ጣልያን የህይወት ኣድን ጀልባዎች እንደምትቀጣ ኣስታውቃለች

የጣሊያን መንግስት ያለምንም ፍቃድ ወደ ጣሊያን ወደቦች የሚገቡ መንግስታዊ ያልሆኑ ህይወት ኣድን መርከቦች በከባድ ለማቅጣት ውሳኔ በማሳለፉ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ስደተኞችን የማዳን እንቅስቃሴ ይበልጥ ኣስቸጋሪ እንደምሆን ተገለጸ።

ድንጋጌው ትዕዛዞችን በመጣስ የጣሊያን የውሃ መስመሮችን የሚገቡ መንግስታዊ ያልሆኑ ህይወት ኣድን መርከቦች እስከ 50,000 ዩሮ ሚደርስ ለመቅጣት የጣሊያን የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ስልጣን ይሰጠዋል። በተጨማሪ፡ ተደጋጋሚ ጥሰቶች የሚፈጽሙ ደግሞ ጀልባቸው እንዲያዝ እና እስከ አመት ድረስ የመንገድ ፈቃዶቻቸው እንዲታገዱ ይደረጋል።

ፋር ራይት የሆኑ የአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ማቲቶ ሳልቪኒይህንን ውሳኔ የዚህ ሀገር ደህንነት ወደፊት የምንወስደው እርምጃ የሚጠብቅ ነውሲሉ ኣድናቆታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪ፡ ሳልቪኒበአገሪቱ እና በዓለም አቀፍ ሕጎች ሁሉ ላይ የሚጣጣሙ መሆናቸው በጣም እርግጠኛ መሆናቸውጨምረዋል። መጀመርያ በሳልቪኒ የቀረበ የመጀመርያ ድራፍት መርከቦችን ወደ ጣሊያን መሬት የምያመጥዋቸው ስደተኞች እያንዳንዳቸው እስከ 5,500 ዩሮ ታስቦ እንዲከፍሉ የሚደነግግ ነው። ይሁን እንጂ ከባድ የሆኑ ትችቶችን ከተለያዩ ወገኖች በመሰጠቱ፡ ፕሮፖዛሉ ተሻሽለዋል። የታቀደው ድንጋጌ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር ፖሊስ ምስጢራዊ ምርመራዎችን ለማካሄድ እና የሕገወጥ ዝውውር ተጠርጣሪዎች ላይ ክትትል ለማድረግ ይፈቅዳል።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ /ቤትና ሌሎች በጎ አድራጊ ድርጅቶች በቅርቡ በበጎ አድራጊዎች ህይወት አድን ጃልባዎች የታወጀውን አዋጅ ላይ ያላቸውን ጥልቅ ማሳሰብያ በመግልፅ ጣልያን አዋጁን እንደገና እንድትመለከተው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአውሮጳ አገሮች በማእከላዊ ሜዲትሪያንያን ህይወትን የማደን ጥረት በሚያቆመበት ግዜ የበጎ አድራጊ ጃልባዎች ከማንም ግዜ በላይ ወሳኝ ናቸው፡፡ሲሉ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ /ቤት የደቡባዊ አውሮጳ ጊዝያዊ ተወካይ ሮናነድ ሺልንግ ተናግረዋል፡፡ያለነሱ ቡዙ ህይወት እንደሚጠፋ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡

በሜዲትሪያንያን በህይወት አድን ስራ ከተሰማሩ በጎ አድራጊዎች መካከል ፍሬዴሪክ ፔናርድ የሜድትሪያንያን ኤስ ኤስ ዴሬክተር አንዱ ሲሆኑእውነታው ጥቂት ህይወት አድን ጃልባዎች ቢኖሩም ጥቂት አማራጮች ያሉዋቸው ሰዎች ምንም እንኳን አደጋ ቢኖሩም ባህር የመሻገር ውሳኔ ይቀጥልበታል፡፡ አሁን ያለው ልዩነት ካአለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር አራት እጥፍ የሚገመቱ ሰዎች እንደሚጠቁ ያሳያል፡፡ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሊብያ ባለው ጦርነትና የህይወት አድን ጀልባዎች ባለመኖራቸው ምክንያት በባህር ውስጥ የሚሞቱት ስደተኞች ከሁሉም ግዜ በላይ የላቀ እንደሚሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስጠንቁቀዋል፡፡በቅርቡ 700 የሚሆኑ ስደተኞች በሊብያ የባህር ጠረፍ በኩል ወደ ማልታና ጣልያን ለመድረስ ሙከራ እያደረጉ መሆናቸውን የእርዳታ ሰጪ ቡዱኖች አስታውቀዋል፡፡

በቅርቡ አመታት ጣልያን ወደ አገሪቱዋ የሚገቡትን ሰዎች ቁጥር ለመቀነስ ጠንካራ እርምጃ ወስዳለች፡፡ ባለፈው አመት ጣልያን ለበጎ አድራጊዎች ህይወት አድን መርከቦች የጣልያን ወደቦችን በመዝጋት እና ጥገኝነት ለማግኘት ብቁ ላልሆኑ ሰዎች የሚደረገውን ሰብኣዊ ከለላ አለማድረግ የሚል አዲስ ፖሊሲ አውጥታለች፡፡

TMP – 26/06/2019

ፎቶ ክረዲት፡ስቴፋኖጋሩ/ ሹተርስቶክ .ኮም

ሪዮሴጉራ፤  የተባለችው መርከብ ከሜሪትሪያንያን ባህር ከዳኑ 250 ስደተኞች ጋር በካልያሪ ወደብ