ስድስት የአውሮጳ አገራት ከተስማሙ በኋላ በባህር ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ታግተው የነበሩ ስደተኞች እንዲራገፉ ተደርገዏል

የሁለት ሳምንት አሰቃቂ የባህር ላይ እገታ አሁን መቋጫ ተደርጎለታል። ችገታው 356 ከነዚህ መካከል 90 ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህፃናት የሚገኙበት ስደተኞች ላይ በሜዲትራንያን ባህር ውስጥ የተደረገ ሲሆን፤ ከሁለት ሳምንት የስቃይ ግዜ በኋላ፤ ማልታ ወደብ ላይ እንዲራገፉ ፍቃድ አግኝቷል። ስድተኞቹ ከማልታ ሊቀባላቸው ወደ ሚችል የአውሮጳ አገር ይሄዳሉ ተብሏል።

የማልታው ጠቅላይ ሚኒስተር ጆሴፍ ሙስካት በትዊተር ገፃቸው በነሀሴ26 እንደገለፁት፤ እነዚህ ስድተኞች በማልታ መከላከያ ሃይል መኪኖች ተጭነው ከባህር ዳርቻ ራቅ ወዳለ ስፍራ ተወስደው በጦሩ ጥበቃ ስር ይቆያሉ።  ካሉ በኋላ ስድተኞቹ ወደ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ኤየርላንድ፣ ሉግዘምበርግ፣ ፖርቱጋልና ሮማንያ አገራት ይላካሉ እንጂ አንድም ሰው ማልታ ላይ አናቆይም ብለዋል።

ስደተኞችን ያሳፈረችው የነብስ አድን ጀልባ ( ኦሽን ቪኪንግ) ማልታ ባህር ዳርቻ ላይ እንድታራግፍ የነበረው ጭንቀት ከባድ ነበር። ይህም  የሆነው መጀመርያ የማልታ መንግስት ፍቃደኛ ባለመሆኑና የጣልያን መንግስትም ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠቱ ነበር።

የማልታና የጣልያን መንግስታት ከሁለት የጭንቀት ሳምንታት በኋላ ፍቃደኛ የሆኑት፤ ድንበር የለሽ ሃኪሞችና ኤስ ኤስ ሜዲትራንያን የተባሉ ግበረ ሰናይ ድርጅቶች የሰብአዊ ቀውስ አደገኛ ሁኔታ ላይ መድረሱን ለአለም ማሕበረሰብ መጮህ ከቀጠለ በኋላ ነው።

የድንበር የለሽ ሃኪሞች ግበረ ሰናይ ድርጅት አስተባባሪ ጃይ ቦርገር የሁለት ሳምንቱ የባህር ላይ እገታውን አስመልክተው እንደተናገሩት ነገርየው ዘስፈላጊ አልነበረም። ሰዎችን ለሁለት ሳምነታት ያህል በባህር ላይ አሰቃቂ ቆይታ እንዲያሳልፉ መበየን አይገባም ነበር። እነዚህ ሰዎች በየአገሮቻቸው ከሚገኙ ሰብአዊ ጥሰትና በሊብያ ካለው አስደናጋጭ የሰዎች መከራ ለማምለጥ የተነሱ መሆናቸው መረዳት አለብን ብለዋል።

ጃይ ቦርገር አክለው፤ የአውሮጳ መንግስታት በባህር ላይ ነብሳቸው የዳኑ ሰዎች አፋጣኝ የእርዳታ አሰራር መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል፤፤ ይላሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦፕን አርም በተባለችው  የስፔይን ግበረ ሰናይ መርከብ ላለፉት 20 ቀናት በባሀር ላይ የታገቱት ስድተኞችን መፍትሄ ሳያገኙ ሲሰቃዩ ቆይቷል። ስድተኞች ይታገቱበት ቀን እየጨመረ ሲመጣ ህይወታቸው ላይ ያንዣበበው አደጋ እየከፋ መጥቷል። በከፋ የጤና መታወክና በጭንቀት ውስጥ የገቡ የተወሰኑ ስድተኞች የማዳን ተግባር ግን ተደርጓል።

በመጨረሻም ባለፈው ነሃሴ 20/2019 83 ስድተኞች፤ በጣልያንም የባህር ዳርቻ በላምፓዶስ  እንዲራገፊ ተደርጓል። ከጥቂት ግዜ በሃላ ወደ ተለያየ የአውሮጵ አገራትይበተናሉ ተብለዏል።

TMP – 30/08/2019

ፍቶ፤በሃናሃ ዋላሴ ( MSF)

በነብስ አድን ግብርሀ ሃይል ህይወታቸው የተረፉ ስድተኞች በኦቨን ቪኪንግ ጀልባ ላይ