውሮጳ እንዲሄዱ የሚያደርገውን ደንብ ትደግፋለች፡፡

TMP – 31/07/2019

ፎቶ፡- አሌሀንድሮ ካርኒሴር/ሹተርስቶክ. ኮም

የሜዲትራንያን ባህር ጉዞ ህገወጥ ስደተኞችን በመግደል ላይ ይገኛል፡፡