በአውሮፓ ውስጥ ቤተሰብ ጋር ማገናኘት ይበልጥ አስቸጋሪ ሆኗል

በአውሮፓ የሚወጡ ያሉትን ቤተሰብ መልሶ ማገናኘት ህጎች በመጸንከራቸው ስደተኞች ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመቀላቀልን ሁኔታ ኣስቸጋሪ እየሆነ ነው።

ከእነዚህ መካከል አንዱ የኤርትራ ስደተኛ የሆነች 2010 ጀምራ ለስምንት ዓመት ከልጆቿ የተለየች የኤርትራ ስደተኛ ሰሚራ* ናት። በስዊዘርላንድ ጥገኝነት ለማግኘት ጥያቄ ያቀረበች ሰሚራ፡ ከቤተሰቧ ጋር ለማገናኘት ደግሞ ሞክራለች፡ ነገር ግን ማመልከቻዋ ጥብቅ የቤተሰብ መቀላቀል መስፈርት ሳታሟላ በመቅረትዋ ተቀባይነት ልታገኝ ኣልቻለችም።

ዓለም አቀፍ የማኅበራዊ አገልግሎት ስዊዘርላንድ (ISS) የህግ አማካሪ ኤሚላ ሪቻርድ እንዳለውበስዊዘርላንድ ውስጥ ደንቦቹ በጣም ጠንከር ያሉ ናቸው። የቤተሰብ መልሶ ማገኛኘት ኣብዛኛው ጉዳቶች ደግሞ በሰዎች ምክንያት ጠፍተዋል። ይህም ማለት ከቤተሰቦቻቸው የተለዩ እና ለችግር የተጋለጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ልጆች ብቻ ይኖሮውናል። እነዚህ ህጻናት በየመንገዱ የመጥፋታቸው አደጋ ከፍተኛ ነው።  እንደነዚህ ያለ ተመሳሳይ ጉዳዮችን በብዛት እያየን ነን።  ይሄ የተረጋገጠ ነው። የዚህ አይነት ክስተት ምክንያት አንዱ  ደግሞ በአውሮፓ ውስጥ ያለው ጥብቅ የሆነ የኢሚግሬሽን ሕግ ነው።ሲሉ ኣስተያየታቸውን ገለጹ።

ከእናታቸው ጋር ለመገናኘት የሰሜራ ልጆች አደገኛ ጉዞውን ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ሞክረው ነበር። ነገር ግን በሊቢያ ተይዞው እንዲታሰረ ተደረገ። ሆኖም ግን ዩኤንኤችሲኣር ባደረገው ጥረት፡ ልጆችዋ ከሊብያ እስርቤት እንዲለቀቁ እና ስምንት አመታት ተለያይቶ ከቆዩ በኋላ ሰሚራ ከነልጆችዋ ለመገናኘት ችላለች።

ጥገኝነት ያገኙ በአውሮፓ ውስጥ ካሉ የቅርብ የቤተሰብ አባላት ጋር ለመገናኘት ተስፋ የሚያደርጉ ስደተኞች ረዥም እና አስቸጋሪ ሂደት ያጋጥማቸዋል። በኤርትራ የሚገኙ በርካታ ቤተሰቦች በኤርትራ በሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ ውስጥ ምንም የቪዛ ክፍል ስለሌለ ቤተሰብ ጋር ማገናኘት ማመልከቻዎችን ለማስገባት አስቸጋሪ ሆኖ አግኝተውታል። ስለሆነም ብዙ ኤርትራውያን በኢትዮጵያ፡ ኬንያ ወይም ሱዳን ማመልከቻዎች ለማስገባት ኣደገኛ የሆነ ጉዞ ያካሂዳሉ። ሆኖም ግን፡ በነዚህ ጎረቤት ሀገሮች የሚያደርጉት ማመልከቻዎች ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች ስለሌላቸው ማመልከቻቸውን ለማስገባት ችግር ይገጥሟቸዋል። እንደ አልጀዚራ ገለጻ አንዳንድ የኤርትራ የቆንስ / ቤቶች ከኢትዮጵያ ጋር የሰላም ስምምነቶች ከተደረጉ በኋላ ባልተለመደ መንገድ አገሪቱን የለቀቁ ሰዎችን የፓስፖርቶች ጥያቄ ውድቅ ማድረግ ጀምረዋል።

በቅርብ ዓመታት ኤውሮጳ የወሰደቹው ስጉም ስደተኞች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ አስቸጋሪ ኣድርጎውታል። ባለፈው ዓመት ጀርመን የደህንነት ጥበቃ ለተሰጣቸው ሰዎች የቤተሰብን ማገናኘት ቪዛ አቋቋመች። ነገር ግን፡ ወርሃዊ 1,000 ኮታ ቤተሰብ የመቀላቀል ቪዛዎች በወር ውስጥ ካለው ከፍ ያለ የማመልከቻ ቁጥር ጋር እንደማይመጥን ነው የሚነገረው። ሱደቸ ዛይተንግ የተባለው የጀርመን ጋዜጣ እንደገለጸው መርሃግብሩ እንደገና ከተጀመረ በኋላ፡ ባሉት አራት ወራት ውስጥ ጀርመን ካሉት ቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት 44,760 በላይ ማመልከቻዎች ተቀብለዋል።

ጀርመን በኢሚግሬሽን ላይ ያለውን አቋም በመጠናከር ስደተኞች ወደ አገራቸው የመመልስ ጥብቅ ህጎችን መከተል እና ህግወጥ ስደተኞች የገንዘብ ማበረታቻዎችን መስጠት ወደ ኣገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ የሚል ነው።  2017 በኢትዮጵያ፡ ሱዳን እና ከንያ  በሚገኙ የጀርመን ኤምባሲዎች ቤተሰብ ጋር የማገኛነት ጥያቄ ካቀረቡ ኤርትራውያን ስደተኞች ከግማሽ በላይ ውድቅ ተደርገዋል።

TMP – 28/06/2019

ፎቶ፥ ኒትፒከር/ ሻተርስቶክ  ኮም

በኑረምበርግ የፌደራል የስደተኞች ቢሮ (BAMF)