ከቱንዝያ በኩል የወጣ ጀልባ በመገልበጡ ምክንያት ቢያንስ የ65 ስደተኞች ህይወት ማለፉ ተሰማ
ዩኤንኤችሲአር እንደገለፀው ህገ ወጥ ስደተኞች ጭና ከቱንዝያ የተነሳች አንድ ጀልባ በባህር በመገልበጥዋ ምክንያት ቢያንስ 65 ሰዎች ህይወታቸው አልፈዋል።
አንድ በህይወት የተገኘ ስደተኛ እንደገለፀው እነዚህ ስደተኞች መይ 9 ቀን 2019 ላይ በሰሜን ምዕራብ የሊብያ ክፍል ከምትገኘው ዙዋራ ከምትባል ከተማ የተነሱ ናቸው። ስደተኞቹ በመሀል ወደ ሌላ ትንሽ ጀልባ እንዲሸጋገሩ ቢደረግም በነበረው ከፍተኛ ማዕበል ምክንያት ጀልባዋ ልትገለበጥ ችላለች።
በመሆኑም ከደቡባዊ የቱኒስ ከተማ ወደ ጣልያን ሀገር ሲያቀና የነበረ ይህ ጀልባ 45 ማይልስ ከስፋክስ ወደብ ከተጓዘ በኋላ አደጋው ሊደርስበት ችለዋል።
ቱንዝያዊ ዓሳ አጥማጅ 16 ስደተኞች ሊያድን ችለዋል። እነዚህ የዳኑ ስደተኞች በቱኒዝያወ የባህር ሀይል አማካኝነት ወጥተዋል። በህይወት የተገኙ እነዚህ ስደተኞች ለቱንዝያው የቀይ መስቀል ማህበር እንደገለፁለት በጣም ቀዝቃዛ በሆነው ባህር ላይ ለስምንት ሰዓታት ቆይተዋል።
“ይህ ቱነዝያዊ ዓሳ አጥማጅ ስደተኞቹ ባያይ ኖሮ አንድም በህይወት የሚቀር ሰው አይገኝም ነበር። እኛም ይሄንን ጉዳይ ልናውቅ የምንችልበት ዕድል ዝግ ነበር።” ብለዋል የቀይ መስቀል ተወካዩ ሞንጊ ስሊም።
አህመድ ቢላል ባንግልድሻዊ የ30 ዓመቱ ገበሬ እና በህይወት የተገኘ የአደጋው አካል ነው። እሱ እንዳለው አንድ የአጎቱ ልጅ እና ዘመድ ነበረው። “አንድ በአንድ ወደ ውሃው እየገቡ ህይወታቸው ሊያጡ ችለዋል።” ብለዋል።
65ቱ ስደተኞች በዚሁ መጥፎ አጋጣሚ ምክንያት ናቸው ህይወታቸው ሊያጡ የቻሉት። አደጋው፤ በዚህ በያዝነው የፈረንጆች አመት ጃንዋሪ ወር ላይ የተከሰተውን 117 ስደተኞችን የሞቱበት አደጋ ቀጥሎ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የታየበት አጋጣሚ ሆኖ ለመመዝገብ ችለዋል። በዚሁ አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ያጡት የሶስት ሰዎች አስካሬን የተገኘ ሲሆን አንድ ሰውም በቀጥታ ወዲ ሆስፒራል ተወስደዋል።
ከእነዚህ ስደተኞች አብዛኛዎቹ ባንግላዲሻውያን መሆናቸው የተሰማ ሲሆን ግብፃውያን፣ ሞሮካውያን፣ ቻዳውያን እንዲሁም ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ስደተኞችም አብሯቸው እንደነበሩ ለማወቅ ተችለዋል።
“ይህ አደጋ ለሌሎች በሜዲትራንያን በኩል ጉዞ ለምያስቡ አካላት ማሳሰብያ ሊሆን የሚችል አሰቃዊ አደጋ ነው።” ብለዋል የዩኤንኤችሲአር ልዩ የሜዲትራንያን ጉዳዮች መልእክተኛ ቪንሰንት ኮክተል።
በመጀመርያዎቹ የ2019 ሶስት ወራት ወደ 15,900 የሚጠጉ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂ ሰዎች በሜዲትራንያን በኩል ወደ አውሮፓ ምድር ለመድረስ ችለዋል። ይህ የምያሳየው ከ2018 ተመሳሰይ ጊዜ ጋር ሲወዳደር በ17% ቀንሰዋል።
TMP – 16/05/2019
Photo credit: ገነ አይስንኮ / ሻተርስቶክ
Photo caption: ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር ላይ
ፅሑፉን ያካፍሉ