ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አዳዲስ የስደተኞች ማእከላት ለስደተኞች ሁለገብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው

አዲስ በወጣው ህግ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ ለስደተኞች ሁለገብ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ አዳዲስ ማእከላት እየተከፈቱ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

የመጀመርያው የስደተኞች ማእከል በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተከፈተ ሲሆን ባምባሲ ላይ ተጠልለው ላሉ ስደተኞች እና ለአከባቢው ህዝብ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ናቸው። ይህ የስደተኞች ማእከል በአከባቢው የሚገኙ ህዝቦች እንደ ልደት፣ ሰርግ፣ ፍቺ እና ሞት  የመሳሰሉ  ወሳኝ ሁነቶች የሚመለከት አገልግሎት እንድያገኙ እንዲሁም ሌሎች ሲቪላዊ ሰነዶችን እንድያገኙ በማገዝ ላይ ነው።  ይህ ማእከል በሀገሪቱ ካሉ 27 ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ማእከላት በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑ ተገልፀዋል።

እነዚህ ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጡ ማእከላት በአውሮፓ ህብረት አጋዥነት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮምሽን፣ በዩኒሴፍ፣ በኢትዮጵያ የወሳኝ ሁነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ እንዲሁም በስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ የጋራ ትብብር የተሰሩ ናቸው። ማእከላቱ የምዝገባ ማረጋገጫ፣ የማንነት መለያ ወረቀት፣ የሲቪላዊ ምዝገባ ሰነዶች በተጠየቁበት በአጭር ጊዜ መልስ የሚሰጡ ናቸው።

ለስደተኞች እና ስደተኞቹ ባሉበት አከባቢ ላለ ህዝብ ሁለገብ አገልግሎት በመስጠት በቀጣይነትም አዲስ በወጣው ህግ መሰረት ለሁለቱም ወገኖች ሁለገብ አገልግሎት በመስጠት እንዲወሃሃዱ የማደረግ ኋላፊነት ያላቸው ማእከላት ናቸው።ብለዋል በአሶሳ ከተማ የአከባቢው የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ተወካይ ዓምደወርቅ የኋላወርቅ።

ክሊመንቲን ንክዌታሳላሚ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮምሽን ተወካይ ሲሆኑ እሳቸውይህ  ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥ ማእከል ከፍተኛ የስደተኞች ቁጥር ያለው መንግስት ስደተኞች ከማእከላት ውጪ እንዲኖሩ እና እንዲሰሩ ለወጣው ፖሊሲ ለተግባራዊነቱ የምያቃላጥፍ ነው።ይላሉ።

አክለውምይህ በባምቢስ የስደተኞች ማእከል እየተሰጠ ያለ አገልግሎት በሀገር ደረጃ እውቅና ያለውን የሀገሪቱ የወሳኝ ሁነት ምዝገባዎች ከተሰጣቸው በኋላ በመላው ሀገር መንግስት የምያቀርባቸውን አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ ይረዳቸዋል።ብለዋል።

ኢትዮጵያ 900,000 በላይ ስደተኞች ከህዝቦችዋ ጋር እንዲወሃሃዱ ያምያስችል ፖሊሲ አውጥታ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። ይህ ፖሊሲ 2018 በሞሮኮ ማራኬሽ ከተማ ውስጥ ስደተኞች ሁሉገብ አገልግሎት እንድያገኙ በሚል የተደረሰ የጋራ ስምምነት አንድ አካል ነው።

TMP – 14/06/2019

ፎቶ አንሺ፦ በአልቫሮ ቪላንዌቫ / ሻተርስቶክ

ፎቶ በኢትዮጵያ ምዕራባዊ ክፍል በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚገኝ የገጠር አከባቢ